በዚህች ምድር ላይ የቆየው ለ40 ዓመታት ብቻ ነው፤ ከ1970 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 2010 ዓ/ም። ተስፋዋና ፍሬዋ ለልጆቿ እንደ መንግሥተ ሠማያት መንፈስ ብቻ በሆነው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ በመከረኛዋና ታሪካዊዋ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ - ጨርቆስ - ተወልዶ አደገ። ብሩህ አእምሮን የተቸረ በዕውቀት ቀሳሚነቱ የናረና ከሁሉም በላይ ግን ሀገራዊና ወገናዊ ሰብዕናን ከስነ ምግባር ጋር ያዋሃደ የኢትዮጵያ ልጅ ኢትዮጵያዊ ሆነ። ስለ ሀገሩና ስለህዝቧም ሲል በናዚስት የዘረኝነት አስተምህሮ ካበዱት ከግፍ ጠማቂዎቹ ናዚስት ወያኔ ገዢዎች የሀገሩን የፍዳ ገፈት ተግቶና ከሀገሩ ተገፍቶ በሰው ሀገር በስደት ተንከራትቶ አለፈ። እሱም ጋዜጠኛና የሰብዐዊ መብት ተሟጋቹ ኢብራሂም ሻፊ ይባላል። ግፈኞቹና በግፍ ዘመነ ሥራ ዕድሜ የጠገቡት ሀገሩን ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ በ1983 ዓ/ም እሱ ገና አስራዎቹን … [Read more...] about “መንግሥት ሲኖረኝ ቀስቅሱኝ”