ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። አትወለድ ይቅር Download “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about አትወለድ ይቅር!
Archives for January 2020
እንዴት ከዘቀጥንበት ወጥተን ወደ ፊት እንራመድ?
ባለፉት ወራት ባገራችን የተከሰተውን አሳዝኝና ትርጉም የለሽ ግድያን በተመለከተ የተለያዩ የመንግሥትና የግል ሚዲያ ተቋማት በየፊናቸው ያስተላልፉ የነበረውን ዜና ከያለንበት ሆነን ስንሰማውና በቴሌቪዥን መስኮቶቻችን ስንመለከተው እንደነበር ይታወሳል። አዎ! ሰዎች በግልጽ በአደባባይ እየተቀጠቀጡ ሲገደሉ አይተን በእጅጉ አዘንን። እጅግ በጣም አሳዛኝና ምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ባልተፈጠርኩ የሚያሰኝ የጭካኔ ጣራ የታየበት ዓመት! በወጣትነት ዘመናችን ሲነገረን የነበረውና እኛም እንደወረደ ስንጋተው የነበረው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ ባህሉን አክባሪና ከሁሉም ጋር ተስማምቶ በፍቅር ኗሪ፣ የደከመውን የሚያበረታታና ያዘነውን የሚያጽናና፣ ፈሪሃ እግዚአብሄርን በመላበሱ በአምላክ ፍጡር ላይ ጉዳትን የማያደርስ ቅዱስ ሕዝብ ወዘተ የሚባለው ባሕላዊ እሴቶቻችን ወዴት እንደተነኑ በበኩሌ አልገባ ካለኝ ውሎ … [Read more...] about እንዴት ከዘቀጥንበት ወጥተን ወደ ፊት እንራመድ?
አቶ ለማ መገርሳ – በህወሃት የማስፈራሪያ አጣብቂኝ ውስጥ
ከለውጡ ሾፌሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ የሽግግሩ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ጃዋር መሐመድ አጥብቆ ሲከራረከር ነበር። አቶ ለማ የፌዴራል ፓርላማ ተወካይ ባለመሆናቸው እርሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳይሆኑ የሚከለክላቸው መሆኑ የታወቀ ቢሆንም በወቅቱ ግን ጃዋር ከጓደኞቹ እነ ሕዝቅኤል ገቢሣ ጋር በመሆን “ኢህአዴግ አዲስ መመሪያ/ሕግ አውጥቶም ቢሆ አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያደርጋቸው ይገባል” በማለት ሃሳብና መመሪያ ቢጤም ሲሰጥ ነበር። ጃዋር ያለውና ያሰበው ሳይሆን አቶ ለማ በለውጡ ሙቀት ውስጥ ባሉበት ወቅት “እኔና ዐቢይን ሞት ብቻ ነው የሚለየን” በማለት የድርጅት ሊቀመንበርነታቸውን ለዶ/ር አብይ አሳልፈው በመስጠት ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን የበኩላቸውንና ድርጅታዊ ኃላፊነታቸውን ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው እውን አደረጉ። የሆሮ ጉድሩ … [Read more...] about አቶ ለማ መገርሳ – በህወሃት የማስፈራሪያ አጣብቂኝ ውስጥ
“የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
መረራ - ሲያልቅ እጅ ሰጡ!! ኦነግን ይዞት በነበረው አቋም አማካይነት ፍጹም እንደማይነሳ አድርገው የቀጠቀጡት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ናቸው። “ኦሮሞ ግንድ እንጂ ቅርንጫፍ አይደለም ” ሲሉም የኦሮሞን አካታችነትና ታላቅ ሕዝብነት በማስረገጥ የጎጥ ፖለቲካ ረብ የለሽ መሆኑንን በጥናት አስደግፈው ኦነግን ያኮሰሱት መረራ፤ ኦነግ ውጤት እንደማያመጣም ተናግረው ነበር። ዛሬ ግን “ተመልሰው ለኦነግ እጅ ሰጡ” ሲሉ ወዳጆቻቸው ሳይቀሩ እየወቀሷቸው ነው። የአምቦ ክፋይ በሆነችው ጊንጪ የተለኮሰው የኦሮሞ ትግል አድማሱን አስፍቶ ወደ ሌሎች ክልሎችም ተስፋፍቶ በጥምረት ለውጤት ሲበቃ፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲንከላወስ የነበረውና ተፈረካክሶ በየአቅጣጫው የተበተነው የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ቤት “በጀግንነት” የመግባት ዕድል ተጎናጸፉ። እናም የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው የጠመንጃውንና … [Read more...] about “የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
ኢሕአፓ ለምን ተከፈለ? ዛሬስ ምን መደረግ አለበት?
በዚህ ርዕስ አጭር ጽሁፍ መፃፍ ከባድ ነው፡፡ ኢሕአፓን ያህል አንጋፋ ድርጅት ለመከፈል ብዙ ውጣ ውረድ፣ ውይይት፣ ንትርክ፣ ተደርጎበት በወቅቱ የነበሩትን አባላት አሳዝኖ የተከሰተ ሂደት ነው፡፡ በኢሕአፓ ታሪክ ተወደደም ተጠላ ይህ የመከፈል ጉዳይ በመጽሐፍ መልክ እንኳ ቢቀርብ እንዴት ነፃ ሆኖ ይቀርባል? የሚለው ይፈታተናል፡፡ ያም ሆነ ይህ መፃፉ አይቀርም፡፡ ለምን ተከፈለ? እንዴት ተከፈለ? ዋናው ምክንያት ምንድነው? ሂደቱስ? ኢሕአፓን ያህል ተመክሮ ያለው ፓርቲ እንዴት የቅራኔ አያያዝ ጥበቡ፣ ዕውቀቱ አነሰውና ለዚህ አሳፋሪ ድርጊት እጁን ሰጠ? ሂደቱ ከተከሰተም በኋላ መከፈሉን የሰሙ ደጋፊዎቹ፣ የቀድሞ አባላቱ እንደገና አንድ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ምነው ሳይሳካ ቀረ? ወዘተ. መልሱ እንኳንስ ሀገር ቤት ላሉት የኢሕአፓ የቀድሞ አባላት፣ ደጋፊዎችና ቤተሰቦች ሌሎችም ይቅርና ሲከፋፈል … [Read more...] about ኢሕአፓ ለምን ተከፈለ? ዛሬስ ምን መደረግ አለበት?