... “ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ፣ ሃሳቤም ተሟላ መንፈሴም ታደሰ፤...” ለዛሬዋ ጽሁፌ መግቢያነት የመረጥኳት ግጥም፣ በእውቁ ድምጻዊ በጥላሁን ገሠሠ ከተቀነቀኑት አያሌ የማኅበራዊ ዘርፍ ዘፈኖች አንዱ የሆነው ዘፈን አዝማች ናት(በሃሳባችሁ ዜማውን እያስታወሳችሁ ተከተሉኝ፤ በተለይ ከአጃቢ የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ጎልታ የምትሰማዋን፣ የአየለ ማሞን የማንዶሊን ዜማ እያዳመጣችሁ)። ... ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት “አማኒ ኢብራሂም — ’ያልታወቀው‘የጥበብ ሰው” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ቢጤ በኢትዮጵያውያኑ ድረ-ገጾች (በኢትዮ-ሚድያ፣ በኢኤምኤፍ፣ በቋጠሮ፣ በጎልጉል...) ላይ ለንባብ አብቅቼ ነበር። ጽሑፉ እንደወጣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ ከሰላሣ ዓመታት በላይ የትና እንዴት እንዳለ ያላወኩትን፣ በሙዚቃ ሙያ በእጅጉ የተካነውን፣ ሁሌም ብዙዎች በአርዓያነት የሚጠቅሱትንና … [Read more...] about ዳግም ተገናኘን!
Literature
ጽፈኪን
“ያን እኔን አፋልጉኝ!”
የዘመኑን ፈሊጥ የመኖርን ምስጢር ሳስተውለው ውዬ ቆሜ ስመረምር ጥበቡ ገብቷቸው መሄጃውን አውቀው መላ የጨበጡት ስሌት አስተካክለው ከተጠቀሙበት ኃያል ብልሃቶች አንዱ ማስመሰል ነው ለመኖር ከሰዎች እንደውም አንዳንዱ ከማስመሰል አልፎ በረቀቀ ጥበብ በተንኮል ቆልፎ ለተዘጋጀበት ላሰበበት ዕቅድ ማሰለፍ ይችላል በግድና በውድ እንዲሁም ሌላውን አድርጎ መሰላል ሁሉንም አሟልቶ እላይ በመንጠልጠል ሲፈልግ አጣልቶ፤ ሲሻው በማስታረቅ ሌላን እየጎዳ ጥቅሙን በማስጠበቅ በተገኘው መላ ባዘጋጀው መንገድ መረቡን ዘርግቶ ገንዘብ ለማሳደድ ምንም ጊዜ - የትም እሱን አስበልጦ አምሮ ተሽቀርቅሮ በአልባሳት አጊጦ ድሮውንም ያለው የቱጃር ቤተሰብ ገና በልጅነት ያየ ብዙ ገንዘብ ሃይማኖት አክባሪ ጿሚ ጸሎተኛ እጁ እማይታጠፍ ካየ ችግረኛ መምሰሉ አስገርሞኝ በማውቀው … [Read more...] about “ያን እኔን አፋልጉኝ!”
ሐተታና ግምገማ፤ የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]
የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]፤ 2009ዓ.ም፤ አ/አ፤ አታሚ አልተገለጸም፤ 10ዶላር፣ 100 ገጽ የማለዳ ድባብ፣ ለ በዕውቀቱ ሥዩም አራተኛ የግጥም ሥራው ነው። መጽሐፉ ሦስት ክፍሎች አሉት፤ “ግጥምና የዘመን መንፈስ” [ገጽ 5-9]። ግጥሞች [ገጽ 17-91]። “ጉደኛ ስንኞች” እና “ሙሾና ባለቅኔ” [ገጽ 93-100]። መድብሉ፣ ቀድሞ ካስነበባቸው ላይ አዳዲሶች ተጨምረውበት የተዘጋጀ ነው [ገጽ 9]። የትኞቹ አዳዲሶች እንደሆኑ አልተገለጸም። ግጥም ከስድ ንባብ ይልቅ የግል እይታዎችን፣ ማህበራዊ ትረካዎችን ለመቋጠርና ለማስታወስ ይረዳል። ቅኝቱና አወራረዱ ለጆሮና ለዐይን ይጥማል። ግጥም ማህበራዊ እሴት አለው፤ በሥልጣን ለሚባልጉ እርምት ለመስጠት [“ይድረስ ለጥም ሚኒስትር”፣ ቁ.71]፣ የሕይወትን አጭርነት ለማሳሰብ፣ ከሚታየው ውጭ የላቀ ተስፋ እንዳለ ለማወጅ፣ የግለሰብ … [Read more...] about ሐተታና ግምገማ፤ የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]
ሞት የሰጠን ደስታ
የታጨደው ሳር ድርቆሽ ነው የከብቶች መኖ በመሆን በበሬ ጫንቃ ድካም ጠግቦ አደር ያደረገን፤ የሞተው የግጦሽ ሳር ነው ጮሌ ፈረስ አሳድጎ በጦር ሜዳ የድል ብሥራት ያቀዳጀን ጀግና ተዋጊ አድርጎ፤ የበሬውን ቆዳ ከበሮ የበሬውን አንጀት ጅማት የፈረሱን ሞት በደል የሸንበቆውን ያካል ስብራት፤ የእንስሳቱን ሞት ከእሳሩ ሞት ጋር ስናዋድደው ከሞት ምንጭ ነው ለካስ የደስታ ጅረት የሚወርደው። የሞተ … [Read more...] about ሞት የሰጠን ደስታ
ጣምራ ቁስል
ደራሲ፤ ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ (ዶ/ር) ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ ቀዳሚ፤ እነሆ ከጣምራ ቁስል በፊት “ቀይ አንበሳ” ነበረ። እነሆም ስለ ‘ቀይ አንበሳ’ ‘በማንኪያ’ እናቀምሳለን። እንዲህ ብለን፤ አልኻንድሮ ዴል ባዬ ኩባዊ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ለንደን፤ እንግሊዝ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሀኪም ወርቅነህ ማርቲን (ደብሊው ማርቲን) በጋዜጣ ላይ ባወጡት ማስታወቂያ አነሳሽነት አምባሳደሩ ፊት በመቅረብ ለአትዮጵያ በፈቃደኝነት ለመዋጋት የሚፈልግ መሆኑን ይገልፃል። አምባሳደር ወርቅነህም ጠየቁት፤ “ከእኛ በኩል ሆነህ ለመታገል ስትል ነው ከአገርህ ድረስ የመጣኸው?” “አይደለም። ከስፔን ገና መምጣቴ ነው። ወደ ኩባ ለመመለስ ነበር እቅዱ። ለውጪ አገር መኮንኖች በአቢሲኒያ ላይ የተቃጣውን ወረራ ለመዋጋት የቀረበውን ጥሪ … [Read more...] about ጣምራ ቁስል
አታስብ ይሉኛል!
ማሰብ ማሰላል - ማጤን ማውጣት ማውረድ፤ ባ'ይምሮ መፀነስ - ሃሳብን ማዋለድድ፤ ከምናብ ጓዳ ውስጥ - ምስጢርን ፈልፍሎ፤ ያይምሮ መረዋን - ማንኳኳት ደውል :: መላ ማፈላለግ - እንዲህ ቢሆን? ማለት ፤ አይምሮን ኮትኩቶ - ዕውቀት ዘርቶ ማምረት፤ ባ'ንዱ ውስጥ ሌላው_ በሌላው ውስጥ አንዱ_ እንዳለ መረዳት:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) አሥራደው (ከፈረንሳይ) … [Read more...] about አታስብ ይሉኛል!
ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
ከውጪ ሀገር የመጡ ሰዎች ለአፄ ምኒልክ ስለ ፎቶግራፍ እንዲህ ብለው አስረዷቸው "በአውሮጳ አንድ ትንሽ ሳጥን አለች ሰውን፣ ፈረሱን፣ ቤተመንግስቱን ሁሉ ወደ ሳጥኗ ታስገባና ሁሉን ትንሽ አርጋ ታሳያለች" አሏቸው። ምኒልክም በሰሙት ነገር ተገርመው እንዴት ይሆናል ይሄን ነገር ማየት አለብኝ ብለው የፎቶ ማንሻ እንዲመጣ አዘዙ። የፎቶ ማንሻውም (ካሜራ) ከእነ አንሺው በ1875 ዓም ወደ ሀገራችን ገባ። ሆኖም ግን አጼ ምኒልክ ፎቶውን ሊነሱ ሲሉ ቀሳውስቱ መኳንንቱ ከለከሏቸው፣ ርኩስ ነገር ነውና አጥፉልን አሏቸው። ምኒልክም "እግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር አታርጉ፣ አትንኩ፣ ነውር ነው ማለት አምላክን መቃውም ነው እንዲህ ያለ ሀሳብ አታስቡ ዞር በሉ ከፊቴ" ብለው ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ም አጼ ምኒልክ የምትመለከቱትን የመጀመሪያ ፎቶ ተነሱ። መልካቸውንም በማየታቸው … [Read more...] about ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
ትልቅ ሰው ትልቅን
ይባላል ... ድሮም ይነገራል ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ሲባል በፊትም ሰምተናል ይኸው ዕውነት ሆኖ ሲፈጸም አየን ቃሉ በነጋሽ ገ/ማርያም፣ በተስፋዬ ሳህሉ የሐምሌ ወርን የሰላሳ ቀናት እቅፍ በነኀሴ ተክተን ሳናልፍ ሁለቱን ታላላቅ የጥበብ ከዋክብት አከታትለን አጣን የአዛውንቶች ክበብን ዘጋን ፀጋዬ ገ/መድህን በጻፈው አባተ መኩሪያ ባዘጋጀው አውላቸው ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ በተጫወቱበት ዓለሙና ሲራክ አብረው በሆኑበት እነ አስናቀች ወርቁ፣ በላይነሽ አመዴ፣ እነ አባተ መኩሪያ መላኩ አሻግሬና ዘነበች ታደሰ እነ ሠይፈ አርኣያ ሙናዬ መንበሩ፣ ኃይማኖት ዓለሙ፣ እነ አስራት አንለይ በኃይሉ መንገሻ፣ ሱራፌል በጋሻው፣ ያ ፍስሀ በላይ በተካፈሉበት ... የላይ ቤት ትዕይንት ተባብረው አብረው አንድ … [Read more...] about ትልቅ ሰው ትልቅን
ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ የቃኚው ማስታወሻ፤ ጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ጁላይ 2 / 2017 “ራስ እምሩን በተመለከተ” በሚል ርዕስ አንድ ፅህፍ ለንባብ አብቅቷል። ይህ የጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣን አቋም ያንፀባረቀው ፅሁፍ ሙያዊ ሥነምግባርን (ፕሮፌሽናል ኤቲክስ) ከብቃትና ከሃላፊነት ጋር ያዋደደ ስህተቱንም በግልፅና ያለማወላወል የተቀበለና ለእርማቱም መፍትሄን ያመላከተ መሆኑ የድረገፁን ዝግጅት ክፍል የሚያስወድሰውና በአርአያነትም ከመጀመሪያው ረድፍ የሚያቆመው ይሆናል። የሚዲያ ተልዕኮ መሰረቱ እንዲህ ሲሆን ተዓማኒነቱንና ሚዛናዊነቱን ያረጋግጣልና። በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በተፃፈው ‘አዳፍኔ’ መፅሀፍ ላይ ክቡራ ልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ በአርበኝነታቸው ሳይሆን ‘ከጣሊያን ደሞዝ ተቆራጭ የሆነላቸው ባንዳ’ ተደርገው ከባንዶች የስም ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ለዚህ ቃኚ … [Read more...] about ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
ስምህን ሳላነሳ፣ ምኑን ሆንከው ፀጋ ለአብሮነት መኖር፣ እየሆንክ አደጋ፣ አድርገህ ከያዝከው፣ የሙሉቀን ሥራ ለማቃባት ደም፣ ኦሮሞን ካማራ። ‘ጀሃዳዊ ሃረካት’፣ እና ‘አኬል ዳማ’ በለምለሟ አርሲ፣ በአኖሊ ከተማ ወያኔ ያቆመው፣ የጥላቻ ሃውልት የተሸከመው እጅ፣ የተቆረጠ ጡት ሆነ ውጤት አልባ፣ አነሰ አሉህ እንዴ አሽከርካሪዎችህ፣ ፍጠር ሌላ ዘዴ? ጦርና ጎራዴ ሕዝቡን ለማማዘዝ ድንገት ቱግ ብለህ፣ የምትረጨው መርዝ። ዕውቀት ነበርኮ፣ ወገንን ለመጥቀም ተከባብሮ እንዲኖር፣ ተዋዶ በሰላም አየ ያንተስ መማር፣ “በረከተ መርገም”!! ተስፋ ለቆረጠ፣ ቀን ለጨለመበት ለጭቁን ወገኑ፣ መላ ለጠፋበት ታጭዶ ለሚወቃው፣ በአግዓዚ ጥይት በአላሚ እሩምታ፣ በቅሊንጦ ታጥሮ ዶጋመድ ለሆነው፣ በሳት ተንጨርጭሮ ፍዳውን ለሚያየው፣ እሥር ቤት ታጉሮ እርቃኑን ለቀረው፣ … [Read more...] about ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!