• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር?

January 21, 2015 01:51 am by Editor 3 Comments

* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ!

ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡

ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ በአሳታሚነት፣ በአከፋፋይነት፣ በአታሚነት፣ በሻጭነት (አዟሪነት)፣ ወዘተ የተሰማሩትን እንዴት ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደሚያዳክም፣ እንደሚያፍን፣ እንደሚያሰቃይና ባጠቃላይ ከሜዳው እንደሚያስወግድ የሚያስረዳ እንደሚሆን ጎልጉል ካገኘው መረጃ ለመገመት ተችሏል፡፡

በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በማያያዝ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ዘገባ በተለይ የኢህአዴግን ቋት የሚሞሉ ለጋሽ አገራት፣ ዓለምአቀፍ የፍትሕ አካላት፣ የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንዛቤ ይዘው ኢህአዴግ አደርገዋለሁ ለሚለው “ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ” ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተሳትፎ እንዴት ውጤት አልባ እንደሆነ የሚያስረዳና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

elec tionበዘንድሮው ምርጫ ባልተጠበቀና ለመቀበል በሚያስቸግር መልኩ የአውሮጳ ኅብረት “በጀት የለም” በሚል ምርጫውን አልታዘብምም ብሏል፡፡ በይፋ የተሰጠው ምክንያት ይህ ቢሆንም ጉዳዩ የበጀት ሳይሆን “ኢህአዴግ ከኢህአዴግ ጋር የሚያደርገውን የ99.6 በመቶ የምርጫ ውጤት መታዘብ በራሱ ያስታዝባል” በሚል ነው ኅብረቱ ምርጫ መታዘቡን በቅድሚያ ትዝብት የተወው በማለት የተሳለቁ መኖራቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በበኩሉ “ባትታዘቡ ምን ገደደኝ” በማለት ኅብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ አለመፈለጉን በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ትዝብት አልፎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ስለ ሚዲያ ነጻነት በሚያትተው አዲስ ዘገባና በኅብረቱ ውሳኔ ዙሪያ ኢህአዴግ “ዓለምአቀፋዊ ሽልማት ባገኙ የዘርፉ ባለሙያዎቹ” ተጠቅሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ባለ “ነጻነት” የሚዲያ ሥራ እንደሚሠሩ በነዚሁ “ሚዲያዎች” ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የአውሮጳ ኅብረትን “ምርጫ አልታዘብም” የማለት ውሳኔን በተመለከተ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ለጎልጉል እንደተናገሩት ኅብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከበጀት እጥረት ሳይሆን እየከረረና እየመረረ የመጣውን የኢህአዴግን አምባገነንነት፣ በቀደሙት “ምርጫዎች” የተከሰተውን ዓይንአውጣ ቅጥፈት እንዲሁም የኢህአዴግን የሞራል ዝቅጠት በማገናዘብና ከተሞክሮ በመነሳት የግንቦቱን ምርጫ አስቀድሞ በማጣጣል ዋጋ እንደማይሰጠው ከመናገር አኳያ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህንን አስደንጋጭ የአውሮጳ ኅብረት ማዕቀብ ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ ድርጅት በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ከምርጫው በፊት አስቀድሞ ማውጣቱ ታስቦና ታቅዶ የተደረገ ብቻ ሳይሆን የአውሮጳ ኅብረትን እነማን ይከተሉታል የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡

በግንቦት 2007 አካሂደዋለሁ ለሚለው ምርጫ ኢህአዴግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የውጭ ምንዛሬ ኮሮጆውን እንዲሞሉለት ከአውሮጳ ኅብረት በተጨማሪ ሌሎች አገራትን በተናጠል መለመኑ ይታወቃል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. እምሩ ዘለቀ says

    January 20, 2015 07:07 pm at 7:07 pm

    ምርጫ የሚባለው ቃል በኢትዮጵያ ዉሎም አያዉቅ፤ አምባገነን ወንበዴዎች የነገሡባት አገር ናት፤ እጅ አዙር የፈረንጆችና ሌሎች የሚገዟት አገር ሁናለች፤ በዚህ አኳሆን ከቀጠለች ህልዉናዋ በጣም ያጠርጥራል፤ ያለዉን ችግር እያወቅን፤ በግልጽ እየተነገርን፤ በግልጽ እየተሰደብን፤ በግልጽ እየተዋረድን፤ በግልጽ እየተገደልን፤
    አንሰማም አናይም አናዉቅም እያልን በራሳችን ላይ ፈረደን የወሬ ቋት ሁነናል፤
    ምርጫ ያሰፈልገናል ወይ፧

    Reply
    • Daniel G/ says

      January 21, 2015 11:12 pm at 11:12 pm

      Kemotnma koytoal

      Reply
  2. dokele says

    January 22, 2015 06:52 am at 6:52 am

    weneteme yewenbede merri

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule