• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ማቅረብ – የቴዲ ተስፋ!

December 28, 2017 11:55 pm by Editor 2 Comments

ለዓመታት በአገር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) እንዳያሳይ የታገደው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ለማቅረብ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ። ችግሮቻችንን አራግፈን ወደፊት መጓዝ አለብን ብሏል።

ዴይሊ ሜይል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ እንደዘገበው በእርሱ ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንዳለ ሆኖ ቴዲ “በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ” ትኩረት ማድረግ መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤቱ ዘና ባለ ሁኔታ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

የልጅነት ዘመኑን በማስታወስ ቴዲ ሲናገር፤ “ልጅ ሆኜ እንደ አንድ አገር ስንኖር አስታውሳለሁ፤ አንድ የምናውቃት አገር ኢትዮጵያ የምትባል ነበረች፤ አሁን በዚህ ዘመን ግን የምንታወቀው በዘራችን ነው፤ ይህ ደግሞ እጅግ አደገኛ እየሆነ መጥቷል” ብሏል።

ህወሓት በቴዲ የጥበብ ሥራዎች ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በተለይ ተደናቂነትን ያገኘው “ኢትዮጵያ” የተሰኘው አዲሱ አልበሙም ሆነ ቀደምት ሥራዎቹ እንደሌሎቹ ባለሙያዎች ህወሓት በተቆጣጠረው ሚዲያ ላይ አይሰሙም። አንዳንዶች ይህንን አስመልክተው ሲናገሩ፤ የቴዲ 17 መርፌ ሙዚቃም ይሁን እቴጌ ወይም ባልደራሱ ወይም ማር እስከ ጧፍ ሁሉም ህወሓትን ያስበረግጉታል።

“ጥቁር ሰው” የተሰኘው አልበሙ ህወሓት ከፈጠረው የዘር ፖለቲካ ጋር ተያይዞ በኦሮሞ ብሔረተኞች ዘንድ ስሙ እንዲጠለሽ ብዙ ተሠርቶበታል። እነ ጃዋር መሐመድ ያደረጉት የበቀል እርምጃ ከህወሓት እኩይ ተግባር ባልተናነሰ መልኩ የቴዲ ሥራ ለሕዝብ እንዳይቀርብ ብዙ እንቅፋትን ፈጥረው አልፈዋል። የቴዲ ኮንሰርት ስፖንሰር አድራጊ የነበረው ሃይኒከን ቢራ በዚህ ዘመቻ ምክንያት ራሱን ማግለሉ የሚታወስ ነው። (ይህንን አስመልክቶ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አትሞት የነበረውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)።

ቤቱ ግድግዳ ላይ በተሰቀለ የምኒልክ ጎራዴ አጠገብ ተቀምጦ ቴዲ ስለተካሄደበት ይህን መሰሉ ህገወጥ ዘመቻ ይህንን ይላል፤ “ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ቀደምት ነገሥታት አሉታዊ አመለካከት ያላቸው ቡድኖች ሊኖሩ ይችላሉ። አመለካከታቸውን ባከብርም የኔን አመለካከት መውደዳቸውም ወይም አለመውደዳቸው እውነቱን አይለውጠውም።”

በሙስሊምና ክርስቲያን መካከል ሰላምና ፍቅር፣ መግባባት እንዲኖር የሚያዜመው ቴዲ ከህወሓት ሌላ በርካታ ነቃፊና ስም አጥፊዎችም በዘመኑ አላጣም። በአድናቂዎቹ ሴቶች ጡት ላይ ይፈርማል በማለት ስለ እርሱ ሲናገሩ ለነበሩ የሰጠው ምላሽ በኢትዮጵያ በውጭ አድናቆትን እንዳተረፈለት ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ዓይነት ነገር ፈጽሞ ሊያደርገው እንደማይችል ነው ቴዲ የተናገረው። ይህንን በመደገፍ ይመስላል የአፍሮ ኤፍ ኤም ፕሮግራም ኃላፊ የሆነው ኢዮኤል ሰሎሞን “(ቴዲ) የሚሰብከው የሚኖረውን ነው፤ እኛ እንወደዋለን፤ ኢትዮጵያውያን ይወዱታል” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

“ኢትዮጵያ” አልበሙ የምረቃ ፕሮግራም የተቋረጠበት ቴዲ አፍሮ፤ ለአዲሱ ዓመት (2010) ያቀደው ኮንሰርትም ተከልክሏል። አሁንም ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ለገና ኮንሰርት ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ እንዲፀድቅለት እየጠበቀ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖ በሙያውና በሙዚቃው ስለ ኢትዮጵያ ከመሥራት ምንም እንደማያዳክመው ተናግሯል።

የቴዲ ምኞት እና ተስፋ ግን በዚህ ብቻ የተገታ አይደለም፤ እስከ አስመራ የዘለቀ ነው። እዚያ የሙዚቃ ድግስ ለማቅረብ ተስፋ ያደርጋል። “የሚያስፈልገን የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርባይነት መንፈስ ነው። ምክንያቱም አሁን ያሉት ችግሮች የታሪክ ቅሬታዎች ያመጧቸው ውጤቶች ናቸው። ልናራግፋቸው፤ ወደኋላ ትተናቸው ልንሄድ ይገባል” ይላል ቴዲ አፍሮ።

ዘገባው ከነፎቶው የተጠናቀረው ከዴይሊሜይል ድረገጽ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Social Tagged With: afro, eprdf, Ethiopia, Full Width Top, Middle Column, teddy, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    January 2, 2018 03:20 am at 3:20 am

    ሰዎች!! ቴዲ አፍሮ ስለ ኢትዮጵያዊነት ያትታል፣ ይዘፍናል፣ እኩልነትን አክሎበት ያውቃል?? ቴዲ ስለ ሀገሩ ለመስበክ ብዙ ይቀረዋል። ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!!

    Reply
    • ለጥይበሉ says

      January 11, 2018 12:20 am at 12:20 am

      ሙሉጌታ!! አንድ መሆን ከእኩልነት የሚልቅ ይመስለኛል። አንድ መሆን በውስጡ እኩልነትንም ይጨምራል። እንደሚገባኝ የቴዲም ሃሳብ ይኸው ነው፣ አንድ እንሁን። እኩልነት የሌለበት “ትክክለኛ አንድነት“ ሊኖር አይችልም። እኩልነት ከሌለ አንድነት የተባለው ነገር ውሸት ወይም ስም ብቻ ይሆናል። ቴዲ የአባትህ ስም እንደሚገባው ይሰማኛል። አንዳርጌ!(አንድ አድርጌ፣ አንድ የሚያደርግ)። እንግዲህ መሰለኝና ተናገርኩ ጎልጉል Speak your mind ስላለ።

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule