“ደሸት” የብርሃን እውነት!
የማጂ፣ የጂማ፣ የመንዲ፣ የመደባይ አባት
የማራ፣ የዥማ፣ የገንቲ፣ የአሬቲ … አያት
የአማራው፣ የኦሮሞው፣ … የዘር ግንድ አውራ
የመተሳሰሪያ እውነተኛ ምንጭ አሻራ!
“ደሸት” ኢፋ ዹጋ ፍጥረተ ማለዳ
የዘር ሀረግ ገመድ ምስጢራዊ ጓዳ
አባ ቃሉ
አባ ውሉ
አያ ፍቅሩ
ትስስሩ
ዘረ ሸጋ
ኢፋ ዹጋ
መሆንህን አምኖ አማራ ኦሮሞ
ስምህን በስሙ አትሞ
“ደ”ን ደግ ብሎ አንብቦ
“ሸ”ን ሸበበ ብሎት አንግቦ
“ት”ን ትስስር ይለዋል ውልደቱን ከትቦ
“ደሸት” የዘር ምንጩ
አባ እቅጩ
ስመ ክብሩ
ውስጠ ምስጢሩ
“ደሸት” የብርሃን እውነት! (ኢፋ ዹጋ!)
ዘሩን ሲያበዛ ሲዘረጋ
ማጂ፣ ጂማ፣ መንዲ፣ መደባይ
ብሎ ሰይሞ የዘር ሲሳይ
መደባይ ስሙን ከስሙ መዞ
ኦሮሞ ብሎ መጠሪያ ይዞ
በደሸት አያትነት ሲኮራ
የጂማ ልጅ ማራ
“አ – ማራ” ወይም “ሃ – ማራ”
ብሎ ራሱን ጠራ
“ማራ” የሱባ ቃል ትርጉሙን
ማ – ማለት እውነት መሆኑን
ራ – ትርጉሙ ብርሃን መያዙን
አረጋግጦ ተቀብሏል
“ማራ” እውነትና ብርሃን ነው ብሏል
እንዲህ ነው የዘር ግንዱ
እንዲህ ነው አወራረዱ
እንግዲህ አማራን ከኦሮሞ፤ ኦሮሞን ከአማራ
በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ስፍራ
ማንም አይችል ሊበታትን ሊለያየው
ደሸት የብርሃን እውነት (ኢፋ ዹጋ) ነው።
ወለላዬ ከስዊድን
***********
ደሸት ”የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” በተባለው መጽሐፍ ላይ የኢትዮጵያ ነገዶች አባት መሆኑ ተጽፏል።
ማስታወሻ:- ለመጽሐፉ ደራሲ ለፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ
መታሰቢያ:- ለደራሲው ጽሑፍ መነሻ ለሆኑት መሪራስ አማን በላይ
ehapa4eve says
We don’t need some fiction and legend to unite amara and oromo. This professor has dodgy sources that he won’t let them be verified and as customary diaspora and ethios back home are accepting it as true. No it is not – simple. The burden of proof is on Professor Tolossa himself. People can be united, especially oromo and amara, without the need to resort to this. Please do not promote such false history. The simple question who is Deshet’s dad? Some fish?