• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

January 20, 2015 12:50 am by Editor Leave a Comment

• “ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን”

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር “በነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ” ዘመቻው ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡ ትብብሩ ዛሬ ጥር 12/2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ “የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ አጋፋሪነት ሊቀጥል ይችላል” ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሆኖም የትግሉ አላማ ኢህአዴግን ማጋለጥ በመሆኑ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ትግሉን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ “ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ ጥሪ ስናደርግ የፖለቲካ ምህዳሩ ተስተካክሏል እያልን አይደለም፡፡ እኛ አሁንም እያነሳን ያለነው የትግል ጥያቄ ነው” ያሉት የትብብሩ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የትብብሩ የትግል አላማ ይህን የተዘጋ ምህዳር ማስከፈት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ትብብሩ “የትግሉ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆንከው መራጩ ህዝብ ነጻነትና ክብርህን ለማስመለስ በምናደርገው ትግል በንቃት እንድታሳተፍ፣ ዛሬውኑ በመመዝገብ የሥልጣን ባለቤትነትህን የምታረጋግጥበትንና ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት የምትቀጣበትን ትጥቅ “የምርጫ ካርድህ”ን በእጅህ እንድታስገባ” ሲል ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እንዲሻሻሉ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች የማይመለሱ ከሆነ እና ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን ብሏል፡፡

ምህዳሩ ተዘግቷል እያላችሁ ህዝቡ ምርጫ ካርድ እንዲያወጣ መጠየቅ አይጋጭም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት “ዜጎች ምርጫ ካርዱን ማውጣታቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ይጠቅማል፡፡ ኢህአዴግ አንድ ለአምስት እየጠረነፈ የምርጫ ካርድ በማስወጣቱ ህዝቡ ተስፋ ሊቆርጥ አይገባም፡፡ ትግሉ ሲጠናከርና ሂደቱ ሲቀርብም ኢህአዴግ እጠቀምበታለሁ ያለውን ሁሉ የማንጠቀምበት ምክንያት የለም፡፡ ለመምረጥም ሆነ ላለመምረጥ ምርጫ ካርድ ማውጣቱ አስፈላጊ ነው፡፡ የመጨረሻ ውሳኔው በሂደቱ የሚወሰን ይሆናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አቶ ግርማ በቀለ በበኩላቸው እስካሁን ትብብሩ ያደረገው ትግል ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ጎን የቆመበት መሆኑን ያረጋገጡበት እንደሆነ ገልጸው ሂደቱን ለመወሰን ህዝቡ ምርጫ ካርዱን አውጥቶ መጠባበቅ እንዳለበትና ምርጫ የመግባትና አለመግባት ጉዳይ ለመወሰን ጊዜው ገና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ከመግባትና ካለመግባት ባሻገር ትግሉን በማጠናከር ኢህአዴግ አንድም በግልጽ በመሳሪያ ብቻ እገዛለው እስኪል አሊያም በምርጫና በመሳሪያ መካከል ያለውን አታላይ መንገድ ትቶ ዴሞክራሲያዊ መንገድን እንዲመርጥ ማድረግ ትልቅ ድል ነው፣ ያሉት የትብብሩ ሊቀመንበር የትግሉ ዋና አላማ የኢህአዴግን አታላይነት ማጋለጥ ነው ብለዋል፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule