ወንዙ እና ዛፉ April 19, 2017 05:37 am by Editor Leave a Comment ስርሽን አየሁት ቁልቁል ተዘርግቶ፣ ረዝሞ ተባዝቶ፣ አንድ አንቺን ሊያሳድግ፣ አንድ አንቺን ሊያቀና፣ እጅግ ተበራክቶ፣ በዚህ ከቀጠለ የጉዞ ርዝመቱ፣ ውፍረት ከጨመረ፣ ካደገ ቁመቱ፣ ወንዙ አንጀቱ ታልቦ፣ መቅኒው ተመጥምጦ፣ አፅመ ወዙ ደርቆ፣ ደም ውሃው ተመጦ፣ መላ አካሉ ፈርሶ እርቃኑን ተጋልጦ፣ ባዶ መቅረቱ ነው ድንጋይ ጥርሱ ገጦ፣ ወለላዬ ከስዊድን (welelaye2@yahoo.com) Share on FacebookTweetFollow us
Leave a Reply