በቅርቡ በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተከበረውን የአባይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በዓል አሰመልክቶ ኤምባሲው በጠራው ስብሰባ ላይ ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዳይገኙ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ባስተላለፉት ቀጭን ትዕዛዝ አዛውንቱ በአሸባሪነት ተፈርጀው በአሉን እንዳይታደሙ መታገዳቸው ሪያድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፈተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። በተለይ ሰሞኑን ውስጥ ወስጡን ሲነገር የነበረው የአምባሳደሩ መሃመድ ሃሰን ነውረኝነት ተግባር አርብ ሜይ 9 2014 ምሸት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ውስጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ በተዘጋጀ የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ አንድ የሃይማኖት አባት ሪያድ ከተማ ውስጥ መኖር … [Read more...] about በሪያድ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች “አሸባሪ” መባላቸው ተቃውሞ አስነሳ
News
ዜና
“ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ
በቅርቡ በግብጽ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ እየተባለ የሚጠበቁት ዕጩ ተወዳዳሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ሲሉ ገለጹ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ በውጭ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “በማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስረዱ፡፡ በግብጽ በተላለፈ የቴቪ ስርጭት ትላንት ቃለመጠይቅ የሰጡት የቀድሞው የግብጽ ጦር መሪ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ ግድቡን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና እንዳልሰጡ አልሃራም የቲቪ ስርጭቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሆኖም ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ … [Read more...] about “ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ
ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው
በአምቦ ህዝብ አዝኗል። የሟቾች ቁጥር ከ22 በላይ እንደሆነ ይገመታል። በድፍን ኦሮሚያ ከ36 ሰዎች በላይ ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች አሉ። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ 11 ሰዎች መሞታቸውን አምኗል። ታዛቢዎች እንደሚሉት ኦሮሚያ እያነባች ነው። ህዝብ ለቅሶ ከተቀመጠ በኋላ ኢህአዴግ በቴሌቪዥን ቅስቀሳ ጀመረ። አርብ ሚያዚያ 24፤2006 (2/05/2014) ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ባሰራጩት መረጃ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝብ ሃሳቡን እንደሚጠየቅ አመላክተዋል። የዚሁ መነሻ እንደሆነ የተነገረለት የቅስቀሳ ዘመቻ ዛሬ በቴሌቪዥን ተላልፏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኩማ የድንበር ጉዳይ እንደማይነሳ በመጥቀስ ተቃዋሚዎችን ወቅሰዋል። ኦሮሚያን ልዩ ዞን ከአዲስ አበባ ጋር ያዋሀደው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በክልሉ ከተካሄዱት ሰላማዊ የተቃውሞ … [Read more...] about ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው
በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት በሞከሩና ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰልፍ በወጡ ወገኖች ላይ አገዛዙ የ"ከፋ" ነው የተባለ ሃይል መጠቀሙ ተሰማ። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ታስረዋል። ለተቃውሞ መነሻ በሆነው አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ኦህአዴድ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አልቻለም። ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያልቻለው ኢህአዴግ ጉልበት መምረጡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የተከማቸ ብሶቶች ጋር ተዳምሮ አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል የሚል ስጋት አለ። ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ … [Read more...] about በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው "ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም" ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው "ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ" በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች "አገር በማተራመስ" ወንጀል ክስ መሰረተባቸው። የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። … [Read more...] about ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?
ዜጎች በጎጃም መሬቸውን እየተነጠቁ፤ በወለጋ ደግሞ እየተፈናቀሉ ነው!
አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው መራዊ፡- በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ያለ ፈቃዳችን መሬታቸውን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ አርሶ አደሮች እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በመራዊ አካባቢ ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ መንግስት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እናካሂዳለን በሚል ከ400 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው እንዲለቁ የተደረገውን እርምጃ አርሶ አደሮቹ በመቃወማቸው እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ከአሁን ቀደም ተመሳሳይ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን የአርሶ አደሮቹ መሬት በአበባ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ወቅት መንግስት ውሃ ለመቆፈር በሚል አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸው እንዲለቁ የሚወስደው እርምጃ በተመሳሳይ ለአበባ … [Read more...] about ዜጎች በጎጃም መሬቸውን እየተነጠቁ፤ በወለጋ ደግሞ እየተፈናቀሉ ነው!
የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል
ሃያ አምስት በመቶ እንደተጠናቀቀ የሚነገርለት የ“ህዳሴው” ግድብ በኢትዮያና በግብጽ መካከል ከፈጠረው የፖለቲካ ቁርቋሶ በተጨማሪ ወደ ሃይማኖት መንደርም እየዘለቀ ነው፡፡ ዛሬ (አርብ) ግብጽን ለመጎብኘት ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አቡነ ማቲያስ ከግብጽ በኩል እንዳይመጡ በተላለፈላቸው መልዕክት መሠረት ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡ በግብጽና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተለያዩ የዜና ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ መልዕክቱ ያስተላለፉት የግብጹ ፓትሪያርክ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ ናቸው፡፡ ፓትሪያርኩ ለአቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት በበርካታ ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የአባይ ግድብ የፈጠረው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ይህንን ጉብኝት ማካሄድ የግብጽን ቤ/ክ “የሚያሳፍር” ይሆናል በሚል ነው ምክራቸውን ለአቡነ ማቲያስ የለገሱት፡፡ ስማቸውን ሳይጠቅሱ መረጃውን ለግብጽ የሚዲያ … [Read more...] about የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
የትምህርት ሚኒስትር በ2006 ዓ.ም በአገሪቱ በተፈጠረው የመምህራን እጥረት ምክንያት በተለ ያዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ኢትዮጵያውያንን ለአንድ አመት ሙሉ ወጫቸውን ችሎ የማስተማር ስነ ዘዴ (ፔዳጎጅ) በማስተማር ወደ መምህርነት እንዲገቡ ማስታ ወቂያ ያወጣል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረ ትም ለማጣሪያነት የቀረበውን ፈተና በመፈተን መልምሎ ለስልጠና እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት በ10 ዩኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ) እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡ ይህ ስልጠና እየተካሄደ ባለበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ሙሉ ወጫቸ ውን መንግስት እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር የመጡት፡፡ በዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ የተደለ ደሉት 330 ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ተማሪዎቹ ቃል በተገባላቸው መሰረት … [Read more...] about የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
ይህንን ምን እንበለው? ኢህአዴግ እስካሁን ያለው ነገር የለም
"መኖሬን ጠላሁት። ራሴን እንዳልገድል ወንጀል ነው። ሰው እንዳልገድል ወንጀል ነው" በሚል ግራ መጋባት አንድ አዛውንት ይናገራሉ። ተበዳዮች ከእርሻ ስራ በኋላ የሚይዙትን በትር ፖሊስ ሰበሰበ። ከዚያም እገበያ ቦታ ላይ ገጀራና ጦር የያዙ ጎረምሶች እየጮሁ ጥቃት መፈጸም ጀመሩ። 16 ሰዎች፣ 26 ናቸው የሚሉ አሉ ጉዳት ደረሰባቸው። አንድ ሰው ተገደሉ። ይህ ዜና የተወሰደው ተበዳዮች ራሳቸው ባንደበታቸው ሲናገሩ ከሚታዩበት ቪዲዮ ነው። የተገደሉት አቶ ጌጡ ክብረት ይባላሉ። የሰባት ልጆች አባት ናቸው። የተገደሉት በገጀራ ነው። ከተገደሉ በሁዋላ አይናቸውን አውጥተዋቸዋል። አንደኛው ተናጋሪ አዛውንት እንደተናገሩት ደግሞ "ብልታቸውን ሸንሽነዋቸዋል"። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለህክምና ሲሄዱ "ሂድና አገርህ ታከም። ይህ የእኛ ሃኪም ቤት ነው" እንደተባሉ ምስክሮቹ ይናገራሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው … [Read more...] about ይህንን ምን እንበለው? ኢህአዴግ እስካሁን ያለው ነገር የለም
በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ
የኢህአዴግን የስለላ መዋቅርና አካሄድ አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ተበራክተዋል። ኢህአዴግ ራሱን እንደሚስለው ዓይነት ድርጅት ሳይሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉድለት ያለበት፣ በሚዲያ ነጻነት ኋላ ቀር፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በማሳደድ ግንባር ቀደም፣ አፋኝ ህግ በማውጣትና በማሸማቀቅ ወደር የማይገኝለት፣ ለሚያወጣው ህግና ደንብ የማይገዛ፣ የውስጥ ችግሩ ታይቶ በማይታወቅ መጠን ዜጎችን ለስደት እየዳረገ እንደሆነ እየተመሰከረበት ነው። ኢህአዴግን ሸሽተው አገር ለቀው የተሰደዱ በስደት ምድርም ኢህአዴግ እየተፈታተናቸው እንደሆነ መግለጽ ከሰነበቱ ቆይቷል። በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በጀርመን፣ በስዊድንና በእንግሊዝ አገር ስደተኞችን በመሰለል ተግባር ላይ የተሰማሩ “የስደተኛ ሰላዮች” በስፋት ስለመኖራቸው መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። የተለያዩ ድርጅቶች በዚህ … [Read more...] about በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ