* ኤርትራ በዚህ ወሳኝ ስብሰባ አለመገኘቷ ከባሕር ወንበዴዎች ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ ከባሕር ላይ ዘረፋ እና ከስደተኞች ሕገ-ወጥ ዝውውር ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመሮች መስተጓጎል ድረስ፣ የዓለምን አንዱን እጅግ ስራ የበዛበት የውሃ አካል የሚያዋስኑ ሀገራት በፍጥነት እየተለዋወጡ ካሉ የባሕር ላይ ስጋቶች ቀድመው ለመገኘት የቅርብ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ። የባሕር ላይ ውጥረቶች በከፊል መካከለኛው ምስራቅ ላይ በግልጽ እየታዩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት፣ የኢትዮጵያ፣ የየመን፣ የጅቡቲ እና የሶማሊያ የደህንነት ባለሥልጣናት ማንም ሀገር ለብቻው ሊወጣው ከማይችለው እያደገ ከመጣው ስጋት የቀይ ባሕርን እና የኤደን ባሕረ ሰላጤን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል የጋራ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ለመምከር በዚህ ሳምንት ናይሮቢ ውስጥ መሰብሰባቸውን የተባበሩት መንግሥታት … [Read more...] about ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ
Archives for August 2026
የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር በየዘርፉ የሚገርሙ ትዕይንቶች ይታያሉ። ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ጉዳዮች ይሰማሉ። አንዳንዶቹ መረጃዎች ደግሞ “መንግስት ሆይ የት ነህ?” የሚያሰኙ ናቸው። ፍትህን በጋራ ወይም ተቧድነው በተዋረድ የሚያዛቡ የማፍያ ይዘት ያላቸው ካድሬዎች በለውጥ ውስጥ ተሰግሰገው ከርመው አሁን አሁን በአደባባይ ቀና ብለው ከነካባቸው እየታዩ ነው። አቧራቸውን አራግፈው ከየስርቻው የወጡ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቅጥቅጦች ላይ መንግስት ከተፋዘዘ ህዝብ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ዕምነት እንዲያጣ ይገደዳል። ይህ ከስር የቀረበው ጉዳይ ስንጣሪ ማሳያ ነው። ጉዳዩን አዝረጥርጠን ያላቀረብነው ያልተቋጩም ጉዳዮች ስላሉ ነው። አዶር አዲስ ሆቴል የማን ነው? ባለቤቶቹን የፍርሃት ቆፈን ውስጥ የጣላቸው “የብሌን ዓይኑ ሰራዊት” ይህ ብዙም ሳይጋፋ፣ ባለው መረጃ መሰረት ጠልቆ ሳይሄድ ለጥቆማና ለማንቂያ … [Read more...] about የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ


