• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምነው ደም ደም አይለን?

June 8, 2018 05:11 am by Editor 1 Comment

ፍትህ ሳያደርቀው የፈሰሰን ፍዳ፣
ንስሀ ሳያጥበው የቆሸሸን ጓዳ፣
ዱለትን መቋደስ ከገዳዮች ጋራ፣
የሐጥያትም ሐጥያት የታሪክም ዕዳ!

ፍትህ ነፃነትን መብትን ተርበው፣
ኢፍታዊነትን እንደ አውሬ ተናንቀው፣
ስንቶቹ ተሰው ባሩድ ተመግበው?

ነፃነት ወይም ሞት በቃ ዘራፍ ብለው፣
ስንቶች ተሰውልን ጫካ ዱር ሸፍተው?

በእሬቻ በጥምቀት በመስጊድ ሰገዳው፣
በሰፈር መንደሩ በገጠር ከተማው፣
እንደ ፋሲካ በግ የታረደ ስንት ነው?

ባዶ ስድስት ጉድጓድ በጪስ የታፈነው፣
ቃሊቲ ዓለም በቃኝ የተዘቀዘቀው፣
ቅሊንጦና ዝዋይ በእሳት የነደደው፣
ሽሮሜዳ ታስሮ ጥፍሩ የወለቀው፣
ብር ሸለቆ አዘዞ ጉረኖ የገባው፣
ማሰቃያ ቦታው ጭራሽ ያልታወቀው፣
ስንት መከረኛ ምን ያህል ዜጋ ነው?

የጋንቤላን ምድር ሽፍን ያደረገው፣
ኦጋዴን በርሃን በጎርፍ የጠረገው፣
ምን ያህል ሬሳ ስንት በርሜል ደም ነው?

ጎንደር ደብረታቦር በባሩድ ያለቀው፣
ባህርዳር ወልድያ ስናይፐር የፈጀው፣
አምቦ ደብረ ዘይት ጥይት ያረገፈው፣
መች ተቆጥሮ ያልቃል ቆጣሪ ቢኖረው?

በሽሽት በስደት በአውሬ የተበላው፣
ባህርን ሲሻገር ድንብልዝ ያሰመጠው፣
ምን ያህል ኮረዳ ምን ያህል ጎበዝ ነው?

ወልቃይት ራያ ዘሩ የመከነው፣
በደኖ በገደል የተወረወረው፣
አሶሳ መተከል የተቆራረጠው፣
ከፋ ኢሉባቦር ሜጫ የከተፈው፣
አይምሯችን ያስላ ምን ያህል ሕዝብ ነው?

ይኸ ግፍ ሲፈጠም ለካስ ያለቀስነው፣
እርሾና አብሲት ጥለን በትኩስ ደማቸው፣
በተሰውት አጥንት ዳቦ ልንጋግር ነው፡፡

ጅቦቹ ሰው በሉ ስንል የነበረው፣
ለካስ የውሻ ጠጉር ካባ ደርበን ነው፣
ትርፍራፊ ልፋጭ መጎተት አምሮን ነው፡፡

በየ አደባባዩ ስንጮህ የነበርነው፣
ለካስ በሙታን ደም ገንፎ ልንሰራ ነው፡፡

አይ ጊዜ ፈታኙ አይ ጊዜ መስካሪው፣
ስንቱን አጭበርባሪ ከርሳም አጋለጥከው፡፡

በእርቅና በሰላም እያመካኘ፣
ስንቱ ይሁዳ ሰው ለሰይጣን ሰገደ፡፡

ዓለም ፍርደ-ገምድል ዓለም ወለወልዳ፣
ቀጣፊን አጽዳቂ ሐቀኛን ኮንና፡፡

በእርቅና በሰላም ስንት ሆዳም ነገደ፣
የሰማእት እሬሳ እየተራመደ፡፡

የሰማእት ሥጋ ቅርጫ ለመቃረጥ፣
በሙታንም አጥንት ንግድ ቤት ለመክፈት፣
ከገዳዮች ጋራ አብረን ስንዶልት፣
ምነው ደም ደም አይለን? ምነው አይለን ስቅጥጥ?

ገዳይ ችሎት ሳይቀርብ ሟችም ሳያገኝ ፍርድ፣
ፍትህ ገደል ገብታ ንስሃ እንጦሮጦስ፣
እርምን ልንጠሸቅም ከገዳይ ስንቀርብ ማድ፣
ምነው ደም ደም አይለን? ምነው አይሰቀጥጥ?

ሥጋውን እንጀራ ደሙንም ሰርተን ወጥ፣
እየሸመለልን ሰማእት ልንውጥ፣
ከነፍሰ በላዎች አብረን ስንቀመጥ፣
ምነው ደም ደም አይለን? ምነው አይለን ስቅጥጥ?

ይገርማል! ሰው ከንቱ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ሰኔ ሁለት ሺ አስር ዓ.ም.

 

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. እውነቱ ይነገር says

    June 18, 2018 05:05 pm at 5:05 pm

    ወገኔ አቶ በላይነህ

    I would like to say thank you for your message. Please keep it up!

    ጥያቄ አለኝ???

    እውነተኛና ግልጽ መልስ ያለው ሰው በመረጃ አስደግፎ ይመልስልኝ!

    1)የኢትዮጵያውያን ዓይኖች መቼ ነው እንባቸው የሚደርቀው/የሚታበሰው?

    2)እየተባባሰ ለመጣው ለኢትዮጵያውያን የዘመናት እንባ ምክንያቱ/ምንጩ በእውነት ምንድነው?

    3)የውጭ ሃገር ወራሪ ጠላት ያላስለቀሰን እኛ ኢትዮጵያውያንን ለምንድነው የራሳችን ወገኖች የደም እንባ እንድናነባ የሚያደርጉን????

    4)አማራው በእውነት በተናጠል ኢትዮጵያንን በሙሉ በማን አለብኝነት ረግጦ በገፍ ገዝቷልን????

    5)በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በእውነት አንዱ ብሔረ ሰብ በሌላው ብሔረ ሰብ ሆነ ብሎ በደል ሠርቷል ወይስ እንደ ማንኛውም ሃገር የሕብረተሰብ እድገት-ታሪክ ሃይልና ጉልበት ያገኘው ጎሳና ሰፈርተኛ በነበረው ንቃተ ህሊና ላይ ተመስርቶ በሚፈጠር ግጭት የመጣ ማንነት ላይ የተመሰረተ ታሪክ?

    6)የሸዋ መሳፍንት ታሪክ ሲጠና ስንቱ አማራ ስንቱ ደግሞ ኦሮሞ እንደነበረ እስቲ በዳታ አስረዱኝ???

    7)በሃይለ ስላሴ፣ በደርግና በወያኔ መንግሥት ዘመናት ወቅት አመራር ላይ የነበረውን አካል በብሔረሰብ ደረጃ በመረጃ አስደግፋችሁ/አሁን ዛመኑ የመረጃ ጊዜ ስለሆነና በአሉባልታና በወሬ ወለደ ወሬ ይህን ትውልድ ማታለል ስለማይቻል/ እስቲ ንገሩን???

    ሁሉም የዘራውን ስለሚያጭድ እንጠንቀቅ?
    ወንድምን ከወንድሙ ጋር ማጋጨቱ ይብቃ?
    እውነት ነጻ ያወጣልና በጋራ
    ለእውነተኛ የጋራ ሃገርና
    መልካም ሥራ በእውነት እንነሳ?

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር
    ሕዝባችንን ማስተዋል ይስጥልን!
    አሜን።

    እውነቱ ይነገር
    ከለሁበት

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule