ለዓመታት በአገር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) እንዳያሳይ የታገደው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ለማቅረብ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ። ችግሮቻችንን አራግፈን ወደፊት መጓዝ አለብን ብሏል። ዴይሊ ሜይል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ እንደዘገበው በእርሱ ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንዳለ ሆኖ ቴዲ “በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ” ትኩረት ማድረግ መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤቱ ዘና ባለ ሁኔታ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። የልጅነት ዘመኑን በማስታወስ ቴዲ ሲናገር፤ “ልጅ ሆኜ እንደ አንድ አገር ስንኖር አስታውሳለሁ፤ አንድ የምናውቃት አገር ኢትዮጵያ የምትባል ነበረች፤ አሁን በዚህ ዘመን ግን የምንታወቀው በዘራችን ነው፤ ይህ ደግሞ እጅግ አደገኛ እየሆነ መጥቷል” ብሏል። ህወሓት በቴዲ የጥበብ ሥራዎች ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በተለይ … [Read more...] about አስመራ ላይ የሙዚቃ ድግስ ማቅረብ – የቴዲ ተስፋ!