“የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንደደረሱ ቢያጠፉ ሆቴሉን ማትረፍ ይቻል ነበር” የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰ፡፡
“በተደወለልን በሁለት ደቂቃ ውስጥ ደርሰናል፤ (የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን) 113 ሠራተኞች በ12 ተሽከርካሪዎችና በአምስት አምቡላንሶች ታግዘው፣ 236,300 ሊትር ውኃና 500 ሊትር ፎም በመርጨት ቃጠሎውን መቆጣጠር (ችለዋል)” አቶ ሰለሞን መኰንን የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ፡፡
“በፍጹም በሁለት ደቂቃ አልደረሱም፤ በሁለት ደቂቃ ወይም በሌላ ማለቱን ትተው በደረሱበት ወቅት ማጥፋት ቢጀምሩ ኖሮ፣ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሕንፃ ሳይዛመት ጃዝ አምባ ላውንጅ ላይ እያለ ማጥፋት ይችሉ ነበር፡፡ ስልካቸው አልሠራ በማለቱ በመኪና እዚያው ድረስ ተሄዶ እንደተነገራቸውና ነጋሪው መጥቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደርሰዋል፡፡ እንደደረሱም ይዘውት የመጡት የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪ ማጥፋት የሚችል ባለመሆኑ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሊዛመት ችሏል፤ ስለ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፍጥነትና መዘግየት በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ይናገሩ” ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰ፡፡ (ምንጭ፡ ሪፖርተር)
Leave a Reply