የሰሞኑ የነ ጃዋር ሲራጅ ግርግር ለኛም ስም አትርፏል፡፡ እንደፈቀደው ይሁን፡፡ እኛ ጉዳያችን ሞልቶልናል፡፡ የታቀደው የቴዲ ኮንሰርት በመሰረዙ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በኮንሰርቱ ታክኮ ሊከሰት የሚችለው የህዝብ መተላለቅ በመቅረቱ እሰየው ነው፡፡ ብርና ዝና ብቻ እያሰቡ የህዝብ መጨራረስን ሊጋብዙ የነበሩ ሰዎች ተንኮላቸው ስለከሸፈባቸው አላህን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡
ታዲያ ያስገረመኝ ነገር ስሜት እውነትን ለመሸፈን ምን ያህል ጉልበት እንዳለው መረዳቴ ነው፡፡ አጃኢብ ነው! ግጭትና ትርምስ ሲሰበክ የነበረው በውሸት የተፈጠረውን ወሬ እንደ ሰበብ በማድረግ ነው፡፡ ውሸቱን ለማዳመቅ በግርግሩ ውስጥ የገቡ ሀይሎች አበዛዝም ያስገርማል፡፡ ከአሜሪካ እስከ ኖርዌይ፣ ከለንደን እስከ ሸገር እየተጠራሩ ሽብሩን ለማጋጋል የተደረገው ጥረት አስደናቂ ነበር፡፡ ለወትሮው በአንድ ብሄር ላይ የሚደረግ ዘረኛ ቅስቀሳን እንቃወማለን ሲሉ የነበሩ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ከኛ ጋር ተባብረው ግጭት እንዳይከሰት ጥረት ያደርጋሉ ብለን ስንጠብቅ የኛ ተቃራኒ መሆናቸው አስገርሞናል፡፡ ለምሳሌ እነ ዳንኤል ብርሃኔ “ቀኝ አክራሪዎች እንዲህ አደረጉ” እያሉ ሲጽፉት የነበረው ነገር በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ነገሮችን በስሜት በመቀበል እውነትን ከውሸት ለመለየት ጥረት አለማድረጋቸው አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ ለምሳሌ በግርግሩ መጀመሪያ ሰሞን “መጽሔቱ ቃለ-ምልልሱን አትሞ አውጥቶታል” ሲባል ከርሞ “ሁለት ዓይነት መጽሔት ነው የታተመው” የሚል ነጠላ ዜማ ተለቀቀ፡፡ ከዚያ ለጥቆም “መጽሔቱ አከራካሪውን ቃለ-ምልልስ ቆርጦ አስቀርቶታል” ተብሎ ተወራ፡፡ “የተቆረጠው ክፍልም ይኸውላችሁ” ተብሎ በአንዳንድ ዌብሳይቶች ላይ ተለጠፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ጭራሽ የቴዲ አፍሮ ቃለ-ምልልስ በኦዲዮ ተቀርጾ በእጃችን ገብቷል የሚል ማስመሰያ ተፈጠረ፡፡ ይህ ሁሉ የውሸት ወሬ ነው፡፡ በግርግሩ የተሳተፉት ግን አንዱንም ለማጣራት አልሞከሩም፡፡ “ጀዋር የተናገረው ነገር ምንጊዜም እውነት ነው” የሚል መመሪያ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ (ያሳቀኝ ነገር ቴዲ አፍሮ ራሱ መጽሔቱ “ቅዱስ ጦርነት” በሚለው ርዕስ አለመታተሙን ያላወቀ መሆኑ ነው፤ እንደዚያ ዓይነት ርዕስ ያለው መጽሔት በጭራሽ አልታተመም)፡፡
እኛ ለቴዲ አፍሮ አልነበረም የተከራከርነው፡፡ ቴዲ ተናገረ የተባለው ቃል ትክክል ነው ያለ ሰው የለም፡፡ በደሌ መጠጣትን አቁሙ መባሉንም የተቃወመ ሰው የለም (እኛ እንዲያውም አስካሪ መጠጥ የተባለ በሙሉ ቢወገድ ነው የምንፈልገው)፡፡ እኛ ያልነው በሀሰተኛ ወሬ ሰውን ለማጨራረስ አትሞክሩ ነው፡፡ ይህንን ሀሰተኛ ወሬ የሚያራግቡ ሀይሎች ድብቅ አጀንዳ አላቸው ነው ያልነው፡፡ ይኸው ነው መልዕክታችን፡፡
ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ቴዲ አፍሮ በትክክል “ቅዱስ ጦርነት” የሚለውን ቃል ተናግሮ ቢሆን እንኳ መደረግ የነበረበት በፍትሕ መንገድ መፋረድ ነው፡፡ ሆኖም የግርግሩ አድማቂዎች በቀጥታ ወደ ዘረኝነት ቅሰቀሳ ነው የገቡት፡፡ ያሳዝናል! የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ወግ ይህ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ትግልም ከስርዓቶች ጋር ነው እንጂ ከሰፊው የአማራ ህዝብ ጋር አይደለም፡፡
በኔ በኩል የምችለውን አድርጌአለሁ፡፡ በአላህ እርዳታ የምፈልገውን ውጤት አግኝቼበታለሁ፡፡ ህዝቦቻችን አልተገዳደሉም፡፡ አልተፋጁም፡፡ እነርሱ እንደተመኙት አልተጨራረሱም፡፡ ስለዚህ ባደረግኩት ነገር ደስተኛ ነኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ታክል ጸጸት አይሰማኝም፡፡ ወደፊትም እንዲሁ ማድረጌን እቀጥላለሁ፡፡
===መነሻው===
ይህንን ሁሉ ትርምስምስ በአጋፋሪነት የመሩትን እናውቃቸዋለን፡፡ ሁሉም በውጪ ሀገር ተቀማጭ ሆነው ነበር እሳቱን ሲያጋግሉት የነበረው፡፡ ዓላማቸው ሰሞኑን የፈጠሩት የሰንበቴ ማህበር ግዙፍ ስኬት እያስመዘገበ እንደሆነ እንደ መጠቆሚያ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ ህዝብ ቢጨራረስ ባይጨራረስ ጉዳያቸው አይደለም፡፡
የግርግሩ ዋና አቀናባሪ ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እንደ ቃል አቀባይ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ግን ጀዋር መሐመድ ነው፡፡ ጀዋር በቅድሚያ ስለጉዳዩ በኔ ኢንቦክስ ሲነግረኝ “የእንቁ መጽሔት ባለቤቶች ጎል ሊያስገቡን የውሸት ሽፋን በፎቶሾፕ ሰርተው በትነዋል” ነው ያለኝ፡፡ እናም “ይህንን መጽሔት መበቀል አለብን” በማለት ሊቀሰቅሰኝ ሞከረ፡፡ “እንቁ ማለት የማይታወቅ መጽሔት ነው፤ ነገሩን ባናጋግለው ይሻላል” አልኩት፡፡ እርሱ ግን “አይደለም! በጣም ግዙፍ የሆኑ ነፍጠኞች ናቸው በገንዘብ የሚደጉሙት” ብሎ ሊያነሳሳኝ ሞከረ፡፡ እኔ በበኩሌ የሰውዬው አጉል ብልጠት ስለሚደብረኝ ግድ አልሰጠሁትም (እርሱ የሚያወራውን ነገር ሁልጊዜ በጥርጣሬ ነው የማየው)፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱን ላለመገናኘት ስሸሸው ቆየሁ፡፡ በዚህ መሀል ቴዲ ሰጠ ስለተባለው ቃለ-ምልልስ ሐቁን ለማወቅ ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ እናም ውሸት መሆኑን አረጋገጥኩ፡፡
ታህሳስ 14/2006 ከጀዋር ጋር በሌላ ጉዳይ ስንገናኝ ግን ቀደም ሲል ውሸት ነው ሲለው የነበረውን ነገር “እውነት ነው! የኦዲዮ ማስረጃ ጭምር አለን፤ የመጽሔቱ አዘጋጅ ማረጋገጫ ሰጥቶኛል” የሚል ማሻሻያ ሰጥቶት ከርሱ ጋር እንድሳተፍበት ይጨቀጭቀኝ ጀመር፡፡ ነገሩ ውሸት ነው ሳልለው “ይህንን ነገር ከማጋጋል መቆጠቡ ይመረጣል” ብዬ ላቀዘቅዝ ሞከርኩ፡፡ እርሱ ግን “እምቢ! ቴዲን አፈር አባቱን ሳናበላው አንተወውም፤ አንተ ደስ ካለህ እንደ ፈለግክ ሁን” እያለ ይፎክርብኝ ገባ፡፡ ለፉከራው ግድ ባይኖረኝም ለራሱ ዝና ሲል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ ያገኘውን ተቀባይነት በመጠቀም ስለሜንጫው የፎከረውን ቃል ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል ብዬ ፈራሁ፡፡ እና የርሱን እንቅስቃሴ የሚያኮላሽ እርምጃ መውሰድ አለብኝ በማለት ወሰንኩኝ (በወቅቱ እኔም እንደርሱ በቢራ የምንቦጫረቅ መስሎት “በደሌ መጠጣት አቁም” ሲለኝ ለጥቂት ነበር ከመሳደብ ራሴን የተቆጣጠርኩት!)፡፡
***** ***** *****
ይህ ሰው በጣም አጭበርባሪ ነው፡፡ የውሸት ወሬ መፈብረክ ይችልበታል፡፡ ደግነቱ የሚፈበርካቸውን ወሬዎች ሀሠትነት ለማረጋገጥ ረጅም ጊዜ አይፈጅም፡፡ የዚህ ሰው ሌላኛው ባህሪ ደግሞ ለሁሉም የፖለቲካ ቡድኖችና ፓርቲዎች የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ሰውዬው ከላይ ሲታይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ይመስላል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ከኦፒዲኦ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም የጠበቀ ግንኙነት አለው፡፡ አንድ ቀን ሳያስበው ይህንን ግንኙነቱን ግልጽ ያደረገበትን ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ እኔ በሰጠሁት ምላሽ ሳስደነግጠው ትንሽ እንደማፈር ብሎ ዘጋው (በወቅቱ የጠየቀኝን ጥያቄ ሌላ ጊዜ ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡ በርሱ ቤት ነገሩን የማላውቅ መስሎታል፡፡ ይሁንና በፌስቡክም ጭምር በሰፊው ሲባል የነበረ ነገር በመሆኑ ብዙም አልደነቀኝም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው ከኦነግ-ቀመስ ቡድኖችም ጋር በትክክል እንደሚሰራ መረጃው አለን፡፡ ከሻዕቢያ ጋር እንደሚሰራም ውስጥ ውስጡን ይወራል፡፡ እነዚህ ግንኙነቶቹ ቀደም ብዬ የሰማኋቸው በመሆኑ ብዙም አላስገረሙኝም፡፡ በጣም የተደነቅኩት ግን “ነፍጠኛ” እያለ ቀን ከሌሊት ከሚሰድባቸው ቡድኖችም ጋር የሚሰራ መሆኑን እራሱ በነገረኝ ጊዜ ነው፡፡ የዚያን ቀን በጣም ነበር የደነገጥኩት (ዕለቱ ህዳር 7/2006 ነው)፡፡ “ይህ ሰው ጥቅም ካገኘ ለሰይጣንም ይሰራል ማለት ነው ለካ!” በማለት ተደመምኩበት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ሰው ጋር የማደርገውን የመልዕክት ግንኙነት ገታ ማድረግ ጀመርኩ (እንግዲህ ለዚህ ሁሉ ማስረጃው በእጄ ነው ያለው)፡፡
ሰውዬው ከነዚህ ሁሉ ቡድኖች ጋር የሚሰራበት ዓላማ ገንዘብና ዝና ማግኘት ይመስለኛል፡፡ በየሀገሩ እየዞረ ብር እንደሚለቅምም ይታወቃል፡፡ እኔ በበኩሌ በግርግሩና በጉዞው ብር ቢያገኝበት ጉዳይ የለኝም፡፡ ብር አገኝበታለሁ ብሎ የማይገባ ድራማ ሲጫወት ግን ዝም ብዬ ላልፈው አልፈቀድኩም፡፡ የጸረ-በደሌውን ዘመቻ በጎን በኩል የተጋፈጥኩት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ አስቡት እስቲ! የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለመታደም ድሬዳዋ ስቴድየም በተገኘው ህዝብና እርሱን በሚቃወመው ህዝብ መካከል ግጭት ቢፈጠር ውጤቱ ምን ሊሆን ነው? በዚያ ውጤትስ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ነው? አማራው ነው? ኦሮሞው ነው? ወይንስ ማን ነው? እስኪ እናንተው መልሱት፡፡ … የጃዋር የፖለቲካ ተንታኝነት ይህ ነው እንግዲህ!…(እንኳንም ኮንሰርቱ ቀረ! እሰይ!)
ከዚህ ሰው ጋር የተዋወቅኩት በኢንተርኔት ነው፡፡ የምጽፋቸውን ጽሑፎች በዌብሳይቱ ለመጠቀም በፈለገበት ጊዜ ሲያነጋግረኝ ነው ያወቅኩት፡፡ ከዚያ ውጪ ሌላ ትውውቅ የለንም፡፡ ለአንድም ቀን አይቼው አላውቅም፡፡ እኔ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ከኔ የፌስቡክ ፔጅ ላይ እየወሰደ ዌብሳይቱ ላይ ይለጥፋል፡፡ በቃ ይኸው ነው፡፡ ባለፈው ክረምት ደግሞ “ያንተን መጽሐፍ እናሳትማለን” የሚል ቃል ሰጠኝ፡፡ በጥቅምት ወር መጨረሻ ገደማ ግን የመጽሐፉ ጉዳይ ቀረና መጽሔት እንጀምራለን ብሎ መጣ፡፡ የመጽሐፉ ጉዳይ መቅረቱ ሆዴን እየበላኝ ብቸገርም እስቲ ትንሽ ልመርምረው ብዬ አብሬው ሰነበትኩ፡፡ ይሁንና ከህዳር ወር 10/2006 ወዲህ የመጽሔቱም ነገር የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ (የማያደርገውን ነገር በስሜት የሚያወራው እንዲህ ዓይነቱ ቀጣፊ ሰው በድሬዳዋ ልጆች ቋንቋ “ሐጂ ቅደደው” ወይንም “ሐጂ ቦንባ” ነው የሚባለው)፡፡
የሆነ ሆኖ የአሁኑ ግርግር ከዚህ ጉዳይ ጋር አይገናኝም፡፡ መጽሔት እናዘጋጃለን ብዬ የለፋሁበትን ድካም መና ስላስቀረብኝ ቂም ቋጥሬ አይደለም ልጋፈጠው የወሰንኩት፡፡ እርሱ ያመጣው ሎጂክ እጅግ አደገኛና ህዝቦችን የሚያጨራርስ በመሆኑ ነው ዝም ማለቱን ትቼ በቀጥታ የገባሁበት (መጽሔቱን በራሴ ወጪ ይፋ አደርገዋለሁ)፡፡
===ታሪክ ====
እኔ የታሪክ ምሁር አይደለሁም፡፡ ግን ስለታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ በተለይ ስለ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በደንብ ነው ያነበብኩት፡፡ ከሰሞኑ ግርግር ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የአጼ ምኒልክንም ታሪክ አንብቤአለሁ፡፡ ነገር ግን ግርግሩ በተጋጋለበት ወቅት ስለርሱ ትንፍሽ አላልኩም፡፡ ወደፊትም እንዲህ አይነት አደገኛ አሻጥር የተመላበት ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ግጭትን የሚያጋግሉ ታሪኮችን አልቆሰቁስም፡፡ ግጭት ሲቀሰቀስ ተጠቃሚው ህዝብ ሳይሆን የህዝብ ጠላት ነው፡፡
አጼ ምኒልክ ደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያን ከግዛተ መንግሥታቸው ጋር ለመቀላቀል ያደረጉት ጦርነት ከፍተኛ እልቂትና ፍጅት የተፈጸመበት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሊታሰቡ የማይገባቸው አጸያፊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ ህዝቦች የገዛ መሬታቸውን ተነጥቀው በትውልድ ቀዬአቸው ጭሰኛ ለመሆን ተገደዋል፡፡ ይህንን ታሪክ የምኒልክ ጸሐፊ ከነበሩት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ-ሥላሴ ጀምሮ በርካቶች በድርሳናቸው ጽፈውታል፡፡
ታዲያ የአጼ ምኒልክ ጦር ያኔ ለፈጸመው ጥፋት የአሁኑ ትውልድ ዕዳ ከፋይ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ ያለበት ሃላፊነት ከታሪክ ተምሮ የያኔው ጥፋት እንዳይደገም መከላከልና የህዝቦች የመብት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ አብሮ መታገል ነው፡፡ ታሪክን የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እያደረጉ እልቂትና ሁከትን መቀስቀስ የህዝቦችን ትግል ወደኋላ ማስቀረት እንጂ ለህዝቦች የመብት ጥያቄ አንዳች መፍትሄ አያመጣም፡፡
የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ስለ አጼ ምኒልክ አልጽፍም ያልኩት አንደኛ ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ነው፡፡ ስውር ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦችና ቡድኖች ህዝቦችን ለማጨራረስ ስለአጼ ምኒልክ በሚነዘንዙበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እነርሱ በሚፈልጉት ወጥመድ ውስጥ ራስን ማስገባት ነው፡፡ ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በአብዛኛው የሚያወዛግቡን በመሆናቸው ታሪኮቹን በሶሻል ሚዲያ ላይ እያመጡ መለጠፍ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ታምራት ነገራ እንደጻፈው እንዲህ ዓይነት የሚያነታርኩ ታሪኮችን በፌስቡክ ላይ መለጠፍ ሌሎች ታላላቅ ህዝባዊ አጀንዳዎች እንዲረሱ መንገድ መክፈት ነው፡፡ ታሪኩን ማወቅ የሚፈልግ ሰው በታሪክ ምሁራን የተጻፉ ድርሳኖችን ቢያገላብጥ ነው የሚሻለው፡፡ ሶስተኛ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ታሪኮችን መጻፍ እኔ ፌስቡክን ከምጠቀምበት ዓላማ ጋር በጭራሽ የማይሄድልኝ በመሆኑ ነው፡፡
===ትምህርት===
ይህ ግርግር ከተጀመረ ወዲህ ብዙ ተብዬአለሁ፡፡ በወረዱ ቃላት ተሰድቤአለሁ፡፡ አብዛኛው ተሳዳቢ የማያውቀኝ ስለሆነ ምንም አልተሰማኝም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚንጫጩበት ግለት ግን በጣም አስደንቆኛል፡፡ ይገርማል! አንድ ነገር ልንገራችሁ፡፡
ወላጅ አባቴ ለኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ ጊዜአት ታስሮ፣ ተደብድቦ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረቱን አጥቷል፡፡ ትግሉ ሲጀመር ጳጉሜ 5/1966 ቀን የመጀመሪያ ሰማዕት ሆኖ የወደቀውና ሬሳው ረጅም ርቀት የተጎተተው ሰው አሕመድ ተቂ (ሁንዴ) የተሰኘው አጎቴ ነው (ጓደኛው ኤለሞ ቂልጡ በዚያው ቀን ነው የሞተው፤ ሆኖም በወቅቱ የአካባቢው ጸጥታ ሀይሎች ስላላወቁት እዚያው የወደቀበት ቦታ ላይ ትተውት ሄደዋል፤ እስከዛሬ ድረስ ያንን የመሰለ ጀግና ገበሬዎች በአንድ ገደል ጥግ በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ራቅ ብሎ ተኝቷል፤ እነ ጀዋርን የመሳሰሉ ሰዎች ግን ሬሳውን እንኳ ደህና ቦታ ስለመቅበር ጉዳይ ላይ ሳይመካከሩ በየስርቻውና በየፓርቲው “ኤለሞ” እያሉ ቱሪናፋ ይነዛሉ… ሐፍረተ ቢስ! አዳማ ውስጥ ደግሞ በርሱ ስም ትልቅ ግንብ አቁመዋል፤ ሬሳውን እንቅበር ብሎ የጠየቀ ሰው ግን እስከ አሁን ድረስ የለም፤ እኛ ከጠየቅን “ሌላ ተልዕኮ አላችሁ” እንባላለን፤ ጉድ እኮ ነው)፡፡
አባቴ የታናሽ ወንድሙን ሬሳ ካየበት ደቂቃ ጀምሮ አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ኑሮው የቀን ጭለማ ሆኖበት ከሰው ተለይቶ በራሱ መንገድ ለብቻው ነው የኖረው፡፡ ደርግ ሲወድቅ ያለ አዋጅ የተወረሰበትን አንድ ክፍል ቤቱን እንዲመልሱለት ጥረት አድርጎ ተከልክሏል፡፡ በዚያው ከተማ ውስጥ ግን እስከ አምስት ክፍል ቤት ያላቸው ሰዎች (ለዚያውም በአዋጅ የተወረሱ) ተመልሶላቸዋል፡፡ በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ አባቴን የት ነህ ብሎ የጠየቀው ሰው የለም፡፡ ከርሱ ጋር የምንቸገረው እኛ ልጆቹ ነን፡፡ አሁንም የድሮው ግርፋት አገርሽቶ እግሩን ፓራላይዝ አድርጎት ሲያስቀምጠው ከርሱ ጋር እየተቸገሩ ያሉት ልጆቹ (በተለይ ሴት ልጁ) ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ “እናውቅሃለን፤ ዘመድህ ነን” ባይ ወገኖች “አባትህ የት ደረሰ” ብለው ጠይቀውኝ እንኳ አያውቁም፡፡ እኔም ነገ ብቸገር የሚገጥመኝ ዕድል ይኸው ነው፡፡ እነዚህ ቱሪናፋ የሚነፉት ወሽከሬዎች ጉዳይ ኖሮኝ እገዛ ብጠይቃቸው አካውንት ዲአክቲቬት እስከማድረግ ይደርሳሉ፡፡ በተለይ ዘላለም ወዬሳ የሚባለው የኦነግን ማሊያ የለበሰ የኦፒዲኦ አገልጋይ “በኦሮሞ እጅ አድገህ፣ የኦሮሞን እንጀራ በልተህ፣ የኦሮሞን ልብስ ለብሰህ፤ ዛሬ ኦሮሞን ከዳህ”… እያለ ሲዘባርቅ ከቤታቸው ኩሽና በየቀኑ እንጀራ በወጥ ሲያቀብለኝ የኖረ ነበር የሚመስለው፡፡
ምሁራን ነን ተብዬዎቹም ኤለሞ ቂልጡን ሲያወድሱት ሳት ብሎአቸው እንኳ በዚያው ቀን በዚያው ሜዳ ላይ ከኤሌሞ ቀድሞ የሞተውንና በርሱ ሰበብ መላው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር የታመሰበትን የሰማዕት አጎቴን ታሪክ በአንድም መጽሔትና መጽሐፍት ሲያነሱት አይቼ አላውቅም (እርግጥ አንድ ጊዜ የድሮው የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ገላሳ ዲልቦ ገለምሶ ከተማ መጥተው የአጎቴን ስም ሲያነሱት ሰምቻለሁ፤ ”ግዝትና ግዞት” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥም ስሙን አይቼዋለሁ፤ ቴዎድሮስ ሙላቱ በጻፈው አኬል ዳማ ውስጥም ታሪኩ በጥቂቱ ተጠቅሷል፤ ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐሰንም በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ ውስጥ አንዴ ስሙን የጠቀሰው ይመስለኛል፤ እነዚህን አራቱን ብቻ በቤተሰቤ ስም አመሰግናቸዋለሁ፤ ከዚህ የተቀረው ሁሉ አስመሳይ ነው)፡፡
ለረጅም ገዜ የዚህ አጎቴ ታሪክ መረሳት በጣም ያንገበግበኝ ነበር፡፡ እናም ታሪኩ መጻፍ አለበት ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ መለስተኛ ጽሑፍ በዊኪፒዲያ ውስጥ ያስቀመጥኩት እኔ ነኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እርሱን ለማወቅ በሚል መጠነኛ ግርግር የተጀመረው፡፡ ከማንም በፊት አጎቴን ያስታወሰው ግን ዓሊ ቢራ ነው፡፡ ገጣሚው አቡበከር ሙሳ እና ዓሊ ቢራ በጋራ ምስጋና ሊደርሳቸው ይገባል፡፡ “ያ ሁንዴ በሬዳ” የተሰኘው ዜማ የተጻፈው ለአጎቴ ለአሕመድ ተቂ ሼኽ ሙሐመድ-ረሺድ ነው (በነገራችን ላይ ዓሊ ቢራንም ለመጀመሪያ ጊዜ በዊኪፒዲያ ያስገባሁት እኔ ነኝ፤ ዓሊ ቢራ ለአጎቴ ማስታወሻ የሰራውን ስራ ለማክበር ይሆን ዘንድ ነው ታሪኩን በዊኪፒዲያ የጻፍኩት)፡፡
ታዲያ የአጎቴ ስም አለመነሳቱ አንዳንዴ ለበጎ ነው ያሰኘኛል፡፡ በርሱ ጦስ የአባታችን ህሊና ተቃውሶ የአባት ፍቅር በደንብ ሳይገባን ነው ያደግነው፡፡ አባቴ በ1975 ከእስራት ወጥቶ ከዝርፊያ የተረፈውን ገንዘብ ዝም ብሎ ሲበትን ጸባዩን ማስተው ያቃታት እናቴ እኛን ለማሳደግ ያሳለፈችው ስቃይ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን ያነደኛል፡፡ በተገደለው አጎቴ ሰበብ ሌላኛው አጎቴም (ኢስራፊል ይባላል) አዕምሮው ተነክቷል፡፡ ሟች እናታቸው መርየም “ልጄ አህመድ ተቂ” እንዳለች ነው ህይወቷ ያለፈው፡፡ ወላጅ አባቱ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ግን የአላህ ሰው ስለሆኑ ትዕግስቱ ነበራቸው፡፡ የአጎቴ ጓደኞች የነበሩት እነ ነጃሽ ዒስማኢል፣ ሙሐመድ በከር፣ ዒስማኢል አሕመዩ፣ ሙሐመድ አብዶ (ሉንጎ) የመሳሰሉት ድንቅ ነጋዴዎች ፣ በግርፋትና ቶርች ብዛት ናላቸው ዞሮ ያለ ጊዜአቸው ከስራው ዓለም ተሰናብተው የሰው ጡረተኛ ለመሆን ተገደዋል (ሉንጎ ከድብደባ ብዛት ዐይኑን አጥቷል)፡፡ የአጎቴን ታሪክ ማንሳት የሚችሉት በርሱ ሰበብ እውነተኛውን ስቃይ ያዩት እነዚህ ሰለባዎችና ቤተሰቦቻቸው ናቸው፡፡ ምድረ አጭበርባሪ መንገደኛ ሁሉ ስሙን እየጠራ መነገጃ እንዲያደርገው አንፈቅድም፡፡
የኔ አጎት የሞተው ለኦሮሞ መብትና ነጻነት ሲል ነው፡፡ አጎቴ አማራን ለመጨፍጨፍ አይደለም ጫካ የገባው፡፡ ከአማራዎች ጋር በጉርብትና ሲኖርና በጋራ ሲሰራ የነበረ ሰው ነው፡፡ እርሱ የታገለው ጨቋኙን ስርዓት ነው እንጂ የአማራ ተወላጆችን አይደለም፡፡ የርሱን ታሪክ ከበደሌ ቢራ ጋር እያገናኛችሁ ማስጠንቀቂያ ልትሰጡኝ የምትሞክሩት ሀይሎች ህልመኞች መሆናችሁን እወቁ፡፡ ለራሳችሁ ሰው የመጨፍጨፍ ዓላማ ካላችሁ በግልጽ አሳውቁን፡፡ የአጎቴን ስም ግን አለቦታው አታንሱት፡፡ እዚያው መቃብሩ ውስጥ በሰላም ይተኛበት፡፡
*****
እንግዲህ አፈንዲ ማለት ይህንን ሁሉ ታግሶ ዝም ያለ ሰው ነው፡፡ ዛሬ “አፈንዲ ጉራጌ ነው፣ አደሬ ነው፣ ጎበና ነው ጂንኒ ጀቡቲ” እያሉ የሚጯጯኹት ታሪክን መሸጥ የለመዱ አስመሳዮች ናቸው፡፡ “ህዝብን ማጋጨት አቁሙ” ማለት ጎበና ከሆነ በእርግጥም ጎበና ነኝ (አንዳንዶች ጭራሽ የጻፍኩትን ሳያገናዝቡት “አባት ማር ስለበላ የልጅ አፍ ጣፋጭ አይሆንም” እያሉ ሊተርቱ ይፈልጋሉ)፡፡
ሰማችሁ ወይ! እኔ ልረዳችሁ ብዬ ነው እንጂ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል፡፡ አንድም ነገር የመጻፍ ግዴታ የለብኝም፡፡ በአባቴ ላይ የደረሰውን ስቃይ እያየሁ ያደግኩ በመሆኔ ከርሱ ህይወት በቂ ትምህርት ወስጄአለሁ፡፡ የሚያሳዝነኝ እንዲህ የሚነገድበት ህዝብ ለሁሉም ነገር ባይተዋር መሆኑ ነው፡፡ ለሁሉም ትምህርት ወስጄበታለሁ፡፡
===የኔ ዓላማ===
ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት እኔ የፖለቲካ ዓላማ የለኝም፡፡ የኔ ጉዳይ ያለው ከህዝብ ዘንድ ነው፡፡ የማንኛውም ህዝብ መብትና ነጻነት እንዲከበር ጽኑ ፍላጎቴ ነው፡፡ የአንዱን ህዝብ መብት ለማስከበር ሌላውን መንካት ትክክለኛ ነገር አይደለም፡፡ እኔ የወጣሁበት የኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከበረው የአማራን ህዝብ በመጨቆን አይደለም፡፡ የአማራውንም መብት ማስከበር የሚቻለው ኦሮሞን በመጨቆን አይደለም፡፡ የጭቆናው ደረጃና ስልት ቢለያይም ሁሉም ህዝብ መብቱን ፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት፡፡
የኔ የምንጊዜም ፍላጎትና ዓላማ ይህ ነው፡፡ ከተወለድኩበት የኦሮሞ ህዝብ በፊት በሀረሪ ህዝብ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ የጻፍኩት በዚህ መንፈስ ነው፡፡ ከገለምሶ የተገኙትን የመምሬ ሙላቱ እና የሼኽ ዑመር ገለምሲይ አስደሳች ታሪኮችን ጽፌ በፌስቡክ እና በድረ-ገጾች ላይ የለጠፍኩት ለዓላማችን መሳካት ያግዘናል በሚል ነው፡፡ ሰዎች የፖለቲካ ታጋይ መስዬአቸው በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱኝ በሚል ልዩ ልዩ ማስታወሻዎችን ለጥፌ ያስነበብኩት “ፖለቲካው አይመለከተኝም” ብዬ ሳይሆን በዚህ ገጽ ላይ ፖለቲካ እንደማላካሄድ ለማሳወቅ በሚል ነው፡፡
ወደፊት በዚህ ገጽ ከኔ ጋር መማማር የሚፈልግ ሰው በዚሁ መንገድ ከኔ ጋር ሊቀጥል ይችላል፡፡ ለኔ የሚከፍል ይመስል እየተሳደበ፣ ቡራ ከረዩ እያለ፤ እየተራገመ ወደርሱ መንገድ እንድገባለት የሚሻ ሰው ካለ ግን በሰላም ወደመጣበት ቢሄድልን እንመርጣለን፡፡ እኛ ለፈጣሪ እንጂ ለሌላ ሀይል አጎብድደን የማናውቅ ሰዎች ነው፡፡ ህሊናችንንም ለገንዘብ ቸብችበን አናድርም፡፡
===ያክብርልኝ===
በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በገጠምኩት ሙግት ብዙዎች (65 %) የሚሆኑት ከኔ ሃሳብ ጋር ተግባብተዋል፡፡ ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡ በተለይ ግን መንሱር አሊዩ፣ ጃዕፈር ሰይፊ (ጃፈር አሕመድ)፣ ፊርዶስ ሐሶ፣ ዑስማን አሕመድ፣ ያሕያ ሙሐመድ፣ ጀሚል ይርጋ፣ ፍጹም ታዬ፣ ታጠቅ ወንድሙ፣ ተካበ መኮንን፣ የሚባሉ ጓደኞቼን በጣም አመሰግናቸዋለሁ (ምክንያቱን ወደፊት ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡
——–
ሰላም
አፈንዲ ሙተቂ
ታሕሳስ 26/ 2006
Afendi Muteki is a researcher and author of ethnography, history and art with special focus on Eastern Ethiopia.
Abegaz says
Afendi,
Let me say this: we all need to see the right of anyone, person or ethnic group, respected. Trying to campaign on something no one has seen is abuse of right. No one among us has seen the improper treatment of Oromos by Menilik. In the court of law to say something happened firmly, you got to observe it. Anything short of that is in question mark and not acceptable. If there is any history showing Menilik did bad against oromos, we take it as history and as you rightly said we read history and keep it for ourselves. pluss Ethiopian emperors represent themselves and not a particular ethnic group. It is all about their power and not democracy. That was the reality then. Atse Tewodros came to Shewa and cut Amhara people hands, history says. But no Shewan Amhara dislike Tewodros. First is was a process of nation building, second no present generation saw that and third old Ethiopia may be full of bad happening as it was anywhere in the world.
Let me challenge Oromo nationalist who claim a distinct Oromia nation. Suppose Menilik did not unite fragmented Ethiopian kingdoms, including the Oromos, what will happen to us? Let me explain one scenario on present-day Oromia since that has been a bone of contention. Places like wollega, Jima and southern Sidamo will be part of English colony as part of Sudan and Kenya. Places like Bale and Arsi would be part of Italian colony with current Somalia. Places like Harar and eastern Shewa would be under France colony. Jawar would have been speaking Somali in present day Somalia. There would not have been any dream of greater Oromia. Is this what the Oromos need? It may be suitable for Jawar since he is interested in radical Muslim government uniting the horn of Africa, but I do not think all oromos prefer this. So let us not cry saying Menilik did this or that. Let us not think of a free nation of Oromia. Can you bring Oromos from Kenya and form an Oromo nation now. Not possible, my brother. That is the legacy of colonialism.
one day says
thank you for your logical reasoning confined to your mind. le me say this: In germany denying jews genocide is a very great crime! In ethiopia, not denying menilik’s genocide, reinforcing, restoring is not crime! In Ethiopia which is frequently seen? : denying menilik’s action as genocide regardless of whether we should live together amharasi or reminding the sorrow, devastating action by oromos? for me the former. Still oromos are living with the rest ethnic groups forgetting the wound from one generetation to another, oromos are forgiver than mandella! mandella was taken to prison by whites oromos were collected in sprit and flesh to grave in millions by menilik. These were forgiven but it is the deny of amharas that reminds oromos the irritation. Guys it is neither you mor me who decides whether oromo stands as free nation or not! the majority of Oromos. If more 50.00000000000000000000….1% of oromos arrived at the thing that oromos craved for no one refrains from doing so! By the way how many years would it take to integrate morethan one ethnic groups coming from different origin? how many years did it take to build Israel kingdom? Don’t bother about time.
aradaw says
I am still suspicious of these writings. For me it contradicts what we preach in current situation and it does not apply to the former generation of Menelik. We condone, condemn the killings , oppression exploitation and in general the devil deeds of Mengistu and Meles TPLF. specially the later one TPLF. What makes the deeds of Menelik different. it really bothers me when it is written as editorial. I really do not understand are we denying that the evil deeds were not committed? or are we trying to glorify Menelik for the war of Adwa and forget what happens in the Southern expansion; depopulation and oppression of the Oromos, Wollamo, Keffa Sidama…What happened to King Tona? Why are we afraid of talking about it? here in America, what happened to the Native American, to our Black relatives, people are talking writing so every generation knows exactly what happened. In South Africa is the same, people talk big. In countries where evil deeds of the past were denied or put under rug for example former Yugoslavia, you might have seen or heard what happened in 1991. The worst war between the Serbs and Croats that took the life of thousands in the middle of Europe. I do not see Menelik history is a way to make the current generation responsible. It is to make the current generation to know exactly what happened and feel the pain as those who felt it and also to help the current generation reserves from unnecessary and hurtful Briticism and name calling as “Oromo Extremists” (as we see it here and other websites) This does not help any one except the common enemy TPLF/EPRDF. They are using this to wedge rift nothing else. It is known that they put their fingers everywhere they find opportunities to divide us.
alem woldel says
Ena yemlew yeha tewlde yalfewn neger asebo geza yemyatefabt neger yelewm yerasun asara telo malfe new yemfelgew esmum be sers ena bewtat enjey be torent yalfew geza yebkal be tarke anenorm !!!!!!
Tewodros A says
Hi Afendi, thank you for the balanced view and revealing the evil nature of the so called political activist. It looks you idea is worthwhile for the present Ethiopia. Well done
በለው! says
>>>>አፈንዲ ሙተቂ፣ መንሱር አሊዩ፣ ጃዕፈር ሰይፊ (ጃፈር አሕመድ)፣ ፊርዶስ ሐሶ፣ ዑስማን አሕመድ፣ ያሕያ ሙሐመድ፣ ጀሚል ይርጋ፣ ፍጹም ታዬ፣ ታጠቅ ወንድሙ፣ ተካበ መኮንን፣(የመጨረሻው ጦማር)ይሁን እንጂ ሀገርና ሕዝብ የማዳን ሥራችሁ ግን የመጀመሪያችሁ እነጂ የመጨረሻ የለውም!ከማንም ቤተሰብ፣ ከየትኛውም ብሔርና የሃይማኖት ዕምነት ተከታዮች ብትሆኑም ቤታችሁ፣ ሀብታችሁ፣ ቅርሳችሁ፣ መጠሪያችሁ፣ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ናት!
* በኢትዮጵያ በዚህ ቀውጢ ዘመን በሰላምና በክብር መኖር ማለት…ለጠላቶቻችን ታላቅ ህፍረትና ውድቀት ለትውልድ ግን ትልቅ ክብርና ፀጋ ነው። ይህ የዋህ፣ ቅን፣ ድሃ፣ እሩህሩህ፣ ሕዝብ ከኑሮ ድቀት፣ ከርሃብ፣ እርዛት አልፎ በእየዘመኑ የሚደርስበት ግርፋት፣ በደል፣ ጭቆና፣ በተጨማሪ የሽብር ጥቃት ከደረሰበት፣ እልውናውን የሚፈታተኑ የሚሽነሪ ባንዳ፣ የነጭ ቅጥረኞች፣ በገንዘብ ተለውጠው ሲነሱበት መልካም ዝናና ከብሩን በርዘው ሀገሩ አጥፊና ጠፊ እንዲሆን የሚሰብኩትና የሚመለምሉት መጪው ዘመን አያዋጣም!ሌሎችም ሀገራት የሄዱበት መንገድ አላዋጣቸውም እኛንም አዘቅት ለመጨመር ያሰፈሰፉ ሹምባሾችን ማጋላጡ መልካም ሥነ-ምግባር፣ ሁሉምና የእያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ፣ ንቃትና ብቃትን ይጠይቃል። ለምን ሰዎች በንፁሐን ደም መበልፀግ ሥምና ዝናን ማትረፍ ተንትነው ለመበትን ይሯሯጣሉ!? “የቤታችን መቃጠል ለትኋን መጥፋት ይጠቅማልን! እንቢኝ በል!!!
*ሠላምን ሰብከው ሠላምን የበሉ ጀዋሪያን(ሻጮች)በኮንሰርቱ ታክኮ ሊከሰት የሚችለው የህዝብ መተላለቅ በመቅረቱ እሰየው ነው፡፡ ብርና ዝና ብቻ እያሰቡ የህዝብ መጨራረስን ሊጋብዙ የነበሩ ሰዎች ተንኮላቸው ስለከሸፈባቸው አላህን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡
*”አፈ ጮሌ ሆደ ጩቤ!” በሁለት ቢላዋ በል! “በእናቴ የመንዝ ኦርቶዶክስ በአባቴ የአሩሲ ጋላ እስላም” ዓይነቶችና አዳናቂ፣ ፈንዳቂና አቃላጭ፣ በአንድ ብሄር ላይ የሚደረግ ዘረኛ ቅስቀሳን እንቃወማለን ሲሉ የነበሩ አንዳንድ ምሁራን ተብዬ የብጥብጥና የእልቂት ስልት ነዳፊ፣ ከቦታ ቦታ የደስታ መልእክትና በሚያሳፍርና በአረመኔያዊ የህዝብ እልቂት እገዛን ሲሰጡ ሲጨፍሩና ሻምባኝና አፋቸውን ሲከፍቱ ታይተዋል።
**ለመሆኑ “ቅዱስ ጦርነት” በአማርንኛ ወይስ በቁቤ ነው የታተመው!?፤ ይህን ያተመ፣ ያሳተመ፣ የጋዜጣውም ኅትመት ኃላፊም ቢሆን በሕግ ተጠያቂ ነው። “ሽብርን በሕዝቦች መካካል መንዛት! ወይም ማስተማር! ወይንም በሕቡ ተደራጅቶ በሀገር ኢኮኖሚና በተለየ የህዘብ ክፍል በሜንጫ መነሳትና ለህወአት አጋር ብሄርተኞች መብት ሲሆን ለተፎካካሪ ፖለቲከኞች የጋዜጣ አምደኞች የፓርቲ አባላት ሽብርተኛ ብሎ የሚሰይመው የሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕገመንግስት ወይንስ የሚያስገነጥል እርስበእርስ የሚያጫርስ የሻቢያህወአት(ማኒፌስቶ)መፈተሽ አለበት። በዚህ ነጥብ የኀይለመለስ ራእይ ብዙ የቤት ሥራና ግምገማ ይጠብቀዋል።እያንዳንዱ በሕግ ተጠያቂ ይሆናል። ወይንም ሕገመንግስቱ ይከበር እንጂ አይተግበር የሚለው የጃዋር ግራ ክንፍ የሀገሪቱን ሥርዓት ከውጭም ከውስጥም እየመራ ነው ማለት ነው።
*እንግዲህ እደሳውዲአረቢያ አስረው ገርፈው ደፍረው አነገት በሜንጫ ሲቀሉ ታይቷል ደጋፊዎቻቸው “ኦሮሞ ኢዝ ኖት ኢትዮጵያ! ዊ ኦሮሞ ኖት ክረሚናል! ሲሉ ዓረቦቹ በሳቅ ሞቱ በግድ ዓረብ መሆን ተጀመረ እንዴ? ኦሮሞ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በጅጅጋ፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰው ከእነነፍሱ ወንዝ የጣለው በሜንጫ የቆራረጠው የጃዋሪያን ሜንጫ አብዮተኞች ቅዱስ ሥራ ብለው ስለሚያምኑ፣የአረብአዊነት መገለጫ፣በሻቢያህወአት ጥላ ሥር የህግ ከለላ ስለተደረገላቸው ነው!?።
**ታሪክን የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እያደረጉ እልቂትና ሁከትን መቀስቀስ የህዝቦችን ትግል ወደኋላ ማስቀረት እንጂ ለህዝቦች የመብት ጥያቄ አንዳች መፍትሄ አያመጣም፡፡የአጼ ምኒልክ ጦር ያኔ ለፈጸመው ጥፋት የአሁኑ ትውልድ ዕዳ ከፋይ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ ያለበት ሃላፊነት ከታሪክ ተምሮ የያኔው ጥፋት እንዳይደገም መከላከልና የህዝቦች የመብት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ አብሮ መታገል ነው፡
**ጀዋሪያን (ሜንጨኞች) ከሻቢያህወአት ጋር የሚያዛምዳቸው ነገር…ድሃ አስገድለው በሞቱ ታጋይ ልጆች አፅም ላይ ፎቅ ሰርተው ኪራይ ሰብሳቢ መሆናቸው ነው። በአፈንዲ ሙተቂና በብዙ የዋህ ደግ ሕዝቦቻችን ላይ በሁሉም ክልልና ዘር የደረሰው ይህ ነው። የኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከበረው የአማራን ህዝብ በመጨቆን አይደለም፡፡ የአማራውንም መብት ማስከበር የሚቻለው ኦሮሞን በመጨቆን አይደለም፡፡ የጭቆናው ደረጃና ስልት ቢለያይም ሁሉም ህዝብ መብቱን ፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት፡፡ ህሊናቸውን በገንዘብና ዝና በአዳራስ ችብጨባ በፌዝ-ቡክ እውቅና፣ በዕድር በእቁብ በሃኢማኖት መስበኪያ ፖለቲካ የሚያስነኩ (የሚያጠቃቅሱ)ገንዘብ ለመቃረም የተነሱ ፅንፈኖች ይወገዱ! በተለይ በአንድ ብሄር ላይ በኅብረት አማራር(በደቦ) የተነሱ፣ በንፅሕ ሙስሊም ወገኖች ሰላማዊ ትግል በተንታኝነት ገብተው በአሻጥር የበተኑ ሁሉ(ጠጨው ዘር አድርጋቸው!) ይበተኑ! አሻጥረኛ፣ አድርባይ፣ ይውደቅ! ኢትዮጵያዊነት ይድመቅ ሰላም ይሰበክ! እኩልነትና አብሮ መኖር ይለምልም!ኢትዮጵያ ከእነ ሁሉም ሕዝቦቿ ለዘለዓላም ትኑር!መልካምን የሰራ የፀጋ በር ክፍት ነው በለው!
Finxw says
Afandi finfinne galte dhala amara salu eegalte moo maal waan isaa dur nagaya qabda.
Banjaw says
Please don’t take time to criticize mentally sick individuals like (j)awar. Whose thinking emanates from their tongue not from their mind. I have a question that is he the one who is learning in that university?
Aref hasabe new yalamekeneyate sew mamot yelabetem yalefa alefa addis hasabe yenuran yekeretan enelemad manedela tekure hono bekeler lemayemasaselut lenachochu yekereta aderega ena gen aned ayenate kelare eyaalen ethiopiawe honen esekamache enegadadelen l says
Ebakachehu kesehetatachen enemar yalefa alefa selamenelek kemenawera ahun eyetadrega yalewen lemen anasekomeme ewenate lehezeb yemanesebkehona yemotu alefu memalese ayechalem ahun eyamotu yaluten enetadegachew
melese says
tiru ginzabe yemiset tsihuf silehone berta E/r yirdah.
zinabu says
berta temechitognal
ras kenny says
!ከማንም ቤተሰብ፣
ከየትኛውም ብሔርና የሃይማኖት ዕምነት
ተከታዮች ብትሆኑም ቤታችሁ፣ ሀብታችሁ፣
ቅርሳችሁ፣ መጠሪያችሁ፣ እናት ሀገር ኢትዮጵያ
ናት!
Abbaa says
Mantajaalasa Tawaarasa, Hoyahoye !!!!
dagny mekonnnen says
በጣም ልትመሰገን የምትገባ ኢትዮጵያዊ ነህ አነተ በቃ ሁሉ የምታውቅ ሰው ነህ አላህ ይባርክህ ለህዝብና ለሀገር እድገት ማሰብ ሲገባ .እነሱ አሜሪካና አውሮፓ እየተማሩና እየሰሩ ተመቺቶአቸው እየኖሩ በተለይ ባሁን ሰዓት የእለት ጉርሳቸውን ለመሙላት አቅቷቸው አላህን በፀሎት በሚለምኑበት ዘመን .የመተላለቅ ተልኮአቸውን ይዘው በየፓልቶኩና በየድረገፁ የሚበተኑት አፍራሽ ተልኮኦች በጣም ያሳዝናል .አንተ ሁሉንም ጨርሰህዋል አላህ ይባርከህ .ኢድ ሙባርክ በርታ ሁሉም ለራሱ ሆድና ዝና የሚሯሯጥ ነው.እነኝህን ሰዎች ደግሞ በጋራ እንዋጋቸዋለን.
Tom says
“ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት::”
You are very much better than those whom wrote and speak an ugly lies driven by their id and some stupid reasons. am expecting more articles worth reading from you
long live to u
temesgen tesfa says
Tom, ur quot makes me
good feeling!
temesgen tesfa says
“ለህዝቦች መብት የሚታገሉ ወገኖችና ቡድኖች ይኑሩ፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመብት ትግልና በርሱ ምክንያት ከሌላ አቅጣጫ የሚሰነዘረው ግብረ-መልስ ውላቸውን ስተው ሌላ አቧራ እንዳይቀሰቅሱ የመከላከሉን ስራ እንስራ፡፡ በህዝቦች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነትን እናጎልብት::”
“You are very much better than those whom wrote and speak an ugly lies driven by their id and some stupid reasons. am expecting more articles worth reading from you
long live to u”
Ibsa Harerge says
I will hung my self if I were JAWAR MEHAMED( the faciest)
Bariisoo says
The truth behind ones art is the integrity of the individual,those individuals who try to use their pen for revenge or serve others knowingly or unknowingly is deteriorating their integrity. It was very interesting to read Mutaqs writing, but this time he vomited every thing ,nothing left in his stomach.well,he forgot tomorrow is another day. who was your friend yesterday is your enemy today, who is your friend today will be your enemy tomorrow. Jawar is crowned as legitimate advocate of his nation, the mass is with him no one can snatch the mass from him.The flies can hoover over any body and rest over any body and affects no one.The dogs can bark, the donkeys can bray but the lion roars and the camels go their way.
Sisay mulu says
1.Ante poletikegna mehon atchilm.agul tewodajinet lemagignet yemtlefa silhonk 2.metsehet azegajim mehon atichilm wegentegna honeh sewochin tanquwashishalehna 3.jewarn beyifa achberbari wushetam yemesaselu wordoch texeqme metsafh berasu dekama mehonehn yasayal liju fitsum endalhone hulachinm binaqm ante endmataworawu aynet worada aydelem yih new agul tewodaj lememsel yemtaregewu xiret ersihn meles belh eyewu 4.sil ante agotna zemedochm bihon tarik kalachew tarik yastawusachewu enji ante ezih amxteh bemeteterkiln sid tsehuf teqeblen ante yasgebahewun wukipidia eyanebebn endnejajal agul lemewoded yemtaregewun xirethn qenseh erashn bitay 5.beterefe xiru tsehafi lithon silmtchil quwanqwhin ena wegentenganethn malet betewosenu girupoch lemewoded atxar ewunetn felfleh bemasreja kaqerebk manm yixlah yiwudedh yeyazkewu ewunet kehon motn amen bileh meqebel qelal new.
Tokkummaa says
Yaa diina barbadoofte!, Ummani Oromoo abshaallumaa keeysan kan qilee nama seensuuf yaaltaniin ergaa gowummaa lakisee turee bar. Caraaqiin kee Kayyoo Oromoon deemuuf kuffisuuf Jawaar irratti duula bante. Garruu jawaarota miiliyoonota attam gottaa? Armaan booda kaayyoo keena namni duwaan akka keetii mitii, qaamni guddaan rabii gadii dhufuu duubatti nun deebisu. Yeroo kee wonta Oromoo gowoomsitu irratti osoo gubuu dhiiystee! Yeroon sun ni darbee bar! kkkkkk
Fitsum says
I appreciate you next to Madiba!!!
God bless you.
Hagos says
I do not believe in racism but we all know Menilik was NOT 100% Amhara. He never led the Amhara liberation front or something like that. He never established ethnocenric army or government that favoured only one ethnic group over the rest. Many of his top generals were Amharas, Oromos, Tigres, etc. That was why he was supported by all ethnic groups and won the biggest war for black people against white suprimist European power. Despite his short comings, he had so many leadership qulities that all black people need to be proud of. Jawar’s effort to create unnecessary animosity between Amharas and oromos did not hold water. Oromos and Amharas are one people. Those that do not accept that are living in their own fantasy world. Thank you very much Afendi. This was an eye opener for me.
Tewodros says
ይህ ግለሰብ በዉሸት የተካነ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚዲያ እንደተንታኝ ሲደሰኩር እዉነት ያስመስላል እዉነታዉ ግን ግለሰቡ የኦነግ አባል ነዉ በአማራዉ ላይ ያለዉን ጥላቻ በግልጽ ያሳየ መሰሪ ነዉ ኦሮሞ በማንኟዉም መልኩ አትገነጠልም አቅሙም የላቸዉም
ችግሩ ዝም ብለን ስለምናያቸዉ ይመስለኛል እነሱ ግን አቅም ያላቸዉና የምንፈራቸዉ እየመሰላቸዉ ነዉ ከእንግዲህ እስኪበቃቸዉድረስ መናገር ነዉ
Tewodros says
Tokkummaa ቢያንስ በእንግሊዘኛ ጻፍ ቌንቌዉ ስለማይገባን የሚረዳህ ቢኖር ኦሮሞ ብቻ ነዉ
Beko says
Tewodros, yours language is also only understood by Amhara & its speakers. so make at least in English.
Arjoma says
I really believe in what has been said by Afendi but guys like you still have no info about the language spoken by huge natives in East Africa. Any way we Oromos are against extremist. We give a sheet to your call to be against TPLF for we know our ways to step forward.
Beko says
Afendi, I would like to thank you for such skilfull writings. For me, it is more than facts. but I would like to recommend you that such informative written documents must be publicized in other language especially Oromiffa language so that the more concerned groups may judge. Try to produce a certain literary on related areas at least in oromiffa & amharic. don’t Give up!
getuu says
obbolessa kiya diina wajjin afaan banun nafxanya senaa isanii halluun watakaa siin finduu …atuu gafaa huduu isanii arabdee quftee as debitaaa… marataa akkaa ati maratee galamsoo gutuu si bekaa. Jazbaa hoga nafxanyaa sibiraa dhabatee namaa obbolessa ke si arabsistu, atii wajjin iyyuu malee wantakka hin beytuu.. namni akamiti senaa kijibaa kan isaanu hin halle tochee kijibaa?? Jinni addareen maataa domsitee.. addaree si marachitee jirtii sirraa laluu…
Abdi says
Galatoomi nama dhiraa.
sol says
What a balanced writing again I appreciate your stand as an Ethiopian. Please keep on delivering such writing. May Allah bless you!!!!!!!!!!!!!!!!!!