ብቅ ብቅ ባለ ሣር የተሳበ በሬ፡አፏን ከከፈተች መሬት ይተርፍ ይሆን! ለምን ሕዝባዊ ትግል አስፈለገ?መስዋዕትነቱስ የሚከፈለው ምንስ ለመቀዳጀት ይሆን? ህይወት፤ ዕውቀት፤ጊዜና ገንዘብለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። የሰው ልጅ እነዚህን መሠረታዊ ሀብቶቹን አሳልፎ መስጠት ካለበት በአንጻሩ ብልጫ ያለው ካልሆነም ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መሻት ይገባዋል። ብሶት ብዙ ጊዜ የሚፈጥረው ትግል፤ በአግባቡ ካልተደራጀና ከታች ወደ ላይ ከላይ ወደ ታች በሚንቀሳቀስ አካሄድ ካልተመራ፣ትግሉ ያልተቀነባበረና ግብታዊነት የሰፈነበት ይሆናል።በንቃት የተደራጀ ከሆነ ቀጣዩን ትግል መልክ ለማስያዝ ጠንካራ ድርሻ ይኖረዋል። በዚህ መልክ ትግሉ ከተመራ የሚከፈለው መሰዋዕትነት በዉጤት የጎመራ ይሆናል። እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ዐብይ ጉዳይ በተበታተነ መልክ ለሚደረግ ትግል የሚከፈለውመሰዋዕትነት … [Read more...] about የትግላችን መነሻና መዳረሻ ምንድነው?
Archives for March 2018
የዶ/ር አብይ አህመድ ፈተናዎች
እርግጥ እንደ መለስ ዜናዊ ባለ ሙሉ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል? ከልክ በላይ ለጥጠው፤ እንደ ልብ አንጠልጥል ፊልም ያቆዩትን ፍትግያ ትናንት በዜና ሲሰብሩት ደስታቸውን ይገልጹ የነበሩት ዜጎች ጥቂት አልነበሩም። ወትሮውን በስብሻለው ከሚለን ስራዓት አዲስ ነገር የሚጠብቅ ተስፈኛ ቢደሰት ብዙም አይደንቅም። የጠቅላይ ሚንስትር እንጂ የስራዓት ለውጥ መች ተመለከትን? ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ ቀውጢ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጡ ግን ከክብሩና ከስልጣኑ ይልቅ ፈተናው ያመዝናል። ለሶስት ቀናት ተብሎ የተጀመረው ግብግብ ይሉት ክርክር በተነገረለት ቀን መቋጨት ያለመቻሉ በራሱ የሚነግረን ነገር ነበር። አወዛጋቢው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ፣ ፓርላማ ላይ በጸደቀበት ወቅት ዶ/ር አብይ በስፍራው ባለመገኘታቸው የህወሃት ሰዎች ክፉኛ እንደተበሳጩ አይተናል። ይህንን ቅሬታ በብሎገሮቻቸውም … [Read more...] about የዶ/ር አብይ አህመድ ፈተናዎች
የHR 128 እና የማግኒትስኪ ሕግ ትሥሥር፤ የህወሓት ፍርሃቻ!
ተጨማሪ መረጃ፤ ያለፈው ሳምንት መገባደጃ አካባቢ የኮሎራዶ 6ኛው ወረዳ እንደራሴ ማይክ ኮፍማን በድረገጻቸው እንዳስታወቁት HR 128 በኤፕሪል ወር ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ድምጽ ይቀርባል ብለዋል። ጉዳዩን ከሚከታተሉ በርካታ ወገኖች መካከል የቅርብ መረጃ ያላቸው አቶ ኦባንግ ሜቶ የቀጠሮው ቀን ኤፕሪል 9 (ሚያዚያ 1) መሆኑን በፌስቡክ ገጻቸው በለቀቁት መረጃ አስታውቀዋል። ይህ ረቂቅ ጸድቆ በሕግ እንዲወጣ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ የሚገኘውን የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግብረኃይል ፌስቡክ ገጽ በመሄድ ለረቂቅ ሕጉ እንዴት ድጋፍ መስጠት እንደሚቻል የበለጠ መረጃ ማግኘት ይቻላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፈው “ህወሓት፡ የHR 128 ፍርሃቻ እና የማግኒትስኪ ሕግ” የሚለውን ዘገባ በድጋሚ አቅርበናል። ይህ ዘገባ ህወሓት ለምን ረቂቅ ሕጉን እንደፈራውና እጅግ በርካታ ገንዘብ በማፍሰስ ለማጨናገፍ … [Read more...] about የHR 128 እና የማግኒትስኪ ሕግ ትሥሥር፤ የህወሓት ፍርሃቻ!
Ethiopia arrests 11 journalist, bloggers and activists
AHRE has found that 11 journalists, bloggers and activists arrested during the weekend, including recently released political prisoners, On March 25 2018, Ethiopian Police and Security forces arrested journalists Eskindir Nega and Temesgen Dessalege, activists Andualem Arage, Addisu Getinet, Yidnekachewu Addis, Sintayehu Chekol, Tefera Tesfaye and Woynshet Molla, and bloggers Mahlet Fantahun, Befiqadu Hailu, Zelalem Workagegnhu, and Fekadu Mehatemework, Their arrest was ordered by the Command … [Read more...] about Ethiopia arrests 11 journalist, bloggers and activists
ሲመቱት ይጠብቃል
የኢትዮጵያ ህዝብ ለበርካታ ዓመታት የሚገባውን እንደዜጋ በነፃነት የመኖር መብት ለመጎናፀፍ ያደረገው ጥረት ሁሉ በአምባገነኖቹ እየተዳጠ አሁን ላለበት ዝቅተኛ ኑሮና ለከት ያጣ ግፍ ተዳርጓል። የግፉ ፅዋ ሞልቶ መፍሰስ በመጀመሩም ከአስከፊው ስርዓት ጨርሶ ለመላቀቅ በተለይ ባለፉት ሶስት ዓመታት እልህ አስጨራሹን ትግል ተያይዞታል። የአሁኑ ትግል ካለፉት በብዙ መልኩ የተለየ ነው። ህዝባዊ አመፁ ሰከን ያለና ህዝቡን ከዳር ዳር ያሳተፈ ለአምባገነኖቹ ጨርሶ ያልተመቸ፣ ግፈኛውን አገዛዝ ቀስ በቀስ እየደማ እንዲሞት የሚያደርግ ነው። ፈረንጆች ሚስማር ሲመቱት እያደር ይጠብቃል እንዲሉ፤ ባለመዶሻው ወያኔ የህብረተሰቡ አንጓ የሆኑትን ራስ ራሳቸውን መታሁ ሲል የበለጠ ማህበራዊ ትስስሩንና የትግሉን ሂደት ሲያጠብቁት እናያለን። አማራውን በጠላትነት በፕሮግራሙ ነድፎ ከሌላው ህብረተሰብ ጋር በማቃቃር … [Read more...] about ሲመቱት ይጠብቃል
“የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች
የአስራ ሰባት ታዋቂ ኦሮሞ ሙስሊሞችን ስም ለማስረጃነት አቅርቧል ከዝርዝሩ ውስጥ የዶ/ር አቢይ አህመድ ስም ይገኝበታል ህወሓት ከፊቱ የተጋረጠበትን የፖለቲካ ቀውስና ቀውሱን ተከትሎ ከጌቶቹ የተነሳበትን ተቃውሞና ግፊት አቅጣጫ ለማስቀየር ሃይማኖትን የተንተራሰ ስልት ተግባራዊ ማድረጉ ተሰማ። የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አገሪቱን ለእስልምና አክራሪ አሳልፎ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ህወሓት በወኪሉ በኩል ስም ዘርዝሮ አቅርቧል። የጎልጉል ዲፕሎማት የመረጃ አቀባዮች ከዋሽንግቶን ዲሲ እንዳስታወቁት ህወሓት አሁን የተነሳበትን ዙሪያ ገጠም ተቃውሞ ከእስልምና አክራሪነት ጋር በማቆራኘት የአስራ ሰባት ኦሮሞ ሙስሊም ታዋቂ ፖለቲከኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ወዘተ ስም ዘርዝሮ ነው ያቀረበው። ዙሪያው ገደል የሆነበት ህወሓት የስም ዝርዝሩን ባቀረበ ጊዜ ራሱን የክርስቲያን መንግሥት አድርጎ … [Read more...] about “የክርስቲያን አገር በሆነችው ሙስሊሞች ሊነግሡባት ነው” ህወሓት ለአሜሪካ እንደራሴዎች
ድምጽ የመስረቅ አባዜ
አይን እና እግር ያወጣ ውሸት ሲሰማና ሲታይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። "ጨፍኑ እናሞኛችሁ" አይነት ንቀት ግን አሁን ላይ ፈሩን እየለቀቀ ይመስላል። ወያኔ እንደለመደው በአደባባይ ህግ አፍርሷል። ይህ ስርዓት ራሱ ያላከበረውን ህገ-መንግስት ሌላው ሕዝብ እንዴት አድርጎ ሊያከብርለት ይችላል? ሃገሪቷን በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሚያስገባ ሕግ ወጥ አዋጅ በተጭበረበረ ድምጽ ዛሬ አጽድቀዋል።ይህ በታሪክ መዝገብ ላይ ከሚሰፍሩ የጨለማ ቀናት አንዱ ነው። የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም፣ 122ኛው የአድዋ በዓል ከወትሮ ለየት እና ደመቅ ብሎ ተከብሯል። ይህ ቀን ለወያኔ ምኑም አልነበረም። ህወሃት የአድዋ ድል ቢቻል ባይነሳ ይመርጣል። ሃገሪቷን እየጠላ፣ ታሪኳን እያንቋሸሸ፣ ሕዝቧን እየገደለ የሚገዛ ስርዓት። ጭንቅ ሲይዘው፣ የባንዲራ ቀን ማክበር እንደጀመረ ሁሉ፣ አድዋም ዘንድሮ እንዲከበር … [Read more...] about ድምጽ የመስረቅ አባዜ
“እምቢተኛውን” ኦህዴድ በመርዝ ወይስ በመሰንጠቅ?
“ስንደመር እናሸንፋለን፣ አንድ ካልሆን እንጠፋለን” የለማ መገርሳ ተማጽንዖ!! ኦህዴድ በድንገት ያካሄደውን “ስትራቴጂክ” የተባለ የአመራር ሽግሽግ አስመልክቶ ለማ መገርሳ በሰጠው መግለጫ በተደጋጋሚ “አንድ ካልሆንን እንጠፋለን፤ ስንደመር እናሸንፋለን” ማለቱን በማስታወስ ህወሓት ኦህዴድን ለመበተን እየሠራ መሆኑን በተደጋጋሚ ለጎልጉል መረጃ የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰዎች ተናገሩ። ወታደራዊ አገዛዙ በትሩን በኦህዴድ አመራሮች ላይ እያሳረፈ ነው። የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ የመረጃ ሰዎቹን ዋቢ በማድረግ እንደገለጸው የኦህዴድ መፍጠን ህወሓትን አበሳጭቷል። በድንገት ኦህዴድ ሽግሽግ ከማድረጉ በፊት የህወሓት ቅርብና ታማኝ የሚባሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላትን አባርሯል፤ አግዷል። እንዲሁም ዝቅ በማድረግ አቅም አልባ አድርጓቸዋል። የማጽዳቱ ሥራ ጅምር እንደሆነና ወደፊትም … [Read more...] about “እምቢተኛውን” ኦህዴድ በመርዝ ወይስ በመሰንጠቅ?
State of Emergency in Ethiopia! A Constitutional Coup D’état?
Introduction What an eventful and an emotional roller-coaster ride February 2018 was in Ethiopia. First, the Oromo People’s Democratic Organization (OPDO) released a groundbreaking and a far-reaching statement. Then the Oromo population, led by the Oromo youth group, Qeerro, staged a hugely successful market boycott along with political rallies throughout Oromia. Within the second day of the Qeerro’s action, the Ethiopia government released thousands of political prisoners, including prominent … [Read more...] about State of Emergency in Ethiopia! A Constitutional Coup D’état?