ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቀድሞ የተናቁና የተዘነጉ አንዳንድ ዘመን አመጣሽ ከባዕድ የገቡ ችግሮች እጅግ አሳሳቢ አደጋ እየጋረጡ እንደመጡ በተለይ በዚህ ወቅት በግልጽ ዕየታዩ ነው፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ቀስ እያለ የሞቀና እያላመደ የተባባሰ የመባባስም ባሕርይ ስላለው የህልውና አደጋ የመጋረጥ ደረጃ (boiling point) ሲደርስ ሁሉ እዛ ደረጃ መድረሱን ሳናስተውለው በፍላት ኃይሉ ተቀቅለን ልንፈራርስ የምንችልበት አጋጣሚ ሰፊ ሆኗል፡፡ ይሄንን አዚማም የችግሩን ባሕርይ ከወዲሁ የተረዱ ግለሰቦችና አንድ ማኅበር በሀገራችን ግብረሰዶማዊነትና የጋረጠውን አደጋ፣ የደረሰበትን አሳሳቢ ደረጃ ለሕዝብ የማሳወቅ እንቅስቃሴ በዜግነታቸው ለሀገራቸው ወይም ለሕዝባቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ማንም ምንም ሳይላቸው ለሀገርና ለሕዝብ ባላቸው ፍቅር በግል ተነሣሽነት ብቻ በመንቀሳቀስ አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል አስመስጋኝ ሥራን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህ እንቅስቃሴ የሁላችንንም ንቁ ተሳትፎ የግድ የሚጠይቅ ነውና ሀገሬ ሕዝቤ ማንነቴ የምትሉ ሁሉ ሳትዘናጉና ሳይመሽ ተመሳሳይ ተግባር ለመሥራት ትተጉ ዘንድ በጥብቅ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ግብረሰዶም ማለት ምን ማለት ነው? ግብረሰዶም ማለት የሰዶም ሥራ ማለት ነው ሰዶም የሰዶማውያን ሀገር ናት ሰዶም በጥንት ዘመን ከ4ሺ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ሸለቆ ከተቆረቆሩ ከተሞች አንዷ ነች፡፡ ቢጤዋ ጎሞራም እንዲሁ በዚህ ሸለቆ በሰዶም አቅራቢያ የተቆረቆረች ከተማ ነበረች እነዚህ ሁለት ከተሞች ተቃጥለው ከጠፉ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በጨው ባሕር ተሸፍነው እንዳሉ ይገመታል፡፡
የእነዚህ ሁለት ከተሞች ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት 19፡1-22 ተቀምጧል፡፡ ባጭሩ ስናስቀምጠው ግን የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ተፈጥሮና ሃይማኖት ከሚፈቅዱት ወይም ከሚያዙት ተስማሚ ከሆነው የተቃራኒ ፆታዎች የወሲብ ተራክቦ የተለየና አጸያፊ በሆነ የተመሳሳይ ፆታ ወሲባዊ ተራክቦ የረከሱ የጎደፉ በዚህ አጸያፊ ግብራቸውም እግዚአብሔርን ያስከፉ ያሳዘኑ በአመፃ ሥራ ያበዱ ርኩስ መንፈስ የሰለጠነባቸው የነገሠባቸው እግዚአብሔርም በዚህ ኃጢአታቸው ተቆጥቶ ከሰማይ እሳትና ዲንን አዝንቦ ያጠፋቸው የሁለት ከተሞተ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም የዚያ አጸያፊ የተመሳሳይ ፆታ ወሲባዊ ግንኙነት መጠሪያ ሊሆኑ ቻሉ፡፡
ከዚያም በኋላ በሙሴ ሕግ ይሄንን ኃጢአት የሚፈጽሙ ሁሉ ያለ ምሕረት ይገደሉ ነበር፡፡ ዘሌዋዊያን 20፡10፣ ዘዳግም 23፡17 ሰዎች እግዚአብሔር መፍራትና ማምለክ ሲተው ለጣዖታትም ሲሰግዱ የዚህ ዓይነት ርኩስ መንፈስ እንደሚያድርባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራ፡፡ በመሆኑም ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ይሄ ኃጢአት በአሕዛብና በእስራኤል የተለመደ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ግን ግብረሰዶማዊያን የሌሉበት አንድም ሀገር እንደሌለ ይነገራል፡፡
እንደሚታወቀው በሚታወቅም በማይታወቅም ምክንያት ምዕራባዊያን በሀገራችን ላይ ጥርሳቸውን ከነከሱ ዘመናት አልፏል፡፡ አንደኛው ምክንያታቸው በቅርብ ጊዜው ታሪካችን ሀገራችን ኢትዮጵያ ለወንድም ሕዝቦች ማለትም ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ከዘር መድሎ(apartheid) አስተዳደርና ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲወጡና ቅኝ ግዛት እንዲያከትምለት እንደ ኔልሰን ማንዴላ ያሉ ተዋጊዎቻቸውንና መሪዎቻቸውን ከማሰልጠን አንሥቶ የራሷን የጦር መሪዎችንም በማሰለፍ ጭምር እጅግ ከባድ ኃላፊነትን ወስዳ፣ ለዚህ ላመነችበት ዓላማም እራሷን በግልጽ አውጥታ በማጋፈጥ የተለየ ትዕግስት ጽናት ጥረትና ቁርጠኝነት ጠይቋት በነበረውና ከባባድ ዋጋ ባስከፈላት በዲፕሎማሲውም (በአቅንኦተ ግንኙነት) እንዲሁ ያደረገችው የማይተካ ሚና ነው፡፡ ይህ ተግባራችን የምዕራባዊያንን ጥርስ አስነክሶ ከትናንት እስከ ዛሬ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ስውርና ግልጽ የበቀል እርምጃዎች ዳርጎናል፡፡ በአጭር ጊዜ የሀገራችንን መሬት ያዳረሰውን ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚቀንስ ታይቶ የማይታወቅ ፀረ-አዝርዕት አረም ከእርዳታ እህል ጋር ቀላቅሎ ከማስገባት አንሥቶ ካለን የተፈጥሮ ሀብትና አቅም አንፃር በትንሽ ድጋፍ ማለትም እንደ ማርሻል ፕላን በመሰለ ድጋፍ ያም ባይሆን ብድር ለመነሣትና ራሳችንን ለመቻል ዕድሉ እንዳለን ሁሉ ጠቀም ያለ ብድር ከቶውንም እንዳናገኝ በመከልከል ስንራብ ብቻ አዛኝ መስሎ ለመታየት ቢዘራ የማይበቅል የተቀቀለ እህል እስከ መወርወር ድረስ ለደረሰ ሴራ ለተሞላበት በቀል ሊዳርገን ችሏል፡፡ መራር ዋጋ አስከፍሎናል ወደፊትም ያስከፍለናል፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህ ሁሉ ጣጣ የተዳረግንባቸው ወንድሞቻችን አፍሪካዊያን ስለ እነሱ ስንል ለዚሁ ሁሉ የበቀል እርምጃ እንደተዳረግን የሚገባውን ያህል አለማወቃቸውና ዋጋና ክብር አለመስጠታቸው ነው፡፡
ይህ ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ የሚፈጥረው ግብረሰዶማዊነትን በሀገራችን የማስፋፋት ዓላማም ከዚሁ ሀገራችንን ከመበቀያ ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታም በከፍተኛ ደረጃ እየተሳካላቸው እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይህ ርኩሰት ወይም ችግር በሀገራችን አይታወቅም ወይም እንግዳ ነበር ይህ ማለት ግን ይሄ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ጨርሶ በሀገሪቱ አልነበሩም ማለት አይደለም ነገር ግን ያሉን (የነበሩን) አሁን እየተሸረሸሩ ያሉ ጠንካራ ባሕሎቻችን የወግ የሥነ-ምግባር የግብረ-ገብ ድንጋጌዎቻችንና ሃይማኖት ይህ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ይሄንን ድርጊት እንዳይሞክሩት አስሯቸው ኖሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዋናነት ሆን ብለው ባሴሩ ባዕዳን በተለይም የቱሪስት (የጎብኚ) መዳረሻ በሆኑ የሀገራችን ከተሞች በጎብኝዎች (በቱሪስቶች) አማካኝነትና በተራድኦ ድርጅቶች ሳቢያ ወደ ሀገራችን በሚገቡ ባዕዳን በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደም ይህን ግብረሰዶማዊነትን በሀገራችን የማስፋፋት ሴራ ይከወን የነበረው በሥውር ነበረ ይህ በሥውር ይሠራ የነበው ሴራ ከሚፈልጉት ውጤት እንደደረሰ ካወቁ በኋላ ግን በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት የእኛን ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የአፍሪካ መንግሥታትን በግልጽ በይፋ በየሀገሮቻቸው ያሉ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴና ተግባር ሕገወጥና ወንጀል መሆኑን ሽረው ሕጋዊ ካላደረጉ በስተቀር ከእንግዲህ እርዳታም ሆነ ብድር እንደማይሰጡ ይፋ አድርገዋል፡፡ እስከአሁን ለዚህ ከቅኝ ግዛት ላልተናነሰ አዋጅ ምላሽ የሰጠችው ጋና ብቻ ናት “እርዳታና ብድራቹህ በአፍንጫችን ይውጣ ለእርዳታና ብድር ብለን ከባሕላችንና ሃይማኖታችን ውጭ የሆነና የሚቃረንን ፀያፍ ድርጊት አንቀበልም” በማለት፡፡ ምዕራባዊያን ዛሬ በሥውርና በይፋ አስገዳጅ ጫና ከማሳደራቸው በፊት አስቀድመው መደላድል ሲፈጥሩ እንደነበሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከሠሯቸው ተንኮል የተሞላባቸው የመደላድል ሥራዎች አንዱ የሴት ልጅ ግርዛትን ጎጅ ባሕል አሰኝቶ ማስቀረት ነበር፡፡ መቶ በመቶም ተሳክቶላቸው የሴትልጅ ግርዛት “ልብ በሉ እያወራሁ ያለሁት ስለሴት ልጅ ግርዛት እንጂ ስለ ብልት ትልተላ አይደለም” እናም የሴት ልጅ ግርዛትን እነሱ ከሚያወሩት አንፃር እውነት ይሁን አይሁን ወይም ጉዳትና ጥቅሙን ትርፍና ኪሳራውን በቅጡ ለመረዳት ሳንሞክርና ሳናጠና በየዋሕነት እነሱ ያሉትን ብቻ አምነን በመቀበል የሴትልጅ ግርዛት ሕገ ወጥ እንዲሆንና እንዲቀር ተደረገ፡፡ ይህ ጉዳይ ለግብረሰዶማዊነት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ በሴት ልጅ ግርዛት ጉዳይ ላይ በሠነድ ደረጃ ያዘጋጀሁት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ነበር፡፡ ከ4 ዓመታት በፊት ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ቀርቤ ግርዛት እንዲቀር ከሚሠሩ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመከራከር ያቀረብኩት ጥያቄ የመንግሥት አካላት መንግሥት አቋም የያዘበት ጉዳይ ነው በማለታቸው ምክንያት ተቀባይነት በማጣቱ ወደ ሕዝቡ ማድረስ ሳልችል ቀርቻለሁ፡፡ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ አሁን ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ማለትም እንደ ሀገረ እግዚአብሔርነቷ ለዚህ አስነዋሪ የምዕራባዊያን አዋጅ አቋም በመውሰድና ምላሽ በመስጠት የሚቀድማት ሊኖር ባልተገባ ነበር፡፡ እንዲያውም ጽድቁ ቀርቶ እንዲሉ ጭራሹኑ አምና የሃይማኖት መሪዎች ግብረሰዶማዊያንንና ድርጊታቸውን በማውገዝ ሊሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ መግለጫውን ሳይሰጡ እንደተለጎሙ እንዲበተኑ ማድረጉ ለእነዚሁ ምዕራባዊያን የጥፋት አዋጅ እጅ መስጠቱ ወይም መንበርከኩ ይሆን የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡ መንግሥት ተጠቃሚ የሚሆን መስሎት ለእርዳታና ብድር ብሎ በይፋም ባይሆን በስውር የእነ እንግሊዝን አዋጅ ከተቀበለና ሥራ ላይም ካዋለ ከእነሱ እጅ በእርዳታና ብድር ስም አንድ ሚሊዮን ብር አግኝቶ ከሆነ በዚህች አንድ ሚሊዮን ብር ሰበብ በገባው ጦስ ሕዝቡን በመቶ ቢሊዮን ብር ከማይመለስ ከማይፈወስ ከማይጠገን ከማይቀረፍ የማኅበራዊ ቀውስ አዘቅት ውስጥ እንዳሰመጠው ይወቀው፡፡ ሀገር የምትለማውና የምትገነባው የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ጤና በመጠበቅ፣ የሰው ልጆችን ሰብእና ሥነ-ልቦናና ኅሊና በሚያንጹ በማይቀፉና በማይኮሰኩሱ እሴቶችና አዎንታዊ ግብሮች እንጅ ኅሊናን በሚጎዱ ሥነ-ልቡናን በሚያቃውሱ ሰብእናን በሚያረክሱ በሚያዘቅጡ ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ በሚፈጥሩ ርኩስ ዘግናኝና አጸያፊ ግብሮች አይደለም፡፡ መንግሥት ማለት የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጤና የሚጠብቅ ወይም የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አካል ማለት እንጂ የገዛ ሕዝቡን ለማያውቀው አደጋ ጥቃት አጋልጦና አሳልፎ የሚሰጥ የሚያስጠቃ አካል ማለት አይደለም ማልማትና ማጥፋት ምን ማለት እንደሆነ ለይተን ልናውቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ አካል ሁለት ዓይነት ሰብእና ሊኖረው አይችልም፡፡ አልያም አንደኛው የማስመሰል ወይም የውሸት ነው፡፡ ባለሥልጣኖቻችን የዚህን ችግር ጉዳት እንደራሳቸው አድርገው እንዲያዩት ያስፈልጋል፡፡ በእኛና በልጆቻችንስ ላይ ቢደርስ በሚል እሳቤ የሰለባዎች ሕመም ሊሰማቸው ስለእነሱም ሊገዳቸው ያስፈልጋል፡፡ የመሪነት ትርጉምም ወይም ሰብእና ይሄው ነው፡፡ ከእኛ አይድረስ እንጅ የራሱ ጉዳይ ነው መባል የለበትም፡፡
ከኢትዮጵያ ሕዝብ 97%ቱ ሃይማኖተኛ ነው 3%ቱ ብቻ ሃይማኖት አልባ ነው፡፡ 97%ቱ ሕዝብ ሃይማኖቱ ግብረ ሰዶማዊነትን አጥብቆ ያወግዛል 3%ቱ ሃይማኖት አልባ ቢሆንምና በሃይማኖቱ ምክንያት የሚያወግዘው ባይሆንም ይሄንን ርኩስ ጸያፍ ግብር የሚጸየፍና የሚያወግዝ ጽድት ያለ እኩሪ ባሕል አለው፡፡ በመሆኑም 100% ይሄንን አጸያፊ ግብር የሚጸየፍ ሕዝብ ባለበት ሀገር በምዕራባዊያን ተጽእኖ ወንጀልነቱና ወጉዝነቱ ቀርቶ መንግሥታዊ ፈቃድና ይሁንታ እንዲኖረው ማድረግ ጨርሶ የማይታሰብና እብደትም ነው፡፡ የምዕራቡን ዓለም ሕዝብ የባሕልና ሃይማኖት እሴት ይዘት ያየን እንደሆነ በተለይ በዚህ ዘመን ሃይማኖት አልባነትን እንደዘመናዊነት እየቆጠሩ በመሆኑ ሃይማኖተኛነት በሸመገሉ ሰዎች ብቻ የተወሰነና የሃይማኖተኛው ቁጥር እጅግ አነስተኛ ሃይማኖት አልባው ሕዝብ ቁጥር ደግሞ እጅግ በርካታውን ቁጥር የያዘ ሆኗል፡፡ ከባሕላቸውም ጋራ ከተቆራረጡና ዘመናዊነትን ባሕላቸው አድርገው ከያዙም ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ በመሆኑም ይሄንን ርኩስና ጸያፍ ግብር ሊጸየፉ፣ ሊያርቁ፣ ሊያወግዙ የሚያስችላቸው የአስተሳሰብ አጥር የላቸውም ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ነው ያለ አንዳች ሀፍረትና መሸማቀቅ ሳይቸገሩ በመንግሥቶቻቸው ደረጃ ሳይቀር በይፋ ለመቀበልና ሕጋዊ ለማድርግ የበቁት፡፡
የሚገርመውና እጅግ የሚያሳዝነው ግን መንግሥቶቻቸው ወይም ሃይማኖት አልባው የሕዝባቸው ክፍል ይሄን መቀበሉ ሳይሆን በሃይማኖት ተቋሞቻቸው ደረጃም ክርስትናን እንቀበላለን እያሉ ክርስትና በግልጽና በጽኑ የሚያወግዘውን ይሄንን ርኩስና ውጉዝ ግብር በዓለም ዓቀፍ ባሉ ቅርንጫፎቻቸው ደረጃም ጭምር በይፋ ተቀብለው ወይም ሕጋዊ አድርገው ወንድን ከወንድ ሴትን ከሴት ጋራ ሥርዓት እየፈጸሙ ማጋባታቸው ነው፡፡ የሃይማኖት መሪዎቻቸውም ግብረ ሰዶማዊያን እንደሆኑ በየጊዜው የሚወጡ ይፋዊ የብዙኃን መገናኛ የዜና መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ እዚህ ሀገራችን ውስጥ ያሉ በእነሱ የሚደገፉና የእነሱ ቅርንጫፍ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት የተባሉትም ከ10 ዓመታት በፊት ተቀብለዋል ተብሎ ውዝግብ ተነሥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የችግሩ ተጠቂ በመሆናቸው በሚደርስባቸው ሥነ-ልቡናዊ ቀውስ መታወክ ሕመም የሞራል(የቅስም) ሥብራትና ውድቀት የተነሣ ለሀገርና ሕዝብ እርባና ቢስ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ተግተው ከተገኙም ባሉበት ወይም በያዙት ቦታ ሆነው የሚያገላቸውንና ያልተቀበላቸውን ማኅበረሰብ በመበቀል እሴቶቹን በማፈራረስ ተግባር ላይ እራሳቸውን ጠምደው ፀረ-ማኅበረሰብ ሆነው ነው፡፡ እንግዲህ እንዲህ ዓይነት ግለሰቦች እንዲበራከቱ ከዚያም እንዲህ ዓይነት ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ዕድል መስጠት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለእናንተው እተወዋለሁ፡፡
ለመሆኑ የዚህ ችግር መንስኤው ምንድን ነው? ብንል መንስኤው የህክምና ሰዎች በሽታ ነው ሲሉት መንፈሳዊያኑ ወይም የሃይማኖት ሰዎች ደግሞ ጋኔን ወይም ርኩስ መንፈስ ነው ይላሉ፡፡ እንዴት መሰላቹህ ነገሩ እንዲህ ነው ይህ በሽታ ወይም ርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች ያላቸውና መፈጸም የሚፈልጉት ወሲብ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ማለትም ወንድ ከሴት ሴት ከወንድ ጋር መራቢያ አካሎቻቸውን በመጠቀም ሳይሆን በተፈጥሮ ምንም ዓይነት ወሲባዊ ስሜት ከማይገኝባቸውና ለዚህ አገልግሎት ካልተፈጠሩት ከመጸዳጃ ጀምሮ ሌሎች ቀዳዳ ወይም ጎድጓዳ የሰውነት ክፍሎችን በመጠቀም ከዚህ ወጣ ሲልም እራሳቸውን ለገራፊ በመስጠትና በማስገረፍ የወሲብ ፍላጎታቸውን የማርካት ጤነኛና ትክክለኛ ያልሆነ ፍላጎት ነው፡፡ ይህ በሽታ ወይም ርኩስ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች ናቸው እንግዲህ ከሕፃናት ጀምሮ እስከ ዐዋቂዎች ድረስ ወንዶችን በመድፈር ከዚያም በገንዘብ ኃይልና በተለያዩ ሐሰተኛ ማጥመጃወች የደፈሯቸውን ሰዎች ከዚያ ሕይወት እንዳይወጡና በሂደትም ሱስ እንዲሆናቸው በማድረግ የእነሱ ርኩሳዊና ጸያፍ የወሲብ ባሪያ እያደረጉ የግብረሰዶማዊያን ጥቃት ሰለባዎችን ተጠቂዎችን ወይም እራስን እስከማጥፋት በሚደርሰ የሥነ-ልቡና ቀውስ ዘወትር የሚታወኩ የሚረበሹ የሚጨነቁ ዜጎችን ከቀን ወደቀን በአስደንጋጭ አኃዝ እያበራከቱ የሚገኙት፡፡
ይህ በሽታ ያለባቸው ወንዶችም ሆነ ሴቶች በበሽታው ወይም በመንፈሱ ምክንያት ከውስጣቸው በሚፈጠር አስገዳጅ ስሜት የወሲብ ሕይዎትን ማለትም ወንድና ሴት በመራቢያ አካሎቻቸው የሚፈጽሙትን ተፈጥሯዊና ትክክለኛውን የወሲብ አፈጻጸም የሚጀምሩት በጣም በልጅነት የእድሜ ዘመናቸው ነው፡፡ ወደዚህኛው ማለትም ጸያፉና ተፈጥሯዊ ወዳልሆነው የወሲብ አፈጻጸም ተሻግረው ሰዎችን ወደማጥቃት የሚቀየሩት ወደ አቅመ ሔዋንና አቅመ አዳም ደረጃ እየደረሱ ሲሄዱና ከበሽታቸው የተነሣ በተፈጥሯዊው የወሲብ አፈጻጸም ካለመደሰት ችግራቸው የተነሣ ነው፡፡ እንደ የሕክምና ባለሙያዎች አባባል ይህ በሽታ እንደ ማንኛውም ሕክምና እንዳለው በሽታ መዳን የሚችል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ መንፈሳዊያኑም እንዲሁ ይህ ርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸውን ሰዎች እንደማንኛውም የርኩስ መንፈስ በሽታ ማዳን እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ግን በእነኝህ ሁለት የመፍትሔ ተቋማት መፍትሔ እንደሚያገኙ ቢያውቁም በሽተኞቹ ወይም ሕመምተኞቹ ከግል ስድ ሰብእናቸው የተነሣ መፍትሔውን ባለመፈለጋቸው በየጊዜውና በየቦታው ሰለባዎቻቸውን በማጥመድና በማጥቃት ወይም በመድፈር የወንጀል ተግባር በመጠመድ የብዙ ሕፃናትና ወጣቶችን ሕይዎት ያበላሻሉ፡፡
ምዕራባዊያን መንግሥታት የሦስተኛውን ዓለም መንግሥታት ለማስገደድ የሚጠቀሙበት የሕጋዊነት ሽፋን አንዱና ዋነኛው የሰብአዊ መብት ወይም የግለሰቦችን ወይም የአናሳ ቡድኖችን መብት ከማስከበር አንፃር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ሰብአዊ መብት ይበሉ እንጅ እንዲሠራ እንዲደረግ የሚፈልጉት ግን ኢሰብአዊ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም ሰብአዊ መብት የሚለውን ቃል ፍጹም ያለቦታው እየተጠቀሙበት እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ ይህች “ሰብአዊ መብት” (human right) የምትባል ቃል ጋጠወጦችና ደጋፊወቻቸው ለጸያፍ ድርጊቶቻቸውና አስተሳሰቦቻቸው መሸፋፈኛ ሲጠቀሙበት በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ጠልቆ ለመረመረው ግን የሚጠቅሱት ቃልና ድርጊታቸው ፍጹም ተቃራኒ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ “ሰብአዊ መብት” ማለት ሰው የመሆን መብት ማለት ነው ይሄም ማለት የሰውን ልጅ እንደሰውነቱና እንደ ማኅበራዊ ፍጡርነቱ ከሌሎቹ ፍጡራን የሚለየውንና የሚያልቀውን ኅሊናውን ለጸጸትና ለጉዳት የማይዳርጉ ተስማሚ አስተሳሰቡንና የጋራ ጥቅሙን ማለትም ማኅበራዊነቱን ጠብቆ ለማኖር ያስችለኛል ብሎ በጋራ ስምምነት የቀረጻቸውን ባሕል፣ ወግ፣ የግብረ-ገብ(የሞራል) ድንጋጌዎችን፣ ሃይማኖት ወዘተ. መጠበቅ መንከባከብ ማክበር ማለት እንጅ የአዕምሮ ጤና ዕክል ያለባቸው ሰዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጤናማ ኅሊና የሚጸየፈውን የሚቀፈውን ሥነ-ልቡናን የሚጎዳውን ከሰውነት አንጻር ተቃርኖ ያለውን የተለየ ሐሳብና ድርጊት ያለ ሀፍረት በድፍረት የትም ቦታ በነጻነት መፈጸምና አፈንጋጭ ድርጊት ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ የጋራ መተዳደሪያ ደገኛ ሥርዓት ማዕዘናቱን ለድርድር ማቅረብና አለማቅረብ፣ ለመጠበቅ ለማክበር የመፈለግንና ያለመፈለግን ጉዳይ የሰዎችን የአዕምሮ ጤና ደረጃና ደኅንነት መለኪያ መመዘኛውም ናቸው፡፡ አቤት! ደኅና የመሰለ ነገር ግን ያበደ የኅብረተሰብ ክፍል አለ ማለት ነው ጃል? አዬ ስምንተኛው ሽህ፡፡
የግለሰብ ወይም የአናሳ ቡድኖች መብት ማለትስ ምን ማለት ነው? የሚከበረውስ እስከምን ድረስ ነው? የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ለመመለስ ሌላ ቦታ ሳንሄድ በየሀገሮቻቸው ግብረሰዶማዊነትና ግብረሰዶማዊያን እንደዛሬው ሳይስፋፋና የወሳኝነት ቦታና ሥልጣን ሳይቆጣጠሩ የያዙትንም ኃይል ተጠቅመው በፈጠሩት ጫና ግብረ ሰዶምንና ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያወግዙና ሕገ ወጥ የሚያደርጉ የቀደሙ ሕግና ደንቦቻቸውን አስለውጠው አሽረው አስቀይረው ግብረ ሰዶማዊነትን ሕጋዊ ሳያደርጉ በፊት የነበሩ የየሀገሮቻቸውን ሕጎችና ደንቦችን መለስ ብሎ ማየት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በግብረ ሰዶማዊያኑ ብርታት ድራሻቸው የጠፋ የእነዚህ ሀገሮች የቀደሙት ሕጎች የግለሰብ ወይም የአናሳ ቡድኖች መብት የሚከበረው ከብዙኃኑ ወይም ከኅብረተሰቡ የጋራ ጥቅም ሰላም ደኅንነት ጋር እስካልተቃረነና ኅብረተሰቡ ተቀብሎት የሚኖረውን ባሕል ወግና ሃይማኖት እስካለተፃረረ ድረስ ነው ይሉ እንደነበረ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ዛሬ እነዚህ ግብረ ሰዶማዊያን ከሀገሮቻቸውም አልፈው በሌሎች ሀገሮች ጫና በመፍጠር በሀገሮቻቸው ላይ ያደረሱትን የሞራል (የግብረ-ገብ) ድንጋጌዎችንና ጠቃሚ ሃይማኖታዊ እሴቶችን ውድቀት በሌሎች ሀገሮችም ላይ ለማድረስ በከፍተኛ ጥረት ላይ ናቸው፡፡
ለእነዚህ መንግሥታት አንድ አመክንዮአዊ (Logical) ጥያቄ ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እነሱም በግልጽ እንደሚያውቁት ሁሉ ማንም የግብረ ሰዶም ጥቃት ሰለባ የሆነ ሰው ወዶና ፈቅዶ ወደዚህ ሕይወት የገባ ከዜጎቻቸው አንድ እንኳ አይኖርም፡፡ ነገር ግን በልጅነት ወይም በወጣትነት ዘመናቸው በደረሰባቸው የመደፈር አደጋ እንጂ፡፡ ከዚያም በኋላ ሁኔታው በሚፈጥርባቸው የሥነ ልቦና ቀውስ ራስን የመጣል ከሰዎች ራስን የማግለልና ብቸኝነት ለአጥቂዎቻቸው ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ ፣ በተጨማሪም አጥቂዎቹ ተጠቂዎቹን ከዚያ ሕይወት እንዳይወጡ በሚፈጥሩት የማጥመጃ ሴራ ታሥረው የዚህ ችግር ሰለባ እንደሆኑ ይቀራሉ እንጂ፡፡ በመሆኑም እነኝህን ወንጀል የተፈጸመባቸው ሰለባዎች ከዚህ ከማይፈልጉትና እራስን እስከማጥፋት ከሚያደርስ የሥነ-ልቡና ቀውስ ከፈጠረባቸው ጥቃት ችግር ለማውጣትና ወደ ጤናማው ሕይወት እንዲመለሱ የሚያስችላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግና የሠቀቀን እንባቸውን ከማበስ ይልቅ ግብረ ሰዶማዊነትን ፈቅደውና ሕጋዊ አድርገው እነዚህን ተጠቂዎች በዚያ የሥነልቦናና አካላዊ ሕመም ስቃይ ውስጥ ሆነው የእነዚያ ወንጀለኞች ደፋሪዎቻቸው የዘለዓለም የወሲብ ባሪያ እንዲሆኑ ማድረግ ፍጹም የለየለት ኢሰብአዊነትና አረመኔያዊነት መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የሰብአዊነትና የፍትሕ ጥያቄና እሴት በውስጣቹህ ሞቶ ተቀብሯል፡፡ ከዚህ በኋላም ስለ ፍትሕና ሰብአዊነት(justice and humanity) የምትናገሩበት አንደበት ከቶውንም ሊኖራችሁ አይችልም በአንባ ገነኖቹም ላይ የወቀሳ ጣታችሁን ለመቀሰር የሚያበቃ የሞራል (የግብረገብ) ብቃት የላቹህም ምክንያቱም በግልጽ ማየት እንደሚቻለው መንግሥቶቻቹህ በቁርጠኝነት እየሠሩት ያለው ሥራ የወንጀለኞችን ግፈኛና ጸያፍ ጥቅም የሚንከባከብ የሚያበረታታና አስነዋሪ አጸያፊ ሥራቸውንም የሚባርክ ይሁንታ የሚሰጥ የሚያስፋፋ ሰለባዎችን ወይም ተጠቂዎችን ለከፋ ግፍ ያልተጠቁ ወገኖችንም ለዚህ አደጋ የሚዳርግ ነውና፡፡ እናስ? ይሄንን ግልጽ ሀቅ ሊያስተባብል የሚችል አንዳች የመከራከሪያ ነጥብ (argument) ሊኖራቹህ ይችላልን? ሚዛኑ ፍትሕና ሰብአዊነት ከሆነ ከቶውንም ሊኖራቹህ አይችልም፡፡ በመሆኑም እናንት የምትሠሩትን ሳታውቁ የግብረሰዶማዊነት (የወንጀለኝነት)እንቅስቃሴ ቃፊር የሆናቹህ ሀገራት መንግሥታት ሆይ ከእንቅልፋቹህ ንቁ ምን እየሠራቹህ እንደሆነም ልብ ብላቹህ ተመልከቱና ተመለሱ፡፡ ለተበዳዮችና የግፍሰለባ ለሆኑትም ቁሙ፡፡ ያኔ ለሰብአዊነትና ለፍትሕ ቆሞናል ለማለት የሞራል ብቃቱ ይኖራቹሃል፡፡ ይሄንን ስታደርጉ እንደ ፖለቲከኛና እንደ ሕዝብ መሪ የተሸለ ማሰብ መቻላችሁንም ታስመሰክራላቹህ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ያላችሁን ብስለት(maturity) ግብረ-ገብነት(morality) ሰብእና(personality) በሕዝብና በታሪክ ፊት ለትዝብት ትዳርጋላቹህ፡፡
በሀገራችን በቀደመው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ይሄንን ወንጀል ፈጽሞ የተገኘን ወንጀለኛ የቅጣት ጣሪያ 15 ዓመታት ነበር በአዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ደግሞ ይህ የጽኑ እሥራት ዘመን ወደ 25 ዓመታት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጅ ይሄንን ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ወንጀለኞችን እያደኑ ለፍርድ የማቅረቡ ሥራ አበረታች እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በሌሎች ሀገሮች የማረሚያ ቤቶች ተሞክሮዎችና በሀገራችንም እንዳለ እንደሚወራው ሁሉ በዚህ ወንጀል ወይም በሌላ ተገኝተው የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ማረሚያ ቤት ገብተውም እዛ ውስጥ ያሉትን ታራሚዎች እንደሚደፍሩ ይነገራል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ግብረሰዶማዊያን የሚያደርሱትን ጥቃት ከመግታት ወይም ከመቆጣጠርና ምስኪን ሰለባዎችንም ከመታደግ አኳያ በሕጉ የተጣለባቸው ፍርድ እንደገና ተከልሶ ከእሥራቱ በተጨማሪ እንዲኮላሹ ማድረግ ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን መገንዘብና እንዲስተካከል ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
እናም እንግዲህ ይህ ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ተረድተን ከግለሰብ እስከ ተቋማት በተለይም የብዙኃን መገናኛዎች የማይመለከተው አይኖርምና ሁሉም በቆራጥነት ይሄንን ርኩሰት መዋጋት ይኖርበታል፡፡ ጉዳዩን ተጸይፎ ዝም ማለትና ራስን ማግለል ጭራሽም ላለመስማትና የጋረጠብንን አደጋም ላለመነጋገር መፈለግ መሸሽ ለችግሩ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና እንደሚረዳ አንጅ ምንም የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ጊዜ ሳናጠፋ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ካለሆነ ግን ሩቅ በማይባል ጊዜ ልጅ ወልዶ ማሳደግና ማስተማር እንደ አንዳንድ ይህ ችግር ሥር እንደሰደደባቸው ሀገሮች ከወጣንበትና ከሄድንበት በሰላም ለመመለሳችንም እርግጠኛ የማንሆንበት የመሳሪያ ድምጽ ጩኸት አልባ የሰላም እጦትና ሁከት ችግር ውስጥ እንደርሳለን፡፡ ማንም የዚህ ችግር ሰለባ ላለመሆኑ ምንም ዓይነት ዋስትና ሊኖረው አይችልም፡፡ ሀገርና ማንነት የሚጠፉት በአጥፊዎች የጥፋት ሥራና ብርታት ሳይሆን በዜጎች፣ በሚያገባቸው፣ ወይም በተቆርቋሪዎች ዝምታ ነው፡፡ ይህ ችግር ምንም እንኳ በእንጭጩ የምንልበት ጊዜ ያለፈ ቢሆንምና በየአቅጣጫው በየትምህርት ቤቱና በሌሎችም ቦታዎች በሚዘገንን ሁኔታ እንዲህ ተደረገ እየተባለ እንደምንሰማው ሁሉ ማናችንም ከምንገምተው በላይ ውስጥ ውስጡን ተጋግሞ የተስፋፋ ችግር በመሆኑ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴና ዘመቻ ካላደረግን በስተቀር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ መድረሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ እረገድ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እስከ ባሕላዊና ማኅበራዊ አደረጃጀቶች ድረስ ያሉ ሁሉ ግንባር ቀደምና ንቁ የተሳትፎ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን ነገ ሳይሆን ዛሬ ከዛሬም አሁን፡፡
ዕድሉ ያላቸው አጋጣሚዎች የሚፈቅዱላቸው የግብረገባዊ እሴት አቀንቃኝ (moralist) የሆኑ ዜጎች ሁሉ እዚህ ጽሑፍ ውስጥ ለምዕራባዊያን መንግሥታት የቀረቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች(arguments) እንዲደርሳቸው በፈለጓቸው መንግሥታት ቋንቋዎች በመተርጎም ለእነኝህ ተሳስተው ለማሳሳት ለሚጣጣሩት መንግሥታትና የብዙኃን መገናኛዎቻቸውም ለማድረስ የሚፈልጉ ቢኖሩ በእጅጉ ይበረታታሉ፡፡
amsalugkidan@gmail.com
aradaw says
Our country has so many problems from social, political to economic. I found this piece very offending and out of date. This type of discrimination based on sexual orientation is immoral and illegal. I am very sorry for the writer who still live back in the 16th century. I would like to refer the writer to what happens in other African countries who propagated discrimination based on sexual orientation, the whole world was against them and above all human right organization. Dear Ato Amsalu, how on earth you propose inhuman actions to innocent people. These are the same people like you the only thing is their sexual orientation different than you. You must accept differences and become tolerant and compassionate to fellow human beings. I have friends, family members who are gay and lesbian, they are wonderful law abiding , kind and compassionate people. What ever they do in their bed room is not your and my business, as it is their business what we do in our bed rooms. I hope you come to your senses to accept fellow human beings for who they are. First of all who are we to judge others. Let us love each other, Lets us work hard to liberate our people from the yoke of tribal dictators. Let us turn our effort and energy to the enemy of our people. Mr. Amsalu be a human who loves all people regardless of their color, race sexual orientation.
ተስፋዬ says
የዝሙት መንፈስ ስለተጠናወተህ የት ይገባሃል?ድንጋይ የሰይጣን ማደሪያ ስለሆንክ አይገርምም አታላይ !!!ከ አንድ ቀን የመንፈስ ባርነት የ ሺ ዘመን የስጋ ባርነት አይሻልም::አሃ ይህንን ልትጭኑብን ነዋ እንታገልልህ የምትሉን ?
aradaw says
I hear you all but I am very surprised when you all raise the name of God for for your hate, bigotry, intolerance, discrimination….for other human being like yourselves. Gays and lesbians are the same as you people, they respect the law of the country where they belong, they love people for who they are irrespective of their color, nationality religion and sexual orientation, unlike your guys full of hatred.
Synonim says
“….Gays and lesbians are the same as you people, they respect the law of the country where they belong, they love people ……”
What you haven’t tell is these gays/Lesbis are morally sick and they disrespect the values of societies; simply trying to cut the underlying social wiring which generations are tied together as a human community. What does your stupid mind tell you about this! You are the messenger of Lucifer….go to hell!
Which one is right? says
Aradaw…..first of all you have to understand what does it mean arada? your context for the meaning of arada is absolutly wrong! arada is the one who is genius in school, who believes in working hard, who spend his life in a productive manners. Specially who has a fear of God! and accepts who he is ! But you don’t have all of this so you are not Arada at all !!! “ሰብአዊ መብት” ማለት ሰው የመሆን መብት ማለት ነው ይሄም ማለት የሰውን ልጅ እንደሰውነቱና እንደ ማኅበራዊ ፍጡርነቱ ከሌሎቹ ፍጡራን የሚለየውንና የሚያልቀውን ኅሊናውን ለጸጸትና ለጉዳት የማይዳርጉ ተስማሚ አስተሳሰቡንና የጋራ ጥቅሙን ማለትም ማኅበራዊነቱን ጠብቆ ለማኖር ያስችለኛል ብሎ በጋራ ስምምነት የቀረጻቸውን ባሕል፣ ወግ፣ የግብረ-ገብ(የሞራል) ድንጋጌዎችን፣ ሃይማኖት ወዘተ. መጠበቅ መንከባከብ ማክበር ማለት እንጅ የአዕምሮ ጤና ዕክል ያለባቸው ሰዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጤናማ ኅሊና የሚጸየፈውን የሚቀፈውን ሥነ-ልቡናን የሚጎዳውን ከሰውነት አንጻር ተቃርኖ ያለውን የተለየ ሐሳብና ድርጊት ያለ ሀፍረት በድፍረት የትም ቦታ በነጻነት መፈጸምና አፈንጋጭ ድርጊት ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ የጋራ መተዳደሪያ ደገኛ ሥርዓት ማዕዘናቱን ለድርድር ማቅረብና አለማቅረብ፣ ለመጠበቅ ለማክበር የመፈለግንና ያለመፈለግን ጉዳይ የሰዎችን የአዕምሮ ጤና ደረጃና ደኅንነት መለኪያ መመዘኛውም ናቸው፡፡ አቤት! ደኅና የመሰለ ነገር ግን ያበደ የኅብረተሰብ ክፍል አለ ማለት ነው ጃል? አዬ ስምንተኛው ሽህ፡፡
aradaw says
I agree with some of the meaning of Arada you mentioned and you can also include “someone who shares what he has and very kind. Above all Arads are very strong in things they believe. I believe in humanity and equality to all human. I do not hate someone because of his color, gender, nationality sexual orientation whether he is gay, lesbian heterosexual. I do not care what a gay person does in his bed room as the same as a straight person does with a women, that is their personal affair.
Arada means love, kindness, tolerance, sharing what ever small. Come to Piassa and Seratgna Sefer and have a taste of Arada.
Amsalu Gebrekidan says
O’w it is so amazing any way I really appreciate your transparency. But I have questions to you and to the people your sorts. There were the answers for your all questions in the article you wouldn’t need to ask me.
-You considered me like a man in 16th century . what is 21st century man look like? Do you think a modernity or civilization means being a Gay? What kind of mind you have?
-You advise me to accept differences and become tolerant and compassionate to fellow human beings. I can’t believe you read the article attentively. Who is the one never feel compassion to fellow human beings?
– You mentioned the words human,moral. What is your understanding about humanity and moral values? I defined them precisely in the article how you couldn’t understand that. If you have a different understanding about it what does it mean? But be careful your answer shouldn’t be subjective and attention I said human not animal or beast. Human is the precious creature please don’t think it is under animal and beast.
– What do you think our’s (human’s) value it makes us different from animals and beasts. By the way do you know animals and beasts are better than you (homosexuals)? Because they know appropriately how, when and with whom they should do sex. So how could you think homosexuality is natural?
– You tried to be considered as you are concerned about our country’s problems. If it is your real attitude how you advise us to accept homosexuality(the core of the problems) I don’t think you have a normal mind you haven’t a moral right and you never feel about citizens responsibility and duty to keep and care about your country and compatriots.
– In general I feel so sorry because of your interests is different? Those all things you have mentioned are what the Gays are saying too. Tell me the truth are you a Gay? Don’t think you have a religion (faith) the religion (faith) which accept homosexuality is not a religion at all. To tell the truth there is no religions (faith) but there is one religion (faith) “One lord, one faith, one baptism,” Eph.4:5 this the only one faith (religion) bible condemn that impure act severely. so as you have not a respect and concern for moral values you also haven’t a religion and its values. So you already lost your own humanity values. Please let your mind un lock and read the article attentively and teach your self. forget about the mentality you have it is so dangerous it will perish you if you let it live with you any longer. may God help you brother Aradaw.
Kidist says
16th century was better@aradaw…yehe yegeleseb mebt aydelem…if u love n care 4 ur friends n families hu u said r gay, help them b4 they burn in hell
aradaw says
Dear Kidest.
This is the same thing one of my uncles told me when I was 10 years old. I ate biscut on Friday and he told me that I will go to hell because of eating biscut. When I was 19 years old my Aunt told I will go to hell because I ate “Mortedela” (asama sega). People have some sense, it is hatred, disrespect, bigotry that sends you to hell.
Worku Temtmie says
እቶ እምሳሉ በጣም እመሰግንሃለው ጥሩ አያረክ ነዉ።አኛ ኢትዮጵያኖች ባሕል እና ታሪክ ያለን ሕዝቦች ነን በተለይ ክርስቲያኑና እስላሙ ፈጣሪውን የሚፈራ ህዝብ ነዉ።ስለዚህ ይሄድርጊት ከሰው ሳይሆን ከሴጣን ስለሆነ ግብረሶደማዊነት ሁሉም ህዝብ ሊያወግዘዉ ይገባል ::
Kaleb says
@Aradaw:
Allow me to lay out a slightly different approach … but you’ve got to promise to your self to listen and analyse other’s people opinion- Being confrontational to a very sensitive subject in Ethiopia won’t get you anywhere.
>>> You keep referring to other’s ideas as – hatred , bigotry and disrespect.: This is because you’re thinking that people are opposing your sexual orientation – NO! you are wrong! People are not so much worried about what you do in your bedroom , it’s the aftereffect of that practice that irritates many…. People are protecting their humanity ! protecting what defines them as a family , society , country and citizens of the world. A gay man or woman chose NOT to have a biological family. Call it nature, orientation, companionship, bias or whatever you’d like to call; gay people denied themselves a chance to have a family. It’s sociology 101.. family is the basic building block of society. You can’t talk about the societies rules and laws while you are working against to it to deny it’s existence.
>>> Deviation happens in the natural world we all dwell in. Am sure you’ve seen a six fingered person, or Kitten with 23 toes…or men with feminine tendency and impotent to be real men or vice-verse. Don’t give me that crap about ‘ a man that had lived with his wife for 10 years and have two kids.. is now saying …. he’s been dating another man outside his marriage -because he feels jailed inside this body….bla bla bla … those people are simply – perverts, who like to experiment infidelity with their God given blessings.
The real question here should be: As a society , shall we inculcate, promote and cultivate a deviated nature and parasitic practice that will out grow and consume the host? OR acknowledge that this is a part of nature that needs to get a cure and seek help?
The answer to me is a NO brain-er. Gay people need to get help and seek cure rather than claiming straight people rights in the name of tolerance and equality! It just the way it is . and It is just the way it’s gonna be …just like in the picture in the story it takes a man and woman to have a child that will replace them in this world.
Ref: A 6th grade science book : Opposites attract – Likes repel ! How easier can this be?
kebele says
Aradaw, Some people try to put themselves as human right champions and very human. This is ridiculous pathetic. Lesbian, gay, bisexual transgender, (LGBT) very cosy name. Now they got this fancy name and they call it LGBT, .. this Ethiopian nigro from Diaspora act like he is very human and doesn’t like peoples to be discriminated because of their sexual orientation. He must be the one who bend in every corner of the street. Listen we Ethiopians have value and we stand for family value, we know what is wrong and what is right, no one dictate our culture tradition and belief system, you keep your dead brain where u are. No room for abnormality in Ethiopia.
aradaw says
I absolutely agree we Ethiopians have values and these values are not static, it evolves and changes. We use to discriminate people who look different have different hair or nose and color,. you do not deny, we even used discriminated people with different profession (azmari, ketkach…) but theses are some how behind us. Education changed our values we became smarter and loving. Look the above posting “this Ethiopian nigro from Diaspora” this is absolutely not Ethiopian value, these are the bigotry that we have to fight. What type of value is this read from above “ከመታደግ አኳያ በሕጉ የተጣለባቸው ፍርድ እንደገና ተከልሶ ከእሥራቱ በተጨማሪ እንዲኮላሹ ማድረግ ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን መገንዘብና እንዲስተካከል ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ Castrating some one is Ethiopian value ?
“Love your enemies” Ethiopian value and humanistic value also.
Mimi says
of course dear there is no doubt this is Wrong!!!!!!Wrong!!!!!!!!!!Wrong!!!!!! why we even discuses this please use your conmen sense and do not agree of this satanic staff under no surcumstancss we talk as normal as it is, we all know it is not come on!!!!!! we are not like this we are not it is so brain washed, if it is some kind of disease please lets help each other you will be cured believe me it is an illness we don’t hate you we love to help you, please admitted it is not normal please ask help, Artist Amsalu will be agreed with me we can help our nation from this kind of killer poisoning idea of others shall we am sure you will be happy to help. but I respect and love you for notice some thing as early as this I taught we are better than this, I feel so sad down I can’t believe this yes we have a lot of good and bad things but not this.
aradaw says
have you ever met a gay or lesbian person. have ever talked and tried to know why they do what they do. Are they really sick ? do they have strong feeling for the same sex as opposite sex do. There is no simple answer as you mentioned above “satanic staff” If it was satanic, we do what we used to do release them from their satanic possession with holy water. It is not also brain washed. If it is it would be reinstated. It is a normal life for those who are engaged. They love each other and who are we to judge them. Leave them alone. Let God give you the strength to accept and love.
selamta says
Since Mr. Amsalu’s writing is projected from a moral value perspective, I would like to ask him the following questions:
1. What is the role of a Christian in a community where the laws of God are clearly violated per our judgment? This includes theft, homicide, prostitution, bribery, rape, etc.?
2. I agree, same sex relationship is sinful. Since you already reached a verdict, I want to know from you how other sins such as adultery, protistiution and rape should be punished.
2. Who is a sinner and what is the worst sin in the eye of God?
3. Abrham was there when God counted down on the demise of Sodom & Gomorrah. In fact, he was begging God to forgive the people. Do you think Abrham sinned by trying to save Sodom & Gomorrah?
4. Mary Magdalene was a protistute condemned by her community until Jesus forgave her sins and put her on his side. Who was wrong, the community or Jesus?
Thanks,
selamta says
In the 70s young people were condemned for wearing flared jeans, big collars and platform shoes. They were often labeled as agent of Jolly jackism. Following this, a dress code was introduced in many public schools. Later followed socialism with its harsh crititisim and heavy hand on ‘imperialism.’ Anyone supporting or associated with USA and Britain was considered enemy of Ethiopia. Their produces were banned from domestic markets. The west was also blamed for our povery, prostitution, diseases, such as AIDS. Now a conspiracy is sought behind the spread of same sex relationships.
When are we going to take the responsibility for our destiny?
What also the author failed to understand is that there is no static culture any where in the world. Things evolve, change and disappear irrespective of geographical locations. Japanese do face work to look like Caucasian ‘ferenji’ as my little neighbor,’Zenebech’ wanted it. We used to prefer Italian shirts when its equivalent Ethiopian Augusta was 1/10th of the price. The West produces and sells stuff as long as there are people out there who buy them: weapons, cigarette, porno, fertiluzers, plant gene, you name it. Musema does the samething in his little kiosk in Addis. He sells condoms for everyone, not only for married couples. I don’t blame him, people should take responsibility, they are in charge of their lives. Committing sucide is a sin, but who in the world can stop it if the person doesn’t want to live. Mr Amsalu claims to have God’s sword in his hands and drumbeats to punish gays and lesbians, ignoring all other social ills.
aradaw says
The author not only failed by his static view of culture but completely failed to understand his own country culture. The culture he mentioned is the northern Ethiopian orthodox culture, ignoring the rest of the country. He wants to dress the country with his “Tibuko” view of culture that is too tight and too old to fit. One size fit all view. The author also failed to understand the meaning of “Human Right. here is what he says about human right ” “ሰብአዊ መብት” ማለት ሰው የመሆን መብት ማለት ነው ይሄም ማለት የሰውን ልጅ እንደሰውነቱና እንደ ማኅበራዊ ፍጡርነቱ ከሌሎቹ ፍጡራን የሚለየውንና የሚያልቀውን ኅሊናውን ለጸጸትና ለጉዳት የማይዳርጉ ተስማሚ አስተሳሰቡንና የጋራ ጥቅሙን ማለትም ማኅበራዊነቱን ጠብቆ ለማኖር ያስችለኛል ብሎ በጋራ ስምምነት የቀረጻቸውን ባሕል፣ ወግ፣ የግብረ-ገብ(የሞራል) ድንጋጌዎችን፣ ሃይማኖት ወዘተ. መጠበቅ መንከባከብ ማክበር ማለት እንጅ የአዕምሮ ጤና ዕክል ያለባቸው ሰዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጤናማ ኅሊና የሚጸየፈውን የሚቀፈውን ሥነ-ልቡናን የሚጎዳውን ከሰውነት አንጻር ተቃርኖ ያለውን የተለየ ሐሳብና ድርጊት ያለ ሀፍረት በድፍረት የትም ቦታ በነጻነት መፈጸምና አፈንጋጭ ድርጊት ማለት አይደለም፡” this is very wide and misleading. This is the same as “Terrorism Law of TPLF” too wide in meaning and too helpful to use for their advantage. It is the same for the author to condemn anything he does not like. Human Right simply means equal right without prejudice, discrimination harassment. Free from violence, from torture such as from Mr. Amsalu’s “እነዚህ ግብረሰዶማዊያን የሚያደርሱትን ጥቃት ከመግታት ወይም ከመቆጣጠርና ምስኪን ሰለባዎችንም ከመታደግ አኳያ በሕጉ የተጣለባቸው ፍርድ እንደገና ተከልሶ ከእሥራቱ በተጨማሪ እንዲኮላሹ ማድረግ ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን መገንዘብና እንዲስተካከል ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡” Free from degrading treatment, freedom of expression and association.
Gojam says
Selamta, i have to give you props for a very insightful and on point comment. The funny (atleast from the writers perspective) thing is there are hard core opponents of LGBT rights in USA & Europe. People in Europe and USA have morals & values that are very much in common with the majority of conservative Ethiopians. But self-entitled members of the society (eg. this article writer) in Ethiopia, have a very radical, extremist positions not based on fact or science rather mere speculation, conspiracy and fear. Interestingly, the vast majority of Ethiopians have same thought process like this writer. But not for so long because the world is heading to a globalized more homogeneous culture. The majority of we Ethiopian people grew up in a system where we didn’t exercise our human rights in full, grew up in fear of family, government and religious institutions, grew up without knowing our rights and responsibilities. This is why we failed to sprint forward fast enough, that we still talk about food security and basic human rights when the rest of the world on a different zone. And another thing i have to break it to majority of Ethiopians; Ethiopia is not famous; Ethiopia is a world super power; Majority Foreigners (Indian including) only know Ethiopia for Hunger and Hunger. If you truly think you are a GREAT Ethiopian, do something meaningful to yourself then change the lives of your brothers and sisters. Betty have sex; gay people are a lot; muslims problem…; those are not issues to millions of Ethiopia rather it is clean water, sanitation and basic food. Do something apart from preaching and talking!!
Synonim says
Hey Selamta, I bet you! you are not a Lesbi, you are the “wo”-man in the satanic gay community.
Synonim says
Why do you care about Selamta? Are you gay for yourself? Do you find people with same sex like you attractive? If so, it is ok. Relax.
Berhanu says
Ato Amsalu, can you please publish the paper about female genital circumcision ? The west use the term FGM – ‘female genital mutilation’. There is a big different b/n circumcision and mutulation.
Regarding this gay disease , I wish goolgule team could re-investigate again the crime that was committed to young kids in Jari, Wolo by NGO run by Terre Des Hommes.
http://search.snapdo.com/?st=ds&q=Jill+Campbell+and+her+husband+Gary+gathered+evidence+which+helped+to+convict+a+British+sex+offender
desta says
ato aradaw betelevision yemibalewn eyesema it is their rt yalkew neche lememsele kalehone besteker yetena aymeselem homosexuality yenechoche besheta newe wedegnam agere yegebaw b NGO bekule newe yehe wanawe yemiasasebene yehuman right aydelem mebete selehone erakutene athedem komowe eyekeru zerachen yanesew albeka belo demo bezi metachu wei tegerem enante gudachu bezu newe yehene ezebe besentu divert tadergutalachu drama FM ahun ma yemute homosexuality lek newe setele nechochun memsele newe yethiopia chegere yehe newe ?
desta says
ato aradaw betelevision yemibalewn eyesema it is their rt yalkew neche lememsele kalehone besteker yetena aymeselem homosexuality yenechoche besheta new
e wedegnam agere yegebaw b NGO bekule newe yehe wanawe yemiasasebene yehuman right aydelem mebete selehone erakutene athedem komowe eyekeru zerachen yanesew albeka belo demo bezi metachu wei tegerem enante gudachu bezu newe yehene ezebe besentu divert tadergutalachu drama FM ahun ma yemute homosexuality lek newe setele nechochun memsele newe yethiopia chegere yehe newe ?
aradaw says
Desta
Where do you get this crazy idea that it is a disease. Brother, it is not a disease. It is a sexual attraction to member of the same sex. You might like Asefash a gay person might like the same way Asefa as you like Asefash. There were thousands of studies done in different countries what cause some one to like the same sex rather than opposite sex and up to date there is no conclusive evidence to show the factor or the factors. Who are you to judge and why do you care for what two consenting adult do in their bed room. Take your time for something else. There are so many bad things around you that you can help. Prostitution is the worst problem in Ethiopia. Why not that be health issue and problem. Alcoholism worst problem. The worst problem of all is corruption (Gubo) from top to bottom. These are societies problems which you need to talk. I can mention a lot, this is enough for the day.
ambelu birhanu says
i think be mindful, God create man&woman how do you get this nonsense idea, don’t be mature, not yet!
Amsalu Gebrekidan says
_ OK Aradaw I gave you a reply , but you couldn’t say anything .
_ Mimi yes I agree with you
_ Ato Berhanu I have three books prepared to publish . this issue what you have asked me to publish is included in the 2nd book . wait for me if it is God’s will and if I get the sponsor it will publish .
_ Ato Selamta you have asked me questions. they are not only questions but they have also answers for your questions . for your no. 1 question question no. 3 and no. 4 have answers . the no. 2 and no.2 questions (because you wrote two times the no. 2) they can answer only by the Judge God .
I got some interesting sayings in your comment << what also the Author failed to understand is that there is no static culture any where in the world >> are you sure ? off course there are so many cultures , thoughts , norms , moral values etc. shared or evolved from one society to the other . but there is also so many static strange and too odd cultures , thoughts , norms, practices , customs , habits ,etc. in many society any where in the world specially in the minor Ethnic groups . you need to know that OK .
I think you believe homosexuality is some society’s culture and some others evolved it from them . some people didn’t agree with that . they are saying there is no society in the world who have had bad practices or habits like homosexuality as a culture . I have a question for them who have that like mentality . how do you define and understand a culture ? don’t you think homosexuality was a culture of Sodom and Gomorrah ? if we agree with that don’t you think there is a society around the world like Sodom and Gomorrah ? anything if it is accepted and practiced by the any society that is already the culture of that society . not necessarily it would be time honored . because every thing has a time it started . hence there is a society any where in the world who have had a bad culture , norm , practice etc.
aradaw says
I do not think I said there are no static cultures, (if I said I am sorry). What I said or intend to say is culture or cultures is or are not statics, it evolves and changes. Culture is not a ” tight Tibuko” for ever. Tibuko outgrows and get old, torn and no longer useful. Culture is the same way not static but evolving. If culture was static, we would have been in the stone age era. Dear Yeneta Amsalu, you want things to the same . I read your piece on Bety Abera and found your cruelty for this young lady who has done nothing to hurt no one. It is those so called vanguard of cultures who want to control every aspect of individual human being life for the sake sake of imperial nostalgia. they want the old to be back. In the new piece Yeneta Amsalu wote about the church, he has no shame asking the “Siso” the one third his church used to get from poor farmers to be reinstated. His Tibuko cultural view also extends in his new piece to his tibuko church view.
ambelu birhanu says
we fight for next generation, don’t be quiet
ambelu birhanu says
prayer is the key to fight this devilish custom, and discipline our children is another parental responssibility