መቼ አስቤው አውቃለሁ? መች አልሜዋለሁ...? ያ! የውሸት-ቋት ‘መስኮት’ - አንጀት አቃጣዩ፣ ቆሽት አሳራሪው - ሽበት አስበቃዩ፣ ድንገት ባንድ ቅጽበት - አክሮባቱን ሰርቶ፣ “ቅበዓ-ቅዱስ” መድኅን - ሃሴት ተቀብቶ፣ ስነግረው የኖርኩትን - መልሶ ሲነግረኝ፣ ወይ ጊዜ ወርቃማው - አፌን አስከፈተኝ፣ ...በቅጽበት የሆነው፣ - ምትሃት ያለበት፣ ከሰማይ የወረደ - እሚመስል አስማት..፣ በፍትህ-አልባው ስርዓት - በግፍ የታሰሩ…፣ የሰቆቃውን ገጽ - ቀርበው ሲናገሩ፣ በኢቲቪ ዜና - በእርግጥ ሰማሁ እንዴ? ጆሮዬን ልኮርኩር - እስኪ ዳግም አንዴ፤ በሕዝብ-አንጡራ ሃብት፣ በኢቲቪ መስኮት… …ቴዲ አፍሮን፣ ብርሃኑን…፣ ታማኝን አየሁት? እስኪ እረጋግጡልኝ? ዐይኔ ነው? ወይ ቅዠት? … አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለም ባንዲራ፣ በዚያች “ጠባብ” መስኮት በድምቀት … [Read more...] about “የኢቲቪ ሱሰኛ;”
Literature
ጽፈኪን
ጠ/ሚ/ር አብይ ከኪነ ጥበቡ ማህበረሰብ ጋር
ዛሬ ሰኔ 20፣ 2010 ዓ.ም ጠቅላዩ ከአርቱ ማህበረሰብ ጋር በጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 03፡00-05፡30 ድረስ በኪነ ጥበብ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ምንም እንኳ ከባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የታደለው የመጥሪያ ደብዳቤ "ሥልጠና" ቢልም፣ ነገሩ ስልጠና ሳይሆን ውይይት ነበር፤ የውይይት ጊዜ ቢያንስም። ዶ/ር አብይ የ"ሰተቴ" እና "እርካብና መንበር" መፃህፍቶች ደራሲ መሆናቸውንም ነግረውናል። የተወሰኑ ኮፒዎችንም በነፃ አድለዋል። እውነቱን ለመናገር ዶ/ር አብይ የአርት ፅንሰ ሐሳብ ላይ ባላቸው ጥልቅ ግንዛቤ ተገርሜያለሁ። አርት በአሜሪካ የጥቁሮች የእኩልነት ትግል ውስጥ ያለውን ሚና ያሳዩበትና በማርከስ ጋርቬይ፣ በማልኮም ኤክስ፣ በማርቲን ሉተር ኪንግ፣ በፕ/ት ኬኔዲ እና በቦብ ማርሌ መካከል የነበረውን የመንፈስ ትስስር ያቀረቡበት መንገድ በጣም መሳጭ ነው፣ … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር አብይ ከኪነ ጥበቡ ማህበረሰብ ጋር
የታሪክ ፈተናችን እና ያሬዳዊ ትዝታ፤ ከክላሽ እስከ ብዕር!
የለውጥ ውርጃ፣ የዘመናዊነት መጨናገፍ፣ የህዝባዊ ኃይል (ድምጽ) ተጽኖ ፈጣሪነት መኮላሸት፣…ድግግሞሻዊ የታሪክ አዙሪት አምሳያ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ እየተንሳፈፈች እዚህ ደርሳለች። የአገር ግንባታ ሲሚንቶ ውሉ አልይዝ ብሎ ንቃቃት በዝቶበት የታሪክ ፈተናዋን መሻገር የተሳናት ኢትዮጵያ፤ በውስጣዊ ቅራኔ እንደተናጠች፣ ቅራኔዎቹ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ ከቶም እየተባባሱ የማህበራዊ ትስስሮሽ ነባር ህሊናዎች እየተናጉ፣ ዘውጋዊ መስመሮች በስታሊናዊ “ዕይታ” የልዩነት መስመሮች እየጎሉ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች እየሻከሩ፣ ደም መቃባቱ እየበዛ በመሄዱ አገሪቱ ወደመፍረስ ጠርዝ በመገፋት ሂደት ላይ ትገኛለች። ከየትኛውም ጊዜ በከፋ መልኩ የርስ በርስ መጠራጠርና አለመተማመን ከፖለቲካ አደባባዩ ተሻግሮ በየግለሰቡ ጓዳ ገብቷል። በደብተራ ፖለቲካ ስትታመስ … [Read more...] about የታሪክ ፈተናችን እና ያሬዳዊ ትዝታ፤ ከክላሽ እስከ ብዕር!
ምነው ደም ደም አይለን?
ፍትህ ሳያደርቀው የፈሰሰን ፍዳ፣ ንስሀ ሳያጥበው የቆሸሸን ጓዳ፣ ዱለትን መቋደስ ከገዳዮች ጋራ፣ የሐጥያትም ሐጥያት የታሪክም ዕዳ! ፍትህ ነፃነትን መብትን ተርበው፣ ኢፍታዊነትን እንደ አውሬ ተናንቀው፣ ስንቶቹ ተሰው ባሩድ ተመግበው? ነፃነት ወይም ሞት በቃ ዘራፍ ብለው፣ ስንቶች ተሰውልን ጫካ ዱር ሸፍተው? በእሬቻ በጥምቀት በመስጊድ ሰገዳው፣ በሰፈር መንደሩ በገጠር ከተማው፣ እንደ ፋሲካ በግ የታረደ ስንት ነው? ባዶ ስድስት ጉድጓድ በጪስ የታፈነው፣ ቃሊቲ ዓለም በቃኝ የተዘቀዘቀው፣ ቅሊንጦና ዝዋይ በእሳት የነደደው፣ ሽሮሜዳ ታስሮ ጥፍሩ የወለቀው፣ ብር ሸለቆ አዘዞ ጉረኖ የገባው፣ ማሰቃያ ቦታው ጭራሽ ያልታወቀው፣ ስንት መከረኛ ምን ያህል ዜጋ ነው? የጋንቤላን ምድር ሽፍን ያደረገው፣ ኦጋዴን በርሃን በጎርፍ የጠረገው፣ ምን ያህል ሬሳ … [Read more...] about ምነው ደም ደም አይለን?
ቋንቋን በቋንቋ
ስለ ቋንቋ የተለያዩ እይታዎች መኖራቸው አዲስ አይደለም። የሚገርመው ይልቅ፣ ብዙዎች እንደ ሹምና አቡን ትእዛዝ ሲሰጣጡ ማየት ነው። ትእዛዙን ማን፣ እንዴት ይፈጽም? እይታዎችን ማቀራረብና መተግበርስ ይቻላል? መቸ በምን ቅደም ተከተል? ወዘተ። ይህን ያሰቡበት ቢኖሩ ድምጻቸው አልተሰማም። የራስን አጉልቶ፣ የሌላኛውን ማድበስበስ የተለመደ በመሆኑ፣ የጽሑፌ ይዘት ለያንዳንዱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ የተዘነጉ ጥቃቅን አሳቦችን ማነጋገር ይሆናል። ቋንቋ ቢያንስ ሀ/ ድንበር ተሻጋሪ መሆን ይኖርበታል፤ አማርኛ ተናጋሪ፣ እርስ በርሱ ብቻ ከሆነ፣ ከኬላው ውጭ በምን ይግባባል? ለ/ ድንበር ተሻግረን እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ወዘተ፣ የቆነጠርን ቢያንስ አኗኗራችንን ለማሻሻል እንደ ሆነ አንርሳ ሐ/ ቋንቋ ተሻጋሪ እንዲሆን፣ ድልድይ የሚሆን ቋንቋ ይሻል። አማርኛ ድልድይ ነው። እርግጥ፣ ሁሉን ቋንቋ ማወቅ … [Read more...] about ቋንቋን በቋንቋ
እኛም እንዳንሰቅለው!
እንደምን? ይመጣል! ከናዝሬት ላይ ነብይ፣ ልክ እንደተባለው ከወያኔም ዓብይ፣ ተገኝቶ ከመጣ - ጌታ ከመረጠው፣ ፈራሁኝ እንደሱ እኛም እንዳንሰቅለው! (ወለላዬ ከስዊድን) … [Read more...] about እኛም እንዳንሰቅለው!
ስማኝ ሰማእቱ!
ከባርነት ሞትን የመረጥከው ወንዱ፣ አፉን ክፍት አርጎ የዋጠህ መቃብሩ፣ የማዋይህ አለኝ ስማኝ ሰማእቱ፡፡ የፈሰሰው ደምህ በህልሜ እየታየኝ፣ አጥንትህ ከመቃብር እየጎራበጠኝ፣ እሾህ ቀጋ ሆኖ አላስተኛህ አለኝ፡፡ ለፍትህ ስትጮህ የቀረኸው ባጭር፣ ጎንደር ደብረታቦር ወልድያ ባህርዳር፣ ቡሬና ዳንግላ ማጀቴና አቸፈር፣ ዛሬም ወንድሞችህ ታስረዋል ግዮን ዳር፡፡ በስናይፐር የፈጁህ ህሊና ቢሶቹ፣ ለውጥ አመጣን ብለው ያንኑ ደገሙ፣ አንድ አስገዳይ ነቅለው ሌላውን ተከሉ፡፡ አጥንትህን ከአምቦ ከእሬቻ ለቃቅሞ፣ መሰላል አረገው ከለማ ጋር ሰርቶ፡፡ በስንት በጎች ደም እንደተነከረ፣ እጁን ሳይታጠብ አቢይ ቀደሰ፡፡ ኢያሱና ሙሴን ተከተሉ እያሉ፣ ስንቱን ዘልዛላ እንከፍ ከጀርባ አሰለፉ፡፡ ተመራጩ አስገዳይ መራጩም ገዳይ ነው፣ የሌላው ማሽቃበጥ ምን … [Read more...] about ስማኝ ሰማእቱ!
ዓመፀኛ ዋሻ
መነሻ፤ ወርሃ የካቲት ለነፃነትና ለባንዲራ ከወራሪዎች ጋር ተናንቀው ኢትዮጵያን በነፃነት ያቆምዋትን ሠማዕታት አብናቶቻችንን (አባት እናቶቻችንን) የምንዘክርበትና ስለባንዲራና ስለኢትዮጵያ ቃል ኪዳናችንንም የምናድስበት ወር ነው። እነሆ ደግሞ በዚህ ዘመን ኢትዮጵያን ካነቀው ሀገር በቀል ዘረኛ ወራሪ የህወሃት አገዛዝ ነፃነቷንና ክብሯን ለመመለስ በሚደረገው የህልውና ትንቅንቅ በህወሃት ወህኒ ቤቶች ወደር አልባ ናዚስታዊ ግፍና ሰቆቃ የተፈፀመባቸውን የነፃነት ታጋዮች ለማስፈታት ይህ ወጣት ትውልድ /ቄሮ ወፋኖ/ ባልተቋረጠው ሠላማዊ ትግል በትንግርተኛው ወርሃ የካቲት እንደ አብናቶቹ ታሪክ ሰርቷል፤ ህወሃትን በግማሽ አንበርክኮ ናሙናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝንም አሰናብቷል። እነሆም ናዚስት ህወሃት በህዝባዊ እምቢተኝነት ማንቁርቱን ታንቆ ያለ ውዴታው ተገዶ በየወህኒው የዘጋባቸው … [Read more...] about ዓመፀኛ ዋሻ
እስክንድር ነጋ “ሃሳብን የመግለጽ መብት” ሽልማት
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዘ ሄግ ከተማ ትናንት ምሽት በተካሄደው የ2018 የፔን እና የኦክስፋም ኖቪፕ - "ሃሳብን የመግለጽ መብት" አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን ያዘጋጁት ኦክስፋም ኖቪፕ እና ፔን ኢንተርናሽናል የተሰኙ አለማቀፍ ተቋማት ሲሆኑ ከእስክንድር ነጋ ጋር የአመቱ ተሸላሚ ሆና የተመረጠችው የቬኒዙዌላዋ ጋዜጠኛ ሚላግሮ ሶካሮም ልብ የሚነካ ንግግር አድርጋለች። እስክንድር ነጋ በስፍራው ተገኝቶ ሽልማቱን መቀበል ባይችልም ከእስር ቤት ሆኖ የላከው I SHALL PERSEVERE (እኔ እጸናለሁ) የሚለው መልእክቱ በምሽቱ ዝግጅት ላይ ተነብቧል። በጃዝ ሙዚቃ እና በግጥም የታጀበው ይህ የስነጽሁፍ እና የሽልማት ዝግጅት እጅግ ደማቅ ነበር። ሄግ ትያትር በተዘጋጀው በዚህ አለም ዓቀፍ የስነ ጽሁፍ ምሽት መክፈቻ ላይ የከተማዋ ከንቲባ - የኦክስፋም … [Read more...] about እስክንድር ነጋ “ሃሳብን የመግለጽ መብት” ሽልማት
“መንግሥት ሲኖረኝ ቀስቅሱኝ”
በዚህች ምድር ላይ የቆየው ለ40 ዓመታት ብቻ ነው፤ ከ1970 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 2010 ዓ/ም። ተስፋዋና ፍሬዋ ለልጆቿ እንደ መንግሥተ ሠማያት መንፈስ ብቻ በሆነው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ በመከረኛዋና ታሪካዊዋ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ - ጨርቆስ - ተወልዶ አደገ። ብሩህ አእምሮን የተቸረ በዕውቀት ቀሳሚነቱ የናረና ከሁሉም በላይ ግን ሀገራዊና ወገናዊ ሰብዕናን ከስነ ምግባር ጋር ያዋሃደ የኢትዮጵያ ልጅ ኢትዮጵያዊ ሆነ። ስለ ሀገሩና ስለህዝቧም ሲል በናዚስት የዘረኝነት አስተምህሮ ካበዱት ከግፍ ጠማቂዎቹ ናዚስት ወያኔ ገዢዎች የሀገሩን የፍዳ ገፈት ተግቶና ከሀገሩ ተገፍቶ በሰው ሀገር በስደት ተንከራትቶ አለፈ። እሱም ጋዜጠኛና የሰብዐዊ መብት ተሟጋቹ ኢብራሂም ሻፊ ይባላል። ግፈኞቹና በግፍ ዘመነ ሥራ ዕድሜ የጠገቡት ሀገሩን ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ በ1983 ዓ/ም እሱ ገና አስራዎቹን … [Read more...] about “መንግሥት ሲኖረኝ ቀስቅሱኝ”