በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ። የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር። የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ … [Read more...] about በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች
Middle Column
በሚዲያ መረሳት ያስፈራል
“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው። ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች … [Read more...] about በሚዲያ መረሳት ያስፈራል
“በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”
“አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበት ክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩ አሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል? ክልሉን እንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል፣ ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ …” ሲል በስልክ ለጎልጉል አስተያየቱን ሰጠ። መናገር አይችልም፤ ሲቃ ልሳኑንን አንቆ ይዞታል። ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ያነሳል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው። በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ተረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች … [Read more...] about “በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”
ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው። በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ … [Read more...] about ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ
“በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል!”
ኤርትራ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታና ወቅታዊው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ልዕልና መላላት ተከትሎ የፖለቲካ ጨዋታው ጦዟል። በበርካቶች ዘንድ ኢሳያስ እንዳበቃላቸው ተደርጎም እየተወሰደ ነው። ኤርትራ ውስጥ ለውጥ ከተካሄደ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለው አጓጊ ጉዳይ የሁሉንም ትኩረት የሳበ አጀንዳ ሆኗል። ኢሳያስ ያሉበት የ"ፖለቲካ ኮማ" ድብታ ውስጥ የከተታቸውም ጥቂት አይደሉም። ኢሳያስን የደረሱበት የኮማ ጣጣ መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችና ወታደሮቻቸው የመጨረሻ እድል ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠራ መረጃ ባይሰጥም ሌላውና ዋናው የጡዘቱ አካል እንደሚሆን በርካቶች ይስማማሉ። በቅድሚያ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የሚጠቁሙም አሉ። ግን ምን አይነት ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት መፍትሄ የሚያቀርቡ የሉም። ዙሪያው ዝግ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራ ውስጥ … [Read more...] about “በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል!”
ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!
“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ" አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው "አቧራው ጨሰ" የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። "ህጻን እናሳድጋለን" እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ "አንቱ" የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር … በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ … [Read more...] about ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!
ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ወገኛ ድርጅት ነው። “ሲያደርጉ አይታ” እንደሚባለው እንደ ኤፈርት አይነት ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ከፈተ። ስሙንም ቱምሳ ኢንዶውመንት አለው። ቱምሳ የድርጅት ቅርጽና መልክ ተበጅቶለት ስራ ጀመረ። በበረሃ ትግል ወቅት በነበረን ሃብት መሰረትነው ለማለት ቀዳሚዎቹ የኦህዴድ ምልምሎች ሳንቲም አዋጡና ወደ ተግባር ገቡ። ቱምሳ በስሩ ዲንሾ ትሬዲንግ፣ ዲንሾ ትራንስፖርት፣ አግሮ ኢንዱስትሪና የንግስ ድርጅቱ የጀርባ አጥንት የሆነውን ቢፍቱ ገነማ የሚባል የጫት ንግድ አቋቋመ። የትራንስፖርት ዘርፉን ይመሩ የነበሩት የአቶ ኩማ ደመቅሳ ወንድም እንክት አድርገው በሉትና ከሰረ። ዲንሾ ንግድ ማዳበሪያ እነግዳለሁ ብሎ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንክ ተበደረና ታሪኩን በኪሳራ ደመደመው። ዲንሾ አግሮም ከእህት ኩባንያዎቹ እንደተማረው ኪሳራ ተከናንቦ መሬት … [Read more...] about ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!
መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል
በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡ (Photo: mesfinwoldemariam.wordpress.com) በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች … [Read more...] about መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል
“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”
/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት "የአስተዋይነት" ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል። ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል። በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት … [Read more...] about “ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”
በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር
የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤- ‹‹… የተለያዩ አፍቃሪ የአልቃይዳ ወኪሎችና አክራሪዎች ከአረብ ምድር እስከ አፍሪካ ብቅ እያሉ መጥተዋል፤ እነዚህ ቡድኖች ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ እንደዚያው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህንን አደጋ ለመቋቋምም በአስር ሺዎች የሚጠጉ ልጆቻችንን በመላክም ሆነ አገራትን መቆጣጠር አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም … [Read more...] about በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር










