The journey which author Ato Kidane Alemayehu chronicles in his new book takes him through Lesotho, Tanzania, Uganda, United Arab Emirates and the Horn of Africa as a representative of the United Nations, and ultimately to establish an organization dedicated to confronting “Fascist Italy and the Vatican.” His book contributes valuable information to the history of East Africa, the United Arab Emirates, and to the rationale behind Ethiopia’s struggle to win recompense from Italy for crimes … [Read more...] about Kidane Alemayehu, My Journey with the United Nations and Quest for the Horn of Africa’s Unity and Justice for Ethiopia
Literature
ጽፈኪን
ደም ነው ሥርየቱ
ዐባይ ቢሻው ይጉረፍ በጣና ላይ ነግሶ አሎሃ ይደፍርስ ተከዜም ደም ለብሶ ማሂንም አቋሽም ጓንግም በሙላቱ መሻገሪያ ይንሳ እስኪያልፍ ክረምቱ ይፎክር ያቅራራ ይኩራ በጉልበቱ ድሮም እንዳይፀዳ በጎርፍ ውኃ ታጥቦ የጀግና ሰው ሞቱ ያውቃሉ እናውቃለን ዛሬም እንደ ጥንቱ ደም በደም ይፀዳል ደም ነው ሥርየቱ። ለጀግና ዕምባ አይረጩም ፀጉርም አይላጩም ዋይታና ለቅሶ ሙሾ አይደረድሩም ወይም ፊት አይነጩም እንደ አባት አደሩ እንደ ጎንደር በሃል ደም ነው ሥርየቱ ደም በደም ይፀዳል። አለፋ ጣቁሳ ደንቢያና ፎገራ ጭልጋ ገለድባ ከሽንፋ እስከ ቋራ ጎዛምን በላያ ከመተክል ፓዌ ከሻግኔ ወንበራ ከፍኖተ ሰላም ማንኩሳ እንጅባራ መተማ ሰራቆ ጫቆና አዳኝ አገር ቆላ ደጋ ዳሞት ቋሪትና አቸፈር እነሴና ነብሴ ሞጣ ቀራኒዎ ጭስ ዐባይ ባህር ዳር ነፋስ መውጫ ጋይንት እስቴ ደብረ … [Read more...] about ደም ነው ሥርየቱ
ዕዘኑ ለቀሪ
የመቅደላው ደባ ቋጠሮ የተቀበረው በቂም ጓሮ የምስጢሩ ገመና ለሥልጣኑ ንግሥና ከጠላት ጋር ወግኖ በተቸረው ኃይል መቅኖ መይሳውን አስገድሎ ለመግዛት ተደላድሎ በትረ መንግሥቱን ምራጭ ካሳ የጨበጠበት ድርጊት ጠባሳ ደረስጌን በውቤ ብሎ የቂም ብድሩን ከፍሎ የጎንደሮች መሬት ቁርሾ የበደሉ ዋይታ ሙሾ የግፉ ክፋት ገመና ይደረደራል ገና በበገና በበገና። ያችን የሙታን እናት አጉል ድከሚ ብሏት ያለ ፋይዳ ከንቱ ልፊ ዘርሽንም በዘር አጥፊ ለማለት ይመስላል መለእክቱ ነገረ ሥራው ኩነቱ። ለባለ ቀኑ ድሎት የማይጓደል አቅርቦት ይረጋገጥ ዘንድ ታልሞ የራሱን ኩራዝ አጨልሞ በየመብራቱ ምሰሶ ስር ዘብ መቆሙ ደብረታቦር ምፀቱ ለገብርዬ... ለገልሞ በአግራሞት አስደምሞ የትንብቱ ቅላጼ መዋዕሉ ለካስ ጊዜ ኖሯል ባለድሉ። ለጎንደሮች መከራ ለባለ … [Read more...] about ዕዘኑ ለቀሪ
አዲስ እንደ ቬኒስ
“አንተስ…?”
ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችንወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ...?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! (ወለላዬ) … [Read more...] about “አንተስ…?”
ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት ኣምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ለሰው ኣይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡ (በእውቀቱ … [Read more...] about ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
“የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!
ለረጅም አመታተ የጣልኩትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው እንድመዝ አስገደደኝ - በ ኢትዮ-ሚዲያ (Ethiomedia) እና በጎልጉል (Googlgule) ድህረ-ገፆች ላይ ከወራት በፊት በዶክተር ፍቃዱ በቀለ በተባሉ ግለሰብ በ"የተቆለፈበት ቁልፍ" መፅሐፉ ላይ የቀረበ አንድ ፅሑፍ። "ሃያሲው" በዘመናችን አቻ ያላገኙለት (ወደር የሌለው) መፅሐፉ መሆኑን ነው የገለፁልን። "...የስነ-ጽሁፍም ዋና ዓላማው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን አስቀያሚም ሆነ ቆንጆ ነገሮች ስዕላዊ በሆነ መልክ መግለጽ ሲችሉና አንባቢውን በልዩ ሃሳብ ውስጥ ተመስጦ እንዲዋኝ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው።..." በማለት ካብራሩ በኃላ ከ`ዚህ አንፃር "የተቆለፈበት ቁልፍ" እንደተዋጣለት መሰክርነታችውን ይሰጣሉ። አንዲህ ሲሉ "....በታሪካችን ውስጥ በመጀመሪያ ጊዜ በልዩ አቀራረብ የተዘጋጀና የተጻፈ ትምህርታዊ መጽሀፍ ነው … [Read more...] about “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!
“እኩል ደራ ደራ ከነ‘ሜቴ ጋራ!”
ገጣሚና ደራሲ... ከግዑዙ መሬት፣ ከመንደሩ ይልቅ ከዘር ማንዘሩ፣ ሰብዓዊነትን ያልማል ብዕሩ “የሰው ልጅ ልብ...” ነው አገሩና ድንበሩ! ሰብዓዊነት ነው ክብሩ፤ ገጣሚ አገር የለውም፣ “ዩኒቨርሱ”ም አይበቃውም፤ ሰዋዊ ህመም ያመዋል፣ ፈውሱም ይፈውሰዋል፣ ገጣሚ ያ ይበቃዋል! ወርዶ ወርዶ “ቀየ መንደር ውስጥ አይወድቅም” አዎ! ገጣሚ፣ ደራሲ እንዲያውም አገር የለውም፣ የበዓሉ አገሩ ሰው ነው፣ “...ህንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ፣ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ፣ የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር፣ የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ድንበር...” (ኦሮማይ) ጸጋዬም ጊንጪ ኢምንት ቢሆንበት ጉደር፣ አምቦ፣ ቡራዩ ... ጠ’ቦበት፣ አዲሳ’ባ ኢትዮጵያም ብታንስበት፣ ብዕሩ ፈርዖኦንን ተመኘ፣ ነፈርቲቲ እና አፍሮዳይትን … [Read more...] about “እኩል ደራ ደራ ከነ‘ሜቴ ጋራ!”
የተካደ ትውልድ
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው የተካደ ትውልድ፤ አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፤ የተወለደ’ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትን የማያውቅ፤ ረፍት የተቀማ አልጋው ያጋም እሾህ፤ ምኝታው የሣማ የተካደ ትውልድ፤ ሞቶ እንኳ ሬሳው፤ አይላላለት ቀንበር በዘብ እጅ ተገድሎ፤ በሹም የሚቀበር ከጡት አስጥል በላይ፤ ኑሮ የመረረው እንዳይሄድ፤ ጎዳናው፤ የተደናገረው ድል ያልሰመረለት ትግል ሳይቸግረው የተካደ ትውልድ በሥጋ በነፍሱ በቀልቡ በገላው ኧረ ምንድን ይሆን ፤ ምንድን ይሆን መላው? (በዕውቀቱ ሥዩም) … [Read more...] about የተካደ ትውልድ
“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ
ሰላም ጎልጉሎች . . . እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ከኢትዮጵያ ዛሬ ጋር በግጥሞቼ ሳቢያ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። እናንተም ግጥሞቼን በተገቢው ሁኔታ ያስተናገዳችሁልኝ ስለሆነ እናንተም (ዘንድ) ቢታተም እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ። ወለላዬ መዝጊያ ትሁንልኝ መቶ ራት ግጥሞችን - ተሸክሜ ይዤ፤ ረብዕ ረቡዕ ስጥል - አንድ አንዷን መዝዤ በዚች ባሁኗ ቀን - በጨበጥናት ሳምንት፤ ወሩን ስደምረው - ሆነኝ ሁለት ዓመት፡፡ ዳግም በአዲስ ዓመት - እስከምንገናኝ፤ የዘንድሮው መዝጊያ - ይቺ ትሁንልኝ፡፡ (ወለላዬ) ወለላዬ በየሳምንቱ ረቡዕ ረቡዕ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል ሳያቋርጥ 104 ግጥሞች በመጻፍ አስነብቦናል። በነዚህ ግጥሞቹ እኛን ሆኖ ውስጣችን ገብቶ ያልተናገርነውን ተናግሮልናል። ታዝበን ያለፍነውን … [Read more...] about “[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ