የመናገር፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ወዘተ መብቶች በሚከበሩባቸው አገራት በመጀመሪያ ደረጃ ፓርላማ የሚባል አካል ካላቸው ገዢው ፓርቲ የ99.6 በመቶ ወንበር አይዝም፤ በፓርላማው የተቀናቃኝ ፓርቲ አባልም አንድ ብቻ አይሆንም፡፡ ይህ ከሆነ ስብስቡ “ፓርላማ” ሳይሆን “የ… ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ” ነው የሚባለው፡፡ ከዚህ ሲያልፍ ረቂቅ ሕግጋትና ውሳኔዎች ሁሉ “በአክላሜሽን” ወይም በሙሉ ድምጽ ወይም “በእልልታ” አይደለም የሚጸድቁት፡፡ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላትም የአገርን ጉዳይ በተመለከተ “የሶስት ደቂቃ” የንግግር ገደብ አይጣልባቸውም፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በኔፓል ፓርላማ የደረሰው “የተከበሩ” የፓርላማ አባላት እንዲህም ያደርጋሉ እንዴ በማለት የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ማክሰኞ ምሽት የአገሪቱን የተሻሻለ አዲስ የሕገመንግሥት ረቂቅ ለማጽደቅ የተሰበሰቡት የፓርላማ አባላት በጉዳዩ ላይ … [Read more...] about በኔፓል ፓርላማ “አንቀጽ 39 በእልልታ” አይጸድቅም!
News
ዜና
የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት እጅግ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሲል ፓርቲው ጥር 15/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ አቶ ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው ነበር ያለው ፓርቲው በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ግልጾአል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አቶ ዘመነ አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ አረጋግጠናል ያለው መግለጫው የሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት … [Read more...] about የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት የፖሊስ ልብስ በለበሱ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው
“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”
የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀውን ዘገባ ማምሻው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?” በሚል ርዕስ ባተመው ዜና ላይ ዘገባው እንደሚወጣ በተናገረው መሠረት ባለ 76 ገጽ ሪፖርቱ በሚዲያ አፈና ዙሪያ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃዎችን አውጥቷል፡፡ ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ አፈና፣ ማስፈራሪያ፣ ህይወት የማጥፋት ዛቻ፣ … ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በትንሹ 22 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ፤ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ አገር ጥለው መኮብለላቸውን በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ እንዲህ ያለው ገለልተኛ ሚዲያን የሚያፍን እና ከሜዳው የሚያስወጣ አሠራር ከወራት በኋላ ይካሄዳል ከሚባለው “ምርጫ” አኳያ የውድድሩን ሜዳ … [Read more...] about “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም”
ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?
* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ! ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ … [Read more...] about ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?
“አእምሮዬ አልዳነም!”
“በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ቶርቸር (አካላዊ ስቃይ) የሚፈጸምባቸው ጩኸታቸው ይሰማኛል፡፡ የቃሊቲ ማጎሪያ ውስጥ የታሰሩ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ንጹሃን ዜጎች፣ ስቃይ አሁንም ከፊቴ አለ፤ የሚሞቱት ሰዎች ሊረሱኝ አይችሉም፤ የእስር ቤቱ ጠረንና ሽታ ይከተለኛል፤ በአካል ደህና ብመስልም አእምሮዬ ግን አሁን ድረስ ሰላም የለውም” በማለት የስዊድን ጋዜጠኛ ማርቲን ሺብዬ በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ተናገረ፡፡ አንድ ዓመት ከሁለት ወር (14 ወራት) ከሥራ ባልደረባው ዮሐን ፔርሶን ጋር ኢህአዴግ አስሮት የነበረው ጋዜጠኛ ሺብዬ ለጎልጉል የአውሮጳ ዘጋቢ ይህንን የተናገረው በዖጋዴን ክልል የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም መሰራጨቱን ተከትሎ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ “በአካል ሰላም አለኝ፤ አእምሮዬ ግን አልዳነም፤ … [Read more...] about “አእምሮዬ አልዳነም!”
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
• “ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር “በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ” ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ “የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል” ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ “ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ … [Read more...] about የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች!
ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጭት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን» እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል። ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር … [Read more...] about ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች!
ኢቦላ በቤላ?
• ከ10 በላይ ሰዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በፖሊስ ታግተዋል፤ እስከ 21 ቀን ቤታቸው ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ • “ይህ የአገር ሚስጥር በመሆኑ ለማንም እንዳትናገሩ” ሴራሊዮን ውስጥ በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ህይወቱ ያለፈውና በሽታው ኢቦላ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የደም ናሙናው ወደ ውጭ ለምርመራ የተላከው ኢትዮጵያዊ ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የአምቡላንስ ሰራተኛና ከእሱ ጋር ተገናኝተዋል የተባሉ ሌሎች 10 ያህል ሰዎች የሚኖሩበት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ የሚገኝ ግቢ በፖሊስ ተከቦ ነዋሪዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል፡፡ ኢሳያስ የተባለና ህይወቱ ያለፈውን ኢትዮጵያዊ በአምቡላንስ ሲያመላልስ የነበር ወጣት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን በተለምዶ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን እሱን ጨምሮ … [Read more...] about ኢቦላ በቤላ?
የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?
“የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንደደረሱ ቢያጠፉ ሆቴሉን ማትረፍ ይቻል ነበር” የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰ፡፡ “በተደወለልን በሁለት ደቂቃ ውስጥ ደርሰናል፤ (የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን) 113 ሠራተኞች በ12 ተሽከርካሪዎችና በአምስት አምቡላንሶች ታግዘው፣ 236,300 ሊትር ውኃና 500 ሊትር ፎም በመርጨት ቃጠሎውን መቆጣጠር (ችለዋል)” አቶ ሰለሞን መኰንን የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ፡፡ “በፍጹም በሁለት ደቂቃ አልደረሱም፤ በሁለት ደቂቃ ወይም በሌላ ማለቱን ትተው በደረሱበት ወቅት ማጥፋት ቢጀምሩ ኖሮ፣ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሕንፃ ሳይዛመት ጃዝ አምባ ላውንጅ ላይ እያለ ማጥፋት ይችሉ ነበር፡፡ ስልካቸው አልሠራ በማለቱ በመኪና እዚያው ድረስ ተሄዶ እንደተነገራቸውና ነጋሪው መጥቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደርሰዋል፡፡ እንደደረሱም … [Read more...] about የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?
ኢህአዴግ የምርጫው ስጋቱ አይሏል
* ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል የአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ የስልጠናው ዋና አላማ በቀጣዩ ምርጫ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራውን አመጽ መቆጣጠር እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ ምንጮች በተለይ ፖሊስና ፀጥታ ጉዳይ ከ“ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ” ጋር በመተባበር የደፈጣ ውጊያን ለመከላከል “የደፈጣ ውጊያ ስምሪት” በሚል አጭር ስልጠና እየወሰዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም … [Read more...] about ኢህአዴግ የምርጫው ስጋቱ አይሏል










