• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እስክንድር ነጋ “ሃሳብን የመግለጽ መብት” ሽልማት

January 19, 2018 01:23 pm by Editor 3 Comments

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዘ ሄግ ከተማ ትናንት ምሽት በተካሄደው  የ2018  የፔን እና  የኦክስፋም ኖቪፕ – “ሃሳብን የመግለጽ መብት” አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን ያዘጋጁት ኦክስፋም ኖቪፕ እና ፔን ኢንተርናሽናል የተሰኙ አለማቀፍ ተቋማት ሲሆኑ ከእስክንድር ነጋ ጋር የአመቱ ተሸላሚ ሆና የተመረጠችው

ሚላግሮ ሶካሮ

የቬኒዙዌላዋ ጋዜጠኛ ሚላግሮ ሶካሮም ልብ የሚነካ ንግግር አድርጋለች። እስክንድር ነጋ በስፍራው ተገኝቶ ሽልማቱን መቀበል ባይችልም ከእስር ቤት ሆኖ  የላከው I SHALL PERSEVERE (እኔ እጸናለሁ) የሚለው መልእክቱ በምሽቱ ዝግጅት ላይ ተነብቧል።

በጃዝ ሙዚቃ እና በግጥም የታጀበው ይህ የስነጽሁፍ እና የሽልማት ዝግጅት እጅግ ደማቅ ነበር።

ሄግ ትያትር በተዘጋጀው በዚህ አለም ዓቀፍ የስነ ጽሁፍ ምሽት መክፈቻ ላይ የከተማዋ ከንቲባ – የኦክስፋም ኖቪፕ እና ፔን ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንቶች በመገኘት ስለ ፕሬስ አፈና ንግግር አድርገዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ለዚህ ሽልማት የበቃው በከፍተኛ አፈና እና ስቃይ ውስጥ ሆኖ ለፕሬስ ነጻነት በከፈለው ዋጋ እንደሆነ የፔን ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ሚስ ጃኒፈር ክሌመንት ተናግረዋል።

የኮክስፋም ኖቪፕ ፕሬዝዳንት ሚስ ፋራ ካሪሚም እስክንድር ነጋ በከፍተኛ ተጽእኖ ውስጥ ሆኖ ሃሳቡን በመግለጹ መታሰሩን ገልሰው – ለእስክንድር እና እንደ እስክንድር ላሉ የፕሬስ ነጻነት ተፋላሚዎች ትልቅ ክብር እንደሚሰጡዋቸው ተናግረዋል።

በሽብር ተወንጅሎ 18 አመታት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዓለም አቀፍ ሽልማት ሲያገኝ ይህ የመጀመርያው አይደለም። በከፍተኛ ተጽእኖ ውስጥ ሆኖ ሃሳቡን በመግለጹ እና በዚህም ለፍትህ አልባ እስር በመዳረጉ፤ እ.ኤ.አ. በ2011  የፔን አሜሪካ አዋርድ በኒውዮርክ ፤ በ2012 ፔን ባርባራ ጎልድስማን፤ በ 2014 ፔን ዋኒፍራ ጎልደን አዋርድ፤ በ2015 ፔን ካናዳ አዋርድ እንዲሁም  ሂዩመን ራይት ዋች ባዘጋጀው የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ነው።

የእስክንድር ባለቤት ሰርካለም ፋሲል ሽልማቱን በባለቤትዋ ስም እንድትቀበል ብትጠራም በአንዳንድ የጉዞ እክሎች ሄግ ላይ መገኝት አልቻለችም። ሰርካለም ከቨርጂንያ የላከችው ልብ የሚነካ መልእክት ግን በአዳራሹ ለታደመው ሕዝብ እንዲነበብ ተደርጋል። ከጫፍ እስከጫፍ ጢም ያለው በዚህ አዳራሽ ውስጥ በርካታ ሎሬቶች፤ አለም አቀፍ ደራሲያን እና ገጣሚዎች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Literature, Social Tagged With: eprdf, eskinder, Milagros Socorro, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    January 20, 2018 10:37 pm at 10:37 pm

    ሰዎች!!! እስክንድር ነጋን መልቀቅ ማለት እውጭ ያለውን ተቃዋሚ ሃይል ማጠናከር ማለት ነው። ባለበት ቢቆይ ለራሱም ይሁን ለቤተሰቡ ደህንነት እንጂ ጉዳት የለውም። የዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ሃይል የበለጠ በጎረቤት ሃገር ማደራጀት ይሆናል። ሁላችንም የሃገራችንን ደህንነት እንፈልገዋለን። ሰላምም እንመኛለን።

    Reply
  2. Tadesse says

    January 22, 2018 03:33 pm at 3:33 pm

    Be honest,why should any one suffer for any thing,ye eskendir Nega ke esir melekek manenm aygodam,bezi yetegodanew beteley egna le netsanet yemnwagaw Tigrewoch nen,netsanet le zelealem.

    Reply
  3. Tadesse says

    January 22, 2018 04:03 pm at 4:03 pm

    I am so deeply sorry for what is done in the name of the people of Tigray.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule