በዚህ ርዕስ አጭር ጽሁፍ መፃፍ ከባድ ነው፡፡ ኢሕአፓን ያህል አንጋፋ ድርጅት ለመከፈል ብዙ ውጣ ውረድ፣ ውይይት፣ ንትርክ፣ ተደርጎበት በወቅቱ የነበሩትን አባላት አሳዝኖ የተከሰተ ሂደት ነው፡፡ በኢሕአፓ ታሪክ ተወደደም ተጠላ ይህ የመከፈል ጉዳይ በመጽሐፍ መልክ እንኳ ቢቀርብ እንዴት ነፃ ሆኖ ይቀርባል? የሚለው ይፈታተናል፡፡ ያም ሆነ ይህ መፃፉ አይቀርም፡፡ ለምን ተከፈለ? እንዴት ተከፈለ? ዋናው ምክንያት ምንድነው? ሂደቱስ? ኢሕአፓን ያህል ተመክሮ ያለው ፓርቲ እንዴት የቅራኔ አያያዝ ጥበቡ፣ ዕውቀቱ አነሰውና ለዚህ አሳፋሪ ድርጊት እጁን ሰጠ? ሂደቱ ከተከሰተም በኋላ መከፈሉን የሰሙ ደጋፊዎቹ፣ የቀድሞ አባላቱ እንደገና አንድ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ምነው ሳይሳካ ቀረ? ወዘተ. መልሱ እንኳንስ ሀገር ቤት ላሉት የኢሕአፓ የቀድሞ አባላት፣ ደጋፊዎችና ቤተሰቦች ሌሎችም ይቅርና ሲከፋፈል ለነበሩት አባላት እንኳ ያስደመመ ጉዳይ ነው፡፡
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply