(ለመቶኛው የኖቤል የሰላም ሎሬት ለ ዶ/ር ዐብይ አህመድ)
የሰው ዘር የምንጭ ህይወት - የዘመናት ታሪክ እናት፣
የነጻነት ቀንዲል ብርሃን - ያለም ማማ የእግዚአብሔር ቤት፤
የመለኮት ምስጢራቱ - ቅድስት አገር ኢትዮጵያ፣
መከራዋን አሸንፋ - ባለም ታየች ሃሌሉያ!
... ከበሻሻ መደብ - አልጋ የተነሳው ብላቴና፣
ቀጭን መንገድ በድክ ድክ - ውጣ-ውረድ.. አለፈና፣
በሰንበሌጥ ተመስሎ - ጎርፉን አልፎ ለጥ ብሎ፣
አሳር፣ ችግር፣ ሞትን ከድቶ - በተዐምር ህይወት ዘርቶ፣
ካለም ጫፍ ላይ በድል ታየ - የክብር አክሊል ወርቁን ደፍቶ።
ያገር አድባር ግዙፍ ዋርካ፣
ስኬት ተስፋው እሚለካ፣
የይቻላል ትምህርት ቤት - ለትውልዱ አርአያ፣
ክብር ኩራት ለናት አገር ለእምዬ ለኢትዮጵያ!
ጌታቸው አበራ
ህዳር 1912 ዓ/ም
(ዲሴምበር 2019)
Leave a Reply