• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ላይ የጣለችው እገዳ እና አንድምታው . . .

July 22, 2013 01:51 am by Editor 3 Comments

በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . .  አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና አነታራኪ ንግግር ነው። ሁለተኛው ሳውዲ ነዋሪውን የሃገሬ ሰው ግራ ያስደነገጠ ያስደሰተው ሲሆን ጉዳዩም  የሳውዲ መንግስት የቤት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ እንዳይመጡ ጊዜያዊ እገዳ የጣለበት ጉዳይ ነው! ሁለቱንም ሰሞነኛ ጉዳዮች መነጋገሪያ ሆነው ሰንበተዋልና መረጥኳቸው ! ያም ቢሆንም የማተኩረው ባንዱ ርዕስ ላይ ብቻ ይሆናል ! እናም የዛሬ ወግ ትኩረቴን በአያሌው ስለሳበውና ሚዛንም ወደደፋብኝ የሳውዲ እገዳ ጉዳይ ላቅና.  . .

የእገዳው ሰበብ …

lemis
ሟች ታዳጊዋ ሳውዲ ለሚስ

በያዝነው ወር ብቻ ሁለት ህጻናት በሳውዲ ዋና ከተማ ውስጥ በኢትዮጵያውያን  የቤት ሰራተኞች የመገደላቸውን ዜና ተከትሎ የሳውዲ መንግስት ከኢትዮጵያ የቤት ሰራተኛ ማስመጣቱን የማስቆም ፍላጎት እንደለ ጭምጭምታ የሰማሁን ከሁለት ቀናት በፊት ቢሆንም የመታገዱን እርግጠኛነት የሰማሁት ግን ባሳለፍነው ሮበ አመሻሹ ላይ ነበር።  ይህንን ለማረጋገጥ  ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ደጋግሜ ብደውልም ሃላፊው ስልካቸውን አያነሰሱም። ውሎ አደረና የደረሰኝ የጓሮው ሁነኛ ምንጭ እውነት ሆኖ ትናንት ሃሙስ ማለዳ  እገዳው በይፋ ታወቀ! በተደበላለቀ ስሜት ተናጥኩ ፣ ሌላው ሁሉ ቢቀር የብዙውን ድሃ ወገን በልቶ የማደር ህልም እውን ማድግ የሚቻለበት መልካሙን እድል መጠቀም አለመቻላችን በቁጭት አደበነኝ። በሌላ ጎኑ በቤት ሰራተኞች ዙሪያ መንግስት ትኩረት ባለመስጠቱ በኮንተራት ሰራተኛ ስምህጋዊ  የሳውዲ እና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት አለመኖርን፣ በዜጎች መብት ጥበቃ የተሟላ ስራ በመንግስታችን በኩል ያለመፈጸሙ ህጸጽ እና የምሰማው፣የማየው የወገን ስቃይና በደል አውጥቸ አውርጀ “በእገዳውን ቢያንስ እረፍት ይገኛል!” ስል የእፎይታ ደስታ ተሰማኝ! መረጃ ለማቀበል ካለኝ ፍላጎት አንጻር በእገዳው አንድምታ ዙሪያ ገብ መረጃዎችን ለመሰባሰብ በጾምና በጸሎት ለፈጣሪው በሚገዛው ነዋሪ መካከል በተረጋጋግቸ መረጃ ስብሰባየን   ገፋሁበት! ራስ ሰንጠቆ ከሚገባው ከጅዳ የበጋ ሙቀት ጋር የቀይ ባህር ወበቅ ከጭንቀትን የማይሸሸውን የስደተኛ ነፍስ ይፈትናል።

ሟች ታዳጊዋ ሶሪያዊት ኢስራ
ሟች ታዳጊዋ ሶሪያዊት ኢስራ

ስለ ሳውዲ መንግስት እገዳ መረጃ መሰብሰቡ ባያደክመኝም አንዱን አንዱን ስል የተኛሁት ሊነጋጋ ቢሆንም በማለዳው ከአልጋየ ሳልወርድ በማቀርበው ወግ ዙሪያ ማብሰልሰል ይዣለሁ.  . . ሁሌም እንደማደርገው የማለዳ ወጌን ከመጀመሬ እና የወጌን ሁነኛ ርዕስ ከመምረጤ አስቀድሞ የመረጃ ግብአት ይሆኑኝ ዘንድ ቅኝቴን የጀመርኩት እለታዊ ጋዜጦችን በመዳሰስ ነበር። የአረቡ አለም ዋና ዋና የሚባሉትን መገናኛ ብዙሃን ድህረ ገጾ እጎበኛቸዋለሁ። የመካከለኛ ምስራቅን ፖለቲካው አድፍጣ የምትዘውረው ሃገር የሳውዲ አረቢያ ጋዜጦች ከቅርብ አመታት ወዲህ ማናቸውንም አይንት ጽንፈኝነት ከመቃዎም ጀመሮ ድሮ ድሮ ሊነኩ ቀርቶ ሊወሱ አዳጋ ያስከትላሉ በሚባሉ የመንግስት ተቋማት ይተቻሉ፣ መገናኛ ብዙሃኑ ከዚህ አልፈው ሄደው ከመንግስት እኩል ባይባልም ከፍ ያለ ቦታ ያላቸው የሃይማኖቱ ተቋማት አሰራርና በአካሔዱ ላይ ነጻ አስተያየት ጥቆማዎችን ያቀርባሉ። ከመንግስት ተቋማትን ዝርክርክነት እስከ አካባቢ አረብ ሃገራትን የፖለቲካ አሰላለፍ ዘልቀው የሚተቹ የፖለቲከኞች ትንታኔ ጽሁፎችን በግልጽ ያወጣሉ። በዚህ ረገድ የሚቀርቡ መረጃዎችን በቅርብ ለተመለከተ መረጃዎቹ በሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አመራር ስር በሚተዳደር ሃገር ስር የወጡ ናቸው ብሎ  እስከመጠራጠር ሊያደርስዎ ይችል ይሆናል። ይህም አካሔድም የሳውዲ መንግስት የተለያዩ ምክንያቶች ደርድሮ ነጻ መገናኛ ብዙሃንን  አስሮም ቢሆን እንደመልቀቅ የሚያደርግበትን አካሄድ መኖሩን ማስተዋል ይቻላል ! እናም ይብዛም ይነስ መረጃዎችን ትንፋሸን ዋጥ አድርጌም ቢሆን ማንበቡን ለምጀዋለሁ ! እናም በጀመርኩት ርዕስ ዙሪያ የምፈልጋቸውን መረጃዎች ስብሰባ ቅኝቴን አገባድጀ ወደ   እኔው የማለዳ ወግ ሙንጨራ ገባሁ! እርግጥ ነው በሳውዲዋና ከተማ ሪያድ ካሳለፍነው ወር ወዲህ ለሚስ የተባለች የ6 አመት ሳውዲ ህጻንንና ሌላ ኢስራ የተባለች የ11 አመት ሶርያዊት ታዳጊ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀል በየትኛውም ሚዛን መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው።  በኢትዮጵያውያን ተገደሉ መባሉ ድግሞ ያሳዝናል ፣ ያሳፍራል! ይህንንም ተከትሎ ሳዊዲ ጊዜያዊ እገዳ አድርጋለች ። የሳውዲ መንግስት ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኛ ቅጥር በጊዜያዊነት ማስቆሙን በሚመለከት በሃሙስ ምሽቱ የጀርመን ራዲዮ ዜና መጽሄት ላይ ከጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ጋር ያደረግኩትን ቃለ ምልልስ ሰምቸ ጨረስኩ። ወዲያውኑ በራዲዮ መረጃው የደረሳቸው በርካታ ወዳጆቸ በስልክ ፣በፊስ ቡክ ገጼና በጓሮ መልዕክት መላኪያ ሳጥን በርካታ አስተያየቶችን ልከውልኛል።

የእገዳው ድጋፍ ፣ ተቃውሞ እና ሰሚ ያጣው ጩኸት ኑሮ. . . .

ከደረሱኝ አስተያየቶች መካከል “እገዳውን እንደግፋለን! ” ያሉኝ አብዛኛው ኢትዮጵያውያን “ያለ ህጋዊ የስራ ኮንትራት መጥተው ግፍና በደል ሲፈጸምባቸው የሚደርስላቸው የመንግስታቸው አካል አለ ማለት አይቻለም።  “ያሉኝ አስተያየት ሰጭዎች ስለደገፉበት ምክንያት ባስረዳት ሲቀጥሉ “አቅም አዳም ያልደረሱ ታዳጊ እህቶቻችን ሳይቀሩ በደላላ ተግዘው እየመጡ ከሚደርስባቸው ግፍ አንጻር ባይመጡ ይሻላል !” በሚልየሳውዲ መንግስተ  የጣለውን  እገዳ እንደሚደግፉ ገልጸውልኛል። በኮንትራት ሰራተኞች ቅጥርና ዝውውር ዙሪያ ያለውን መጠነ ሰፊ ችግር የሚገልጹ  አስተያየት የሰጡኝ ወገኖች መንግስት ሌላው ቢቀር  ዜጎቹን ከድህነት ማላቀቅ ባይችል በአረብ ሃገራት የተገኘውን የስራ እድል ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ አልቻለም ሲሉ ቅሬታቸውን በመግልጽ “በመታገዱ የምንሰማው የመከራ ጩኸት እስኪ ይብረድልን! “በማለት ወቀሳቸውን በመብት ማሰከበሩ “አልሰራም! !” ባሉት መንግስት ላይ አነጣጥረው መታገዱ ጥሩ ሆኗል የሚል አስተያየት የሰጡኝ በርካታ ናቸው ። በመታገዱ የተከፉትም ሃሳባቸውን ገልጸውልኛል።

መንግስት ስራውን ባለመስራቱ ለችግሩ ሁሉ ምክንያት ነው በማለት መንግስትን የሚወቅሱት አስተያየት አቅራቢዎች  ኮንተራት ስራ ብሎ እንቅስቃሴ ሲጀመር በሃገራት መካከል ሁለትዮሽ ስምምነት አለመደረጉ ትልቁ ስህተት መሆኑን ያስረዳሉ።  ከዚያም ቀጥሎ ስራው ሲጀመር ባልተቀናጀ በቂ ጥናት ፣ ያለ በቂ ቅድሚያ ዝግጅት ፣ ያለ በቂ ስልጠናና የመሳሰሉትን ዝግጅቶች አለማድረጉ በማመላከት ስህተቶቹ ለእገዳ ምክንያት መሆናቸውን በአጽንኦት ያስረዳሉ። “የሳውዲ ሰራተኛ ቅጥሩ እገዳ ይጎዳናል!” የሚለውን ሃሳብ የሚደግፉት እኒሁ ነዋሪዎች አጥፊው መንግስታችን ነው ሲሉ ደጋግመው ይወቅሳሉ። ተጠያቂዎቹ ከማዕከላዊ መንግስት ቸልተኝነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢንባሲና ቆንስል ሹሞች ይወርዳል በማለት ሲያስረግጡ ” መንግስት ለዜጎች የመጣውን እድል እንዲጠቀሙ ማድረግ አልቻለም!” ብለውኛል።  ወደዚህ መሰል መደምደሚያ ምን እንዳደረሳቸው ጠይቄያቸው ሲመልሱ  “መንግስት ዜጎችን የመደገፉ ሃላፊነት ተዘንግቶታል እንኳ ቢባል ከገቢ አንጻር ያልተመለከተበት አካሄድ አውጥቶ ላወረደው ግራ ያጋባል!” በመለት የመጣውን ወርቃማ እድል መንግስት እንዳልተጠቀመበት እና ይህም እንዳሳዘናቸው ገልጸውልኛል። እርግጥ ነው የሰራተኞች አቅርቦት ኮንትራት ሰም መንግስት የማመልከቻ ደብዳቤ ለማጻፍ ከሚያስከፍለው ጀምሮ ፖስፖርት በማደስ ፣ ቪዛ በማጽደቅ ፣ በውክልና ፣ በምስክርነትና በመሳሰሉት ከፍተኛ የሆነ በአመታዊ ሪፖርት ተለይቶ ባይነገረንም ከቆዳና ሌጦ ያላነሰ ገቢ አስገብቷል። ጥቅሙ ከመንግስትም ወርዶ  ከህጋዊ እስከ ህገ ወጥ ደላላ ከግለሰብ የሁሉንም ካዝናዎች ማጣበቡ እውንት ነው! ዜጎችም ቢሆን ብዙ መከራ እና ስቃይ እያዩም ቢሆን የተወሰነ በሚያገኙት ገቡ የደፈኑት የወላጅ ዘመድ አዝማድ የችግር ቀዳዳ መጠነ ሰፊ መሆኑን መካድ አይቻለም። በድህነት እየተጠበሰ ያለ ወላጅ በኑሮ ውድነት ኑሮው ይባስ ሲከፋበት ከፋ ህይወቱን በልጆቹ መስዋዕትነት ሊያልሳልፍ በእድሜ ያልበሰሉ ገና ያልጠነከሩ  ታዳጊ ልጆችን ከህገ ወጥ ደላሎች ቀቢጸ ተስፋ ተደልሎ ወደ አረብ ሃገር እየላከ ነው ። ከሁሉም የሚሳዝነው  ወላጅም ሆነ መንግስት ታዳጊዎች የሚላኩባቸው ሃገራት በሰራተኛ ሰብአዊ መብት ይዞታ በማይመሰገኑ ፣ ቤት ሰራተኛ አያያዝ የሚወገዙ የአረብ ሃገራት ያለ ህግና ስርአት መላካቸው ስለመሆኑ ብዙ ማለት ይቻላል።  በአደጋ በተከበበት መንገድ የሚገፋው በአረቡ አለም የቤት ሰራተኝነተ ህይዎት በተለያዩ ምክንያቶች ግፍ ተፈጽሞባቸው ስንኩል ሆነውና ሞተው በድናቸው ሃገር ሲገቡ ማየት ተለምዷል። የታደሉት ሬሳቸው የሚታወቅበት፣ ያልታደሉት ሬሳቸው ሳይቀር የማይታወቅበት አስከፊ  የአረብ ሃገሩ ስደት ለመሆኑ ወላጅና መንግስት ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው። ወላጅ ድህነት ችግሩ ብሶበትና በደላሎች ቀቢጸ ተስፋ ተታሎ በአብራኩ ክፋዮች ላይ ጨክኗል! መንግስት ችግሩ ትውልድን እያጠፋ ለመሆኑ በእማኝ እያየና እየሰማ ችግሩን ለመከታተልና ለማስቆም ብጣሽ ህግ ማውጣት ተስኖታል። ለተበዳዮች መብት ማስከበርም ሆነ ሲበደሉ ፍትህ መጠየቁን ትቶታል። የሁሉም ስደተኛ ሰራተኛ ህይወት ይህን ሁሉም ይህን ይመስላል አይባልም። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባል የአረቡ ስደት ተጠቂዎች መሆናቸው የሚታበል ሃቅ አይደለም። እስካሁን በዜጎች ላይ እየደረስ ያለው ግፍና መከራ ግን ለቀሪው ትምህር ሆነው ስደቱን ሊገድበው አልቻሉም።

የሳውዲ መንግስትን የሰራተኛ ማስገባት ጊዜያዊ እገዳ ጠልቀን ማየት ከሞከርን እርምጃውን ደገፍነም ተቃወምን ፣ አስደሰተንም አስከፋን አንድ እውንታ ድጋፍ ፣ ደስታ፣  ተቃውሞ ፣ መከፋቱን አንድ ያደርጋቸዋል!  በእገዳውን የመደሰትና የመደገፋችን ስሜት ምንጩ መንግስት ለዜጎች ተቆርቁሮ የመብት ጥበቃ አለማድረጉ ሲሆን  በአንጻሩ እገዳውን ያስከፋን መንግስት በድህነት አረንቋ ውስጥ ያሉ   ዜጎች በመጣውን እድል መታደግ ባለመቻሉ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል ባይ ነኝ ! በዚህም ጎን ለጎን በያዝነው ሳምንት አጋማሽ የወጣው የሳውዲ መንግስት ጊዜያዊ እገዳ መንግስታችን እያፈሰው ያለው ገቢ ጋብ ብሎ ኢኮኖሚውን ከማሽምድመድ ባይደርስም በዙሪያው ተጠቃሚ ለሆኑት ደላሎች ታላቅ መርዶ ነው! በባለጊዜዎች ከለላ ሲንቀሳቀሱ ለከበሩት የምስለኔዎቻችን ወዳጆችም እገዳው ዱብ እዳ ነው !

በአንጻሩ የፈልግው ይምጣ ብለው ሰርተው ለመለወጥ ቋምጠው ለመሰደድ በቋፍ ላይ ላሉት ዜጎች መልካም የምስራች አይደለም! መርዶ እንጅ! የሳውዲ በቅርቡ የሳተውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በወረፋ ላይ ላሉትም ቢሆን ዜናው መልካም አይደለም!  ገጽታችን እንገንባ እያሉ ገጻችን እያበላሹ ለዚህ ላበቁን ይብላኝላቸው እንጅ በሳውዲ ለከተምን እየተሰራ ያለው አንገታችን አስደፍቶናል ! በአረብ ባገሩ ስደት ህይወት የዜጎችን በደል ፣መከራና ሰቆቃ ከባለቤቶቹ ስቀበል ለባጀሁት ጎልማሳም ስሜቱ ከላይ የገለጽኩት አይነት የተቀላቀለ ነው! አገዳው ያስደስታልም! ያሳዝናል ፣ ያስቆጫልም! እየሆነ ያለው ደፍሞ ያሳፍራል! መንግስት ሆይ! በደል ፣ ጭንቀት ሃዘናችን ስማ! በጎ በጎውንም አስብልን!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Wado Gada says

    July 24, 2013 05:51 am at 5:51 am

    Wondime tiru tintana new yekerabkaw.sharafi adirge wodalafikaw agenda ley yebekulen tinish libel.yewondim juwar nigigir asafari bilehal endet new baki asafari yehonaw?beherun bagiltsi siltangare?ethiopiawinatin silaldagafe?awo juwar oromo new degmom muslim new nigigiru kayetignawum gar aygachim.oromo bazihagar lemato amat belay tegazito berasu hagar ley techokino yenore new mangist yebeher albekebilot belela be eminet lisanachinim mete,libibel lamisale ante islam woneh none oromo kewonki yeante gudat awun new astawul jawarina yene bitewochi hulete magodatachin new silazi huletum fith ayasfaligachewum tilaleh?ye muslimochin guday kemaleh muslim gar entagalalen yegariyosh bemehonu yebeherin guday egna erasachin enwotalen huletum legna andinachew so lazi hizibh tigilun min yanatatilewal?huletum yemeninat guday nechew ?tigilu legna “killing two birds with one stone”new le eminat metegal mamot,matasar nasri eskimete diras samayawhi awaj new,le oromonetm metegal yesawun salfalig bahagare mabten askabire ka chikona kenber erasen malekek fitawinat new .Lazih new tigilu yemimasasalew.Nagar gin tebeboch ye juwarin nigigir le politika fijotachaw “ethiopiwintin”silaldegafe yakorafut paparazi wula egnan leyayiton,kafafilon ye muslimun tigil leyakachichu yefaligalu”egn ye ethiopia muslimoch andi nen babiher binlayayim samayawi awaj astasasironal anlayayim ledinachin zab enkomalen”hulem islam fithin yeshal insha allah nasiru qirbi new!paparaziwochu zemen bikeyeyerim yemilewatu basalem yemayaminu aydelum zaragnoch ye abatochachin ideology andi hegar,andi haymanot,andi quanka,andi bandira yemilu “zionist” nechew!ye oromon negar ayhonachawum dagim ba lela chikun hizib na oromo hizihbi zandi bota yelechawum ba hiwot eyelen lela atse aymaranim we are apeople of 21 centurey.

    Reply
  2. tewodros says

    July 24, 2013 05:32 pm at 5:32 pm

    betam yasaznal eyehone yalew neger mngst lemn talka gebto cgrun endemayifeta ayigebagim
    betam kelal neger neber mn alebet dhochinna mskinochin bitadeg
    lemangawum egziabher yemibegewun lehulachinm yizezlen
    selam egziabher kehulachin gar yihun cher yigtemen.

    Reply
  3. selam says

    August 2, 2013 06:10 pm at 6:10 pm

    @ wado Gada endilemen gen tenesh enkua neqa atelum yeoromon hezeb eko lek end Amahrarwo hezeb regetewo yegezut yeneberut menegesetatoch enji oromo be ethiopiawinet ayedelem yeteregetew maleti hullum ethiopiawian yehonuten nawo yehonew yehenenem gezot lmegelagel ye ethiopia hezeboch beheberet tagelen gen wutitu be oromowoch , be tegerioch ,be ogadiniwoch zeregnenet tedenaqefe ena aradawoch yehn edel teteqemewo be aquarach negeru bemeqeyer yehew tegeriwoch ahun lalnebet cheger daregewunal so ye ethiopia cheger ye beher chegeru ye hayemqnot chegeru hullu yetefeterewo ke laye beteqesekuwachewo beheroch zeregnenet mekeneyat sihon ante endalekewo chegeru 1bandira 1 hager 1hezeb mebalu ayedelem!!!!!! Awo wondemi pls sefa aderegen enasebew mekneyqtum ato juhar le eni qeteregna ye woyani telalaki enji ewunet ye oromo lijoch teqorequari alemehonu enqm lek ye ante ayenet wondemochachenen bemesab le telekoachew mefetsem yehew eyeteteqemubachew naw so qom belena asebewo juhqr enedalewo iselam ke beher gar menum kemenum ga ayegnagnem zegochen lemadenager gen betam yeteqemal so manem belefelef quter teneseten anachebecheb mekeneyatum ye woyani aquam beheren ke beher hayemanoten ke haymanot bemagachet yeseletan zemenachewon marazem kalehonem egnan achefachefew zewor belewo tegerayen megenetel nawo pls yezih mesaria atehunu yegeremehal eni ethiopiawi ye Amehara beher tewolaj bihonem oromon gen ke rasi ekul yemewod zegam wonedemem negn enam islam oromowochgabicha sayehon hullum behereseboch wuset yegegnal endalekewo islamen woyenem cheresetena hayemanoten lemetebeq bezat ayedelem mefetehiw deg asabi enji so ebakachihu woyani egnan lemekefafel beteleyem wana telatoch aderego yeferejachew Oromo ena Amharawochun sihon endeye bizatachewom bizu yejuhar ayenet virusochen bemekakelachen bemasegebat ke hager hager ke hayemanotem hayemanot endayenoren lemadereg besefewo zemetewubenal so juhar yeoromo beher tewelaj bicha selehon leteketelew woyem letamenew ayegebam mekeneyatum ke eyanedandu beher Banda endal qom beleh aseb hayemanotachenen woyenem manenetachenen yemenasekeberew lik be juhar ayenet asemesay wondemochachen ayedelem ena neqa enebel.God Bless Ethiopia senel nawo hullum hayemanotoch ethiopia wust mekeber yemichelut. Amesegenalehu!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule