ተጠርጣሪዎቹ ሽፈራው ጃርሶ የሚመሩት ቦርድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ናቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ከእነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች 15 የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ፍለጋ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥና የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ ባልተከተለ መንገድ ኪራይ ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን፣ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባካሄደው ጥናታዊ ምርመራ በዚህ የሙስና ወንጀል መንግሥትን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዳሳጣው ለጉዳዩ ቅርበት የኮሚሽኑ ምንጮች … [Read more...] about በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
News
ዜና
ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
አጠገብ ያሉ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ እንዲለቁ ተነገራቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ለማድረግ ስምምነት ሊያደርግ ነው በግዙፉ የጀሞ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች መንደር ውስጥ በአንድ በኩል በመስመጥ ላይ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሕንፃ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሕንፃው እንዲለቁ ተነገራቸው፡፡ በሁለቱ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሕንፃዎቹ እንዲለቁ የተጠየቁት በክፍለ ከተማው የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት አማካይነት መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የውሳኔው መነሻ ወደ አንድ ጐን በማዘንበል ላይ የሚገኘው ሕንፃ አጠገብ ያሉት ሁለት ሕንፃዎች ተመሳሳይ ችግር አለባቸው በሚል ቢሆንም፣ በሕንፃዎቹ ላይ በዓይን የሚታይ ችግር መኖሩን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ሕንፃዎች ተመሳሳይ መሰነጣጠቅ በውስጥ አካላቸው … [Read more...] about ግዙፉ የጀሞ ኮንዶሚኒየም ዘምሟል
በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!
ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ረቡዕ ለት በጭንቅ እንዲያርፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ አደጋው ከአምስት ደቂቃ በፊት ቢከሰት ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡ 78 መንገደኞችንና ሠራተኞችን አሣፍሮ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Bombardier Q400) አውሮፕላን ከክንፎቹ በአንዱ ጭስ መነሣቱን የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ በመደወሉ እጅግ አስጨናቂ በሆነ መልኩ እንዲያርፍ መደረጉን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው ስማቸው ከመግለጽ የተቆጠቡ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደጻፈው አውሮፕላኑ ከማረፉ ከአንድ ደቂቃ በፊት የግራው ክንፍ እየጨሰ መሆኑን ማስጠንቀቂያው ማመልከቱንና አንዱ ሞተር ደግሞ እንደሚገባው ይሰራ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በስልክ ያነጋገራቸው ተሳፋሪ ጭስ … [Read more...] about በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!
ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ
ኢህአዴግ ለሚገዛት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ የሚሠጠው የዓለም ባንክ፤ ለዕርዳታና ልማት የሚልከው ገንዘብ ኢህአዴግ የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ለመጣስ ተጠቅሞበታል በሚል ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ፡፡ የባንኩ ውሳኔ ኢህአዴግን የማነቂያው ገመድ እንደሚያከረው ተገለጸ፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል በሰጡት መግለጫ “ይህ በጥናት ከምናካሂደው ትግል አንዱ ውጤት ነው፤ ገና ጅማሬ ነው፤ ጠንክረን እንሠራለን” አሉ፡፡ የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ ውሏል በሚል ከዚህ በፊት ክስ ቀርቦበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጉዳዩን ከ9 ወራት በፊት በዘገበበት ወቅት ተጠቂዎቹ ዜጎች ያቀረቡትን ማስረጃና … [Read more...] about ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ
ቤተልሔም ፕላዛና ደብረወርቅ ታወር አገልግሎት እንዳይሠጡ ተከለከሉ
(ከጎልጉል አዘጋጅ - ለመስታወቱ ብቻ ቤተልሔም 9ሚሊዮን ብር ደብረወርቅ ደግሞ ከ15ሚሊዮን ብር በላይ አውጥተው እዚህ እስኪደርስ ድረስ የከንቲባ ኩማ መስተዳድር የት ነበር? ላዲሱ ከንቲባ ድሪባ የከተማውን ቁልፍ ሲያስረክብ ይሆን?) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ የሆናቸው ሁለት ሕንፃዎች ደረጃቸውን አልጠበቁም በሚል ምክንያት የመጠቀሚያ ፈቃድ ከለከላቸው፡፡ሁለቱ ሕንፃዎች መገናኛ ድልድይ አካባቢ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛና ሜክሲኮ አካባቢ ከቡናና ሻይ ሕንፃ ፊት ለፊት የሚገኘው ደብረ ወርቅ ታወር ናቸው፡፡ ሁለቱ ሕንፃዎች የተጠቀሙበት የውጭ መስታወት አንፀባራቂ ነው በሚል ምክንያት አስተዳደሩ መስታወታቸው እንዲነሳ ማዘዙ ታውቋል፡፡ መገናኛ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛ ባለ ሰባት ፎቅ ነው፡፡ ያረፈው በ800 ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ … [Read more...] about ቤተልሔም ፕላዛና ደብረወርቅ ታወር አገልግሎት እንዳይሠጡ ተከለከሉ
ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ማስፈጸም አይችልም
“ዕድገት”፣ “ትራንስፎርሜሽን”፣ “ህዳሴ”፣ “የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)”፣ … በሚመሯት ኢትዮጵያ ሙስና እየከፋ መሄዱ ታወቀ፤ ከመቶ ሰዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ጉቦ የሚሰጡ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡ ሰሞኑን ዓለምአቀፉ የግልጽነት ድርጅት (Transparency International) ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ የአፍሪካ አገራት በሙስና “መበስበሳቸውን” ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ አገራት መካከል እንደምትገኝ ዘግቧል፡፡ ከዚህ በፊት በያዝነው ዓመት ጥር ወር የሙስና አደጋ የተጋረጠባቸው አገራትን ዝርዝርና የአደጋውን መጠን በሰባት ደረጃ በመከፋፈል ይኸው ድርጅት ባወጣበት ጊዜ ኢትዮጵያን በከፍተኛ የሙስና አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት ዝርዝር ውስጥ አስገብቷት ነበር፡፡ በዚህ ዘገባ መሠረት በሙስና የተዘፈቁትን አገራት በመከፋፈል ባስቀመጠው ባለዘጠኝ መዘርዝር … [Read more...] about ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ማስፈጸም አይችልም
በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?
ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ"ከፍተኛ" ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር "ምንጮቼ ነገሩኝ" በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ "ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች" በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም። ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው "በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት … [Read more...] about በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?
ከእሁድ እስከ እሁድ
አልሸባብ በሶማሊያ ተሽመደመደ፤ ሼኽ ዳሒር ሃዌስ ተይዘዋል፤ አሸባሪነትን በመዋጋት ሲሞዳሞዱ የቆዩት ኢትዮጵያና አሜሪካ ወዴት ያመሩ ይሆን? የአልሸባብ መሪዎች በራሳቸው ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ። ከተገደሉት መካከል አንደኛው ያሉበትን ለጠቆመና ላጋለጠ አምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ የታወጀባቸው ነበር። የቪኦኤ የአማርኛው ክፍል በዘገበው ዜና መሰረት አልሸባብ በሶማሊያ እየተንኮታኮተ የመክሰም ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች ይመስላል። አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ አባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሲያውል፣ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ያሉ ነበሩ ብሏል። “ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር … [Read more...] about ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች በሪያድ "ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች" የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም። ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ … [Read more...] about አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች