አይን እና እግር ያወጣ ውሸት ሲሰማና ሲታይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። "ጨፍኑ እናሞኛችሁ" አይነት ንቀት ግን አሁን ላይ ፈሩን እየለቀቀ ይመስላል። ወያኔ እንደለመደው በአደባባይ ህግ አፍርሷል። ይህ ስርዓት ራሱ ያላከበረውን ህገ-መንግስት ሌላው ሕዝብ እንዴት አድርጎ ሊያከብርለት ይችላል? ሃገሪቷን በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሚያስገባ ሕግ ወጥ አዋጅ በተጭበረበረ ድምጽ ዛሬ አጽድቀዋል።ይህ በታሪክ መዝገብ ላይ ከሚሰፍሩ የጨለማ ቀናት አንዱ ነው። የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም፣ 122ኛው የአድዋ በዓል ከወትሮ ለየት እና ደመቅ ብሎ ተከብሯል። ይህ ቀን ለወያኔ ምኑም አልነበረም። ህወሃት የአድዋ ድል ቢቻል ባይነሳ ይመርጣል። ሃገሪቷን እየጠላ፣ ታሪኳን እያንቋሸሸ፣ ሕዝቧን እየገደለ የሚገዛ ስርዓት። ጭንቅ ሲይዘው፣ የባንዲራ ቀን ማክበር እንደጀመረ ሁሉ፣ አድዋም ዘንድሮ እንዲከበር … [Read more...] about ድምጽ የመስረቅ አባዜ
state of emergency
ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካፀደቀ የህወሃትን ገመድ በአንገቱ ላይ በገዛ እጁ እንዳሰረ ይቆጠራል
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፤ የህወሃት የወታደራዊ አገዛዝ አዋጅ ማለት፤ እንኳን የሰው ልጁ እንስሳትም ቢሆኑ አንገታቸው ላይ ገመድ ሊታሰር ሲል በፀጋ አይቀበሉም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመላ ኢትዮጵያውያን ያልተደገፈና ከውጭ አገራትም ሆነ ከአለም አቀፍ ድርጅቶችም ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳበት መሆኑ በሚገባ ይታወቃል። የአዋጁ ዋና ዓላማ ህወሃት በኢትዮጵያ ሕዝብ የተነሳበትን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ፤ በኦህዴድና ብአዴን እየተነሳ ያለውን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ትግልን ለማጨናገፍ፤ ኦህዴድና ብአዴን የህወሃትን የበላይነት ለማስወገድ ከክልላቸው ሕዝብ ጋር ተቀራርበው ለመስራት የሚያደርጉትን ጥረት ለማደናቀፍ እና ለህወሃቶችና ለሸሪኮቻቸው አገሪቷን የመዝረፍ ዘመቻቸውን በስፋት የሚቀጥሉበትን መንገድ ለማረጋገጥ ነው። ይህ አዋጅ የአገር ወይም የሰፊው ሕዝብ ደህንነት አዋጅ ሳይሆን የጥቂቶችን የበላይነት … [Read more...] about ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካፀደቀ የህወሃትን ገመድ በአንገቱ ላይ በገዛ እጁ እንዳሰረ ይቆጠራል