ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የደቡብ ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከኬኒያው ቴሌቪዥን KTN ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሳልቫ ኪር እና ሬክ ማቻርን ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ ናቸው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በትጥቅ ትግሉ ወቅት በረሃ እንደነበሩበት ሁኔታ በነጻ አውጪ አእምሮ አገር መምራት የለባቸውም በማለት ወቅሰዋል፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያለ በዘር እና ጎሣ ላይ የተመሠረተ አገዛዝን ተግባራዊ ያደረገ ቡድን ለደቡብ ሱዳን የዘርና ጎሣ ችግር መፍትሔ ማምጣት አይችልም፤ በአገዛዝ ላይ ያሉት የህወሃት/ኢህአዴግ መሪዎችም ሆኑ የዑጋንዳውን መሪ በአምባገነንነት ከ20 ዓመታት በላይ በሥልጣን የቆዩ በመሆናቸው ለሳልቫ ኪር አምባገነናዊነትን ያስተማሩና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መሸምገል የሚችሉ አይደሉም ብለዋቸዋል፡፡ በውይይቱ ላይ በኬኒያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ተገኝተዋል፡፡ (ውይይቱን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ)
ayalew says
Congratulation, it was a remarkable conversation not only about RSS but Ethnic conflicts in Africa.
Thank you
Ayalew