በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዘ ሄግ ከተማ ትናንት ምሽት በተካሄደው የ2018 የፔን እና የኦክስፋም ኖቪፕ - "ሃሳብን የመግለጽ መብት" አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን ያዘጋጁት ኦክስፋም ኖቪፕ እና ፔን ኢንተርናሽናል የተሰኙ አለማቀፍ ተቋማት ሲሆኑ ከእስክንድር ነጋ ጋር የአመቱ ተሸላሚ ሆና የተመረጠችው የቬኒዙዌላዋ ጋዜጠኛ ሚላግሮ ሶካሮም ልብ የሚነካ ንግግር አድርጋለች። እስክንድር ነጋ በስፍራው ተገኝቶ ሽልማቱን መቀበል ባይችልም ከእስር ቤት ሆኖ የላከው I SHALL PERSEVERE (እኔ እጸናለሁ) የሚለው መልእክቱ በምሽቱ ዝግጅት ላይ ተነብቧል። በጃዝ ሙዚቃ እና በግጥም የታጀበው ይህ የስነጽሁፍ እና የሽልማት ዝግጅት እጅግ ደማቅ ነበር። ሄግ ትያትር በተዘጋጀው በዚህ አለም ዓቀፍ የስነ ጽሁፍ ምሽት መክፈቻ ላይ የከተማዋ ከንቲባ - የኦክስፋም … [Read more...] about እስክንድር ነጋ “ሃሳብን የመግለጽ መብት” ሽልማት