• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች!

January 17, 2015 07:55 am by Editor Leave a Comment

ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጭት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን» እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋሉ በእርስ በእርስ ግጨቱ የተሳታፊ 4 ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው ላይ ከደረሰው መለስተኛ ጉዳት አገግመው በአሁኑ ሰዓት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በኢትዮጵያውያኑ መሃከል በሚከስት ግጨት በደም የተጨማለቀ በጠራራ ፀሃይ በሳንጃ አንጀቱ የተዘረገፈ ሬሳ መንፉሃ ውስጥ ማየት የተለመደ መሆኑን የሚገልጹ የአይን እማኞች የዛሬ አመት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በቡድን ይከስት የነበረ የዕለት ተዕለት ዘግናኝ ትእይንት ለወራት ጋብ ብሎ ቢቆይም ሰሞኑንን በአዲስ መልክ በማገርሸቱ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ አስደንግጦል ብለዋል።

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን መሃክል በሚከስት ግጨት ህይወቱ የሚያልፈውን ወገን ለማታደግ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከአመት በፊት የጀመሩት ጥረት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድክመት መስተጓጎሉ የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች በአሁኑ ሰዓት ጭካኔ የተሞላበት የኢትዮጵያውያኑ የእርስ በእርስ ግጨት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንፉሃ በሚኖሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ ይነገራል።

ቀደም ብሎ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሚናገሩ ወገኖች መንፉሃ እንደወትሮው በኑሮ ውድነት ሃገራቸው ውስጥ መኖር ተስኗቸው መሄጃ ባጡ ኢትዮጵያውያን ዳግም መጨናነቋን ይናገራሉ።

እልባት ያላገኘው ይህ የኢትዮጵያኑ የብሄር ግጭት በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ግምት ወስጥ በማስገባት በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን ሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ በመደውል ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ባይሳካም አምባሳደር መሃመድ ሃሰን አፈጉባኤ አብዱላ ገመዳ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት ከመግባታቸው በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸውንና ኤምባሲው በጊዜያዊነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እየተመራ መሆኑን አንድ ስማቸውን መጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የኤምባሲው  ሰራተኛ ከስጡኝ መረጃ ማረጋጋጥ ፡ተችሏል።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi
ይህ ሰሞኑንን ሪያድ መንፉሃ እና አካባቢውን ሲያብጥ የከረመው ዘግናኝ የብሄር ግጭጥ ትዕይንት ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ።

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule