በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው … [Read more...] about ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ
News
ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል። መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ … [Read more...] about ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!
“Are Ethiopians without a country?”
Press Release Washington, DC, November 11, 2013 SMNE Calls on the Saudi government to stop this brutal and inhumane treatment of the Ethiopian migrant workers immediately And on the TPLF/ERPDF regime to Protect Ethiopian Citizens in Saudi Arabia The Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE), a non-political and non-violent social justice movement of diverse people that advocates for freedom, justice, good governance and upholding the civil, human and economic rights of the people of … [Read more...] about “Are Ethiopians without a country?”
በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ
ኢትዮጵያ ግራ በሚያጋባና ሊተነበይ በማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ያመኑ የህወሃት ሰዎች መካካል የእርቅ ሃሳብ ላይ ለማተኮር እቅድ እንዲያዝ ሃሳብ ማንሳታቸው ተሰማ። ኢህአዴግ የቀድሞው የአፈና ገመዱ መንተቡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውና አለመተማመን መንገሱ ተጠቆመ። ለጎልጉል መረጃ በመስጠት የሚታወቁ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራርና ዲፕሎማት እንዳሉት ህወሃት ውስጥ "እርቅ አስፈላጊ ነው" በሚል እቅድ እንዲያዝና እንዲሰራበት ሃሳብ ቀርቧል። በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሃት ሰዎች የእርቅ ሃሳብ እንዲሰራበት ያቀረቡት ሃሳብ ግን በመደበኛ ስብሰባ አይደለም። በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ከመለስ ሞት በኋላ መበላሸቱ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ደረጃ የተፈጠረው ልዩነትና በሙስና ስም … [Read more...] about በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ
ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?
በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት "ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል። ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር … [Read more...] about ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?
ከእሁድ እስከ እሁድ
“መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤ መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤ በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ
ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ። አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት "አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል" በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት … [Read more...] about ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ
ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ "አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም" ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል። በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች "የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ … [Read more...] about ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ማንን እንመን ? ኢህአዴግ ሶማሌ፣ ትህዴን "ኢትዮጵያዊያን ናቸው" ይላል በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች እንዳልሆኑ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ አስታወቀ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ስማቸውም "ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው" ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል። የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችሁዋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ያመለከተው ዜና የሶስት ሰዎችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 ነው። በሌላ በኩል ኦክቶበር 16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የአዘርባዣኑ ኢህአዴግ
ትላንት ረቡዕ በአዘርባዣን የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነጻና ፍትሓዊ እንደማይሆን የብዙዎች ግምት ነበር፡፡ ከ10ዓመት በፊት ከአባታቸው ሥልጣን በውርስ የተረከቡት ፕሬዚዳንት ዒልሃም አሊዬቭ የጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በመገደባቸው የምርጫው ውጤት ምን እንደሚሆን ለመገመት ያዳገተ አልነበረም፡፡ እንደ ኢቲቪና ሬዲዮ በአገሪቷ መንግሥት የሚቆጣጠረውና ለገዢው ፖለቲካ መሣሪያነት የዋለ ሚዲያ በመኖሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የነጻ ንግግር ገደብ እንዳሳሰባቸው ሲጠቁሙ ቆይተዋል፡፡ ቢቢሲም የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡ ምርጫ ተካሂዶ ቆጠራው ከመፈጸሙ በፊት የአዘርባዣን ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን ለብልህስልኮች (smartphones) አዘጋጅቶ የለቀቀው ግብረታ (app) ፕሬዚዳንቱ በ72.76 በመቶ ማሸነፋቸውን የሚያሳይ ነበር፡፡ እኤአ በ2003 … [Read more...] about የአዘርባዣኑ ኢህአዴግ