• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢቦላ በቤላ?

January 16, 2015 08:43 am by Editor Leave a Comment

• ከ10 በላይ ሰዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በፖሊስ ታግተዋል፤ እስከ 21 ቀን ቤታቸው ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ

• “ይህ የአገር ሚስጥር በመሆኑ ለማንም እንዳትናገሩ”

ሴራሊዮን ውስጥ በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ህይወቱ ያለፈውና በሽታው ኢቦላ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የደም ናሙናው ወደ ውጭ ለምርመራ የተላከው ኢትዮጵያዊ ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የአምቡላንስ ሰራተኛና ከእሱ ጋር ተገናኝተዋል የተባሉ ሌሎች 10 ያህል ሰዎች የሚኖሩበት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ የሚገኝ ግቢ በፖሊስ ተከቦ ነዋሪዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል፡፡

ኢሳያስ የተባለና ህይወቱ ያለፈውን ኢትዮጵያዊ በአምቡላንስ ሲያመላልስ የነበር ወጣት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን በተለምዶ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን እሱን ጨምሮ ከእሱ ጋር የሚኖሩት እህቱና ባለቤቱ እንዲሁም ተከራይቶ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ከ10 በላይ ሰዎች ከህዝብ እንዳይገናኙ በፖሊስ ታግተዋል፡፡ ግቢው በፖሊስ ተከቦ ሰው ከግቢው እንዳይወጣና ወደ ግቢው እንዳይገባ መከልከሉን ተከትሎ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ የሚኖረው ህዝብ በኢቦላ በሽታ ስጋት ተወጥሯል፡፡

የጤና ባለሙያዎችና ፖሊሶች ኢሳያስ የተባለው ግለሰብ ሟቹን በአምቡላንስ ሲያመላልስ እንደነበር ከትናንት ጠዋት ጀምረው ቢያረጋግጡም እስከ ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ከሰው ጋር እንዳይገናኝ ሳይከለክሉት ቆይተዋል ተብሏል፡፡ የአምቡላንስ ሾፌሩ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ ከ20 በላይ ሰዎች የሚኖሩ ቢሆንም 10 ያህሉ ግለሰቦች ብቻ ከግቢ እንዳይወጡ የተከለከሉት ዛሬ ጠዋት ነው ተብሏል፡፡ ሆኖም ከግቢው ውጭ ከኢሳያስ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ግለሰቦች ላይ ምንም አይነት ክትትል ያልተደረገ ሲሆን ግቢው ውስጥ ከሚኖሩት መካከልም በጠዋት በስራና በሌሎች ምክንያች የወጡ ግለሰቦችም ተመልሰው ወደ ግቢ እንዳይገቡ ከመከልከላቸው ውጭ ክትትል እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ታውቋል፡፡

የአምቡላንስ ሾፌሩና ከእሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉበት ግለሰቦች የሚኖሩበት ግቢ በርከት ባሉ ፖሊሶችና የደህንነት ሰራተኞች መከበቡን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰባስበው ስለ በሽታው እየተወያዩ አስተውለናል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም የአንቡላንስ ሾፌሩ ከበርካታ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበረው መሆኑ፣ እንዲሁም ግቢው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችም ከግቢ ውጭ የሚገኙ በመሆኑ በሽታው ከተከሰተ ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱም አስጊ እንደሆነ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በፖሊስና ደህንነት ከበባ ብቻ አንድ ግቢ ውስጥ ተከሰተ የተባለውን ጉዳይ በአግባቡ መያዝ አለመቻሉን ጠቅሰውም “መንግስት ዝግጅት ሳያደርግ ዜጎችን መላኩ ትክክል አልነበረም” ሲሉ ተችተዋል፡፡

በፖሊስ ከታገቱት መካከል በስልክ አግኝተን ያነጋገርናቸው ሰዎች ደህንነቶች “ይህ የአገር ሚስጥር በመሆኑ ለማንም እንዳትናገሩ” ብለው እንዳስጠነቀቋቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስና ደህንነቶች ሰው እንዳይወጣና እንዳይገባ በመከልከላቸው እስካሁን ምግብ እንዳልገባላቸውና “የሟቹ የደም ናሙና ነገ እስኪመጣ ድረስ ከግቢ መውጣት አትችሉም፡፡ ሌሎች ሰዎችም ወደ ግቢ መግባት አይችሉም፡፡ እስከነገ ለማንም መረጃ ባለመስጠት ተባበሩን” እንደተባሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ግቢውን በከበበት ወቅት የግቢው ነዋሪዎች “ችግር ካለ ባለሙያ መጥቶ ያረጋግጥ፡፡ ፖሊስ ለምን ያግተናል?” በሚል ከግቢው እንወጣለን በማለታቸው ጭቅጭቅ ተፈጥሮ እንደነበርም የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ይህ ዜና ከተሰራጨ በኋላ የተገኘው ተጨማሪ መረጃ ይህንን ይመስላል፡፡

በኢቦላ በሽታ ስጋት ከቤታቸው እንዳይወጡና እንዳይገቡ በፖሊስ እየተጠበቁ ያሉት የፈረንሳይ ሌጋሲዮን ነዋሪዎች በሽታው እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው እስኪታወቅ ድረስ 21 ቀን ቤታቸው ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉ ከጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደተነገራቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሐሙስ ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት መጥተው የጎበኟቸው ሲሆን በአካባቢ ተሰብስቦ ስለ ጉዳዩ የሚነጋገረውን የአካባቢውን ነዋሪ ፖሊስ ከቦታው በትኗል፡፡

ወደ ግቢው የሚገቡ የህክምና ባለሙያዎችና ባለስልጣናት እንዲሁም ሰዎቹ እንዳይወጡ የሚከታተሉት ፖሊሶችና ደህንነቶች ምንም አይነት ጥንቃቄ እንደማያደርጉ ከቤታቸው እንዳይወጡ የተከለከሉት ሰዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ከቤታቸው እንዳይወጡ የተደረጉት 10 ያህል ሰዎች በተለይ ወደ ውጭ የተላከው የሟቹ የደም ናሙና ሰውየው በኢቦላ እንደሞተ ካመለከተ 21 ቀን ሊቆዩ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ፖሊስ ሳይዛቸው ከቤት የወጡት የግቢው ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የተከለከሉ ሲሆን ከህመምተኛው ጋር ግንኙነት ነበረው ከተባለው የአምቡላንስ ሾፌሩ ጋር የተገናኙ ቢሆንም ለ21 ቀን ከቤታቸው ውጭ ሊቆዩ ይችላሉ ተብሏል፡፡ (ምንጭ፡ ነገረ ኢትዮጵያ ፌስቡክ ገጽ)

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule