• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች

February 8, 2014 03:26 am by Editor 5 Comments

በዓለማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማወዳደር ደረጃ የሚያወጣው (4 International Colleges & Universities (4icu)) የአፍሪካ ምርጥ የተባሉትን ዩኒቨርሲቲዎችን ዝርዝር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ ነበር፡፡ ድርጅቱ በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ለማንም ወገን ያላዳላ ጠለቅ ያለ ሒሳባዊ ትንታኔ በማድረግ ደረጃውን እንደሚያወጣ በድረገጹ ላይ ጠቁሟል፡፡

ከአንድ እስከ ሃያ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የደቡብ አፍሪካና የግብጽ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃውን በብዛት ተቀራምተውታል፡፡ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ቦትስዋና እና ኬኒያ እስከ ሃያ ባለው ደረጃ በመግባት የአገራቸውን የትምህርት ተቋማት ብቃት አስመስክረዋል፡፡

ከተመሠረተ 60ዓመታት ያለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ ስሙ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ) እስከ መቶ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የ53ኛ “ክብር” ተጎናጽፎዋል፡፡ ከተመሠረቱ ጥቂት ዓመታት በሆናቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተበልጦ ለዚህ የበቃው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀደምት ዓመታት የበርካታ አፍሪካውያን ኩራት ነበር፡፡

ህወሃት/ኢህአዴግ ሎሌዎቹን ከየቦታው ሰብስቦ ሥልጣን በያዘ ማግስት መጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስተማረቻቸውን 42 ምሁራን በሁለት መስመር ደብዳቤ ማባረር ነበር፡፡ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ዶ/ር ዱሪ መሐመድ ያባረሯቸው እነዚህ ምርጥ ምሁራን እንደ ምሁርነታቸው በነጻ በማሰባቸውና ተማሪዎችንም እንደዚያው እንዲያስቡ በማድረጋቸው እንጂ በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው ተፈላጊ ባለመሆናቸው እንዳልነበር የታወቀ ነው፡፡

ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በየቦታው የፈለፈላቸው የካድሬ ማምረቻ “ዩኒቨርሲቲዎች” ስሙን ከመያዝ በስተቀር እስከ 100 ባሉት ዝርዝር አንዳቸውም ለመገኘት አለመብቃታቸው የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ ነው፡፡

በ1963 ዓም ምረቃ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አክሊሉ
በ1963 ዓም ምረቃ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አክሊሉ

“ስንዋጋ ከረምን፣ በረሃ መድፍ ስናገላብጥ ነበር፣ … እያሉ የሚምሉት የወያኔ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ሲገቡ ከመለስ ጀምሮ በብርሃን ፍጥነት የከፍተኛ ዲግሪ ባለቤቶች ሆኑ፡፡ ከዚያም አልፎ በበርካታ ዓመታት ከፍተኛ ጥናትና ምርምር የሚገኘው የፒኤችዲ ዲግሪ ሲሻቸው “በክብር” ካልሆነም “አገር እያስተዳደሩ ከምትተርፋቸው ጥቂት ጊዜ በመቆጠብ” እየተምነሸነሹበት ነው” በማለት የምሬት አስተያየታቸውን አንድ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቅ ይገልጻሉ፡፡ የሚያስመርቁትን ተማሪ ሥራ ማስያዝ ሲያቅታቸው ደግሞ “ኮብል ስቶን” የማንጠፍ ዲግሪ ነው የሰጠናችሁ በማለት የድንጋይ አንጣፊነት “የሥራ ዕድል” መክፈታቸውን በአደባባይ ይለፍፋሉ ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ሆነ ከሌሎች በየመንደሩ ከተፈለፈሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረተው ተመራቂ ለካድሬነትና ለሆዱ እንዲያድር የሚደረግ መሆኑ በተመራቂዎቹ “የእውቀት ጥራት” እየታየ ነው፡፡ ሰሞኑን የወጣው የ“4icu” ደረጃ መለኪያም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

በአሜሪካ በሚገኝ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሥራ እያከናውኑ የሚገኙ አንድ ኢትዮጵያዊ ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ፤ “እኔ ባለሁበት ዩኒቨርሲቲ በርካታ ነጻ የትምህርት ዕድሎች ይመጣሉ፤ አብረውኝ ያሉ መምህራንም ካገርህ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ወገኖችህን ጋብዝ ይሉኛል፡፡ አብዛኛዎቹ ዕድሉን የምልክላቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ቢሆኑም በቅጡ የማመልከቻ ፎርም ለመሙላት በጣም የሚቸገሩ፣ እንግሊዝኛ በትክክል አሳክተው አንድ አንቀጽ የማመልከቻ ደብዳቤ መጻፍ በጣም የሚቸግራቸው ሆነው በማግኘቴ በተደጋጋሚ አንገቴን ደፍቻለሁ” ብለዋል፡፡ ውድድሩ ለከፍተኛ ትምህርት በመሆኑ መሠረታዊ የሚባሉትን መስፈርቶች ማሟላት የግድ እንደሆነ የጠቀሱት እኚሁ ሰው፤ አሁንም ግን ተስፋ እንዳልቆረጡና በየጊዜው እንደሚሞክሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ልጆች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተከፈለላቸው በአውሮጳና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ይሰማራሉ፡፡ ዓላማው ወደፊት አማራጭ በሌለው መልኩ ከኢትዮጵያ ልጆች አብላጫውን ይዞ በመገኘት የማንኛውንም ክፍለኢኮኖሚና አመራር ለመቆጣጠር ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው ሌላው የበይ ተመልካች ሆኖ ዕድሜ ልኩን ይኖራል በሚል አስተሳሰብ እንደሆነ የትግራይ ነጻ አውጪው ህወሃት ዕቅድ ነው፡፡

ለህወሃት አሽከር በመሆን ታላቅ “ሹመት” ያገኙትና በቅርቡ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የተሰጣቸው የቀድሞ ትምህርት ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዚህ የከፍተኛ ተቋማት መለኪያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለዚህ “ክብር” ማብቃታቸው ሌላ “ዲግሪ” እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ነው በማለት በአውሮጳ የሚገኙ ሌላ ምሁር ሃዘናቸውን በምጸት ገልጸዋል፡፡ አቶ መለስ በአንድ ወቅት ማሃይምም ቢሆን የኢህአዴግን አቋም እስከተከተለ ድረስ ለሚኒስትርነት እንሾማለን ማለታቸው ለትምህርት ያላቸውን ጥላቻ ብቻ ሳይሆን በካድሬዎቻቸው “ሊቁ፣ ምሁሩ፣ …” ተብለው ቢጠሩም መለስ አላቸው የተባለው ዕውቀት በሙሉ ጥራዝ ነጠቅና ከአፍ ብልጠት የማያልፍ ዕውቀት ብቻ እንደነበር ደጋግሞ ያስመሰከረ ነው፤ ውጤቱን ይኸው እያየነው ነው በማለት እኚሁ ሰው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በቅርቡ ከዕንቁ መጽሔት ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ዩኒቨርሲቲው 53ኛ መውጣቱ “ይገባዋል” የሚያሰኝ ደረጃ ደጋፊ ሃሳብ መሰንዘራቸው ይታወቃል፡፡ በቃለምልልሱ ዶ/ር ዳኛቸው ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር፡- “ዩኒቨርሲቲ ከሕዝብም ሆነ ከፖለቲካ አመራሩ ክፍል የሚመጣ ሃሳብ የሚፈትሽበት፤ ለማኅበረሰቡም ሆነ ለአስተዳደር ክፍሉ ገንቢ አስተያየቶችንና አመለካከቶችን የሚቀርቡበት ተቋም ነው፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በተገላቢጦሹ ሃሳብና ምክር ይፈልቅበታል በሚባለው ተቋም ሹመኞች በተለያየ ምክንያት እየመጡ አስተማሪዎችን እየሰበሰቡ የሃሳብና የምክር አቅራቢነት ሚና መጫወታቸው በጣም ያስገርማል፡፡ በተለያየ ጊዜ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን እየሰበሰቡ ከኃይማኖት እስከ ልማት፣ ከዕድገት እስከ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ … ወዘተ “አሰልጣኞች” ተመድበው “ሥልጠና” ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ይህን ጉዳይ ይበልጥ ለማብራራት በቅርቡ አቶ ብርሃኑ አስረስ ከጻፉት መጽሐፍ መጥቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡ ከታህሳሱ ግርግር በኋላ ጀኔራል መንግሥቱ ነዋይ ተይዘው ፍርድቤት በቀረበቡበት ወቅት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ “የተናቀ መንደር ‘በምንትስ’ ይወረራል” ብለው የተረቱት ተረት ሁኔታውን በሚገባ የሚገልጸው ይመስለኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ሠልጣኝ የመንግሥት ሹመኞች አሰልጣኝ የሆኑበት ግቢ ሆኗል፡፡”


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Editor says

    February 10, 2014 07:20 am at 7:20 am

    የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ 53ኛ ነው!

    “የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ – 53ኛ!” በሚል ርዕስ ላተምነው ዜና የተለያዩ አስተያየቶች በፌስቡክ ገጻችን ላይ ተሰጥተውበታል፡፡ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያገኘው ከራሱ ከድርጅቱ ድረገጽ መሆኑን በግልጽ ለማስረዳት ይፈልጋል፡፡

    በቀጥታ ከድርጅቱ ድረገጽ የተገኘው መረጃው እዚህ ላይ ይገኛል፡፡

    ድርጅቱ ዓመታዊ የደረጃ ዘገባ የሚያወጣው ዓመቱ ሲያልቅና በዓመቱ አጋማሽ ላይ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ዓመታዊም ሆነ የመንፈቅ ሪፖርት ሲወጣ ሪፖርቱ እስከወጣበት ቀን ወይም ወር ድረስ ያለውን የማያካትት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሰኔ ላይ የተዘጋ የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ሐምሌ ወይም ነሐሴ ቢወጣ ሪፖርቱ የሐምሌንና የነሐሴን መረጃ የማይጠቀልል እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ የሰፈረው መረጃ በሁለቱ ሪፖርቱ ባላካተታቸው ወራት እየተፈጸመ ካለው ጋር ፍጹም የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ የሁለቱ ወራት መረጃዎች ከሌሎች ወራት ጋር ተቀናብረው በመጪው ዓመት ሪፖርት ውስጥ ይካተታሉ፡፡

    የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃም ሆነ የኮሌጅ ትምህርት የወሰደ እንዲሁም ፌስቡክ መጠቀም የሚያው በሙሉ ወ/ሮ ስርጉትን ጨምሮ ይህን ይገነዘባል በሚል እሳቤ ዜናውን ስናትም ሪፖርቱ የ2013 መሆኑን በግልጽ አለመጥቀሳችን ስህተት የሚያስብል ከሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ አሁን በድረገጹ ላይ የሚታየው የ32ኛ ደረጃ ድረገጹ በየወሩ ደረጃውን “update” ከማድረግ አሠራሩ ጋር የተያያዘ እንጂ የመጨረሻና በማስረጃ መልክ የሚጠቀስ ደረጃ አይደለም፡፡ የሚቀጥለው ወር ደረጃው ሊቀየር ይችላል፡፡ በየወሩ የሚከሰተው ከፍና ዝቅ ማለት አንድ ላይ ተሰብስቦ የመጨረሻው ሪፖርት በማስረጃነት ሲወጣ የዩኒቨርሲቲው ደረጃ ይህ ነው ይባላል፡፡

    ይህንን የ53ኛ ደረጃ እኛ የዘገብነው ብቻ ሳይሆን The African Economist በድረገጹና ፌስቡክ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

    ከዚህ ያለፈ መረጃ የሚፈልጉ ሁሉ የሪፖርቱ ባለቤት የሆነውን (4 International Colleges & Universities – 4icu) በደብዳቤ፣ በኢሜይል. በፋክስ፣ በፌስቡክ፣ በእግር፣ በግምባር፣ … መጠየቅ ይችላሉ፡፡

    ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ

    Reply
  2. aradaw says

    February 10, 2014 09:13 pm at 9:13 pm

    One thing at-least Meles Zenawi has a chance to to attend the dinning hall for two years. This is a big achievement for TPLF.

    Reply
  3. jarso says

    February 11, 2014 08:47 pm at 8:47 pm

    It is not heart breaking news for Ethiopians who knows well the quality of education provided
    currently in Ethiopian schools and fake universities . In fact all universities that have been established by woyane are ‘white elephants” to be used to hood wink donor organizations in a bid to paint self image and draw more funds to fatten their pocket in the name of Education. How come bunch of illiterate woyane who have no the slightest appreciation expect to build universities that produces inquisitive citizens which run counter against the rock headed woyane mafiosos?Thus it is not wondering not to see Ethiopian barn universities being not rated even within the 100 best universities. But it would have been a disgrace for 4icu, if the woyane thrash universities had been included in the number. Be that as it may the Addis Abeba university deserves to be in that line up thanks , at least,for Haile Selassie.

    Reply
  4. temesgen mera says

    February 14, 2014 02:38 pm at 2:38 pm

    I thank to God by this exact infomation.

    Reply
  5. MF says

    March 3, 2014 09:29 am at 9:29 am

    Oh my country, where r u going?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule