• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካፀደቀ የህወሃትን ገመድ በአንገቱ ላይ በገዛ እጁ እንዳሰረ ይቆጠራል

February 25, 2018 04:30 am by Editor 2 Comments

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፤ የህወሃት የወታደራዊ አገዛዝ አዋጅ ማለት፤ እንኳን የሰው ልጁ እንስሳትም ቢሆኑ አንገታቸው ላይ ገመድ ሊታሰር ሲል በፀጋ አይቀበሉም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመላ ኢትዮጵያውያን ያልተደገፈና ከውጭ አገራትም ሆነ ከአለም አቀፍ ድርጅቶችም ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳበት መሆኑ በሚገባ ይታወቃል። የአዋጁ ዋና ዓላማ ህወሃት በኢትዮጵያ ሕዝብ የተነሳበትን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ፤ በኦህዴድና ብአዴን እየተነሳ ያለውን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ትግልን ለማጨናገፍ፤ ኦህዴድና ብአዴን የህወሃትን የበላይነት ለማስወገድ ከክልላቸው ሕዝብ ጋር ተቀራርበው ለመስራት የሚያደርጉትን ጥረት ለማደናቀፍ እና ለህወሃቶችና ለሸሪኮቻቸው አገሪቷን የመዝረፍ ዘመቻቸውን በስፋት የሚቀጥሉበትን መንገድ ለማረጋገጥ ነው። ይህ አዋጅ የአገር ወይም የሰፊው ሕዝብ ደህንነት አዋጅ ሳይሆን የጥቂቶችን የበላይነት ለማስጠበቅ የታለመ አዋጅ ነው። ምክንያቱም በቅርቡ እንኳን እንደተረጋገጠው የፌደራል የፀጥታና የመከላከያ ኃይል በማይኖርበት ጊዜ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉንም ይሁን ተቃውሞውን አሳይቶ በሰላም ወደ ቤቱ እንደሚመለስ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች በግልፅ የሚታወቅ ነው። በአብዛኛው ረብሻና ግጭት የሚቀሰቅሰው የአጋዚና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በሚያዳርጉት ግድያና ትንኮሳ ምክንያት ነው።

ያለምንም ጥርጣሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የህወሃትን የዘረፋና የግፍ አገዛዝ ለማስቀጠል የታለመ ነው። ህወሃት ከዚህ በፊት እንደለመደው ብአዴንና ኦህዴንን በመጠቀም የበላይነቱን የሚያስጠብቅበት የፖለቲካ ቁማርና ጫወታ መቀጠል ባለማቻሉ አሁን ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም የበላይነቱን ለማስጠበቅ ነው። ይህንን ህወሃትና የህወሃት የጦር አለቆቹ ከፈለጉ በቀጥታ ያድርጉት እንጂ ፓርላማውን መጠቀም አይኖርባቸውም፤ ወታደራዊ አገዛዙ በግልፅ እንዳይወጣ ፓርላማው ሽፋን ሊሰጥ አይገባውም። በአለማችን ታሪክ የወታደራዊ አገዛዝ እንዲመሰረት የወሰነ ፓርላማ ቢኖር አንድ ብቻ ነው። እሱም እኤአ በ1933 የጀርመኑ ሬችስታግ የናዚ ፓርቲ ጀርመንን በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንድትሆን ለሂትለር የሰጠው ድምፅ ነው። ይህም በአለማችን ላይ ያደረሰውን እልቂትና ጥፋት ሁልም የሚያውቀው ነው። በኢትዮጵያም ፓርላማው ይህንን የእልቂትና የጥፋት መንገድ ለህወሃቶች ለማፅደቅ ድጋፉን በእጁ ከሰጠ፤ ከአሁን በኃላ በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ለሚፈሰው ደምና ለሚደርሰው ጥፋት የፓርላማው አባላቶች ቀጥተኛ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ምንም ሊያጠራጥር አይገባም። ሕዝብን ጨፍጭፉ ብሎ ሕግ ማፅደቅ ታላቅ ወንጀል ነው። በታሪክ እንዳየነው በግፍ ሕዝብ በሚጨፈጭፍበት ወቅት ከጨፍጫፊው ተኳሽ ወታደር በላይ ጭፍጨፋው እንዲፈፀም ሕግ ያወጣውና ትእዛዝ የሰጠው ዋና ተጠያቂ ነው።

የህወሃት ዓላማ በጣም ግልፅ ነው። ህወሃት በተግባር እያደረገ ሆነ እያቀደ ያለው የፓለቲካ ምእዳሩን ለማስፋት ሳይሆን እንዴት የፖለቲካ ምእዳሩን የሚያጠብበትንና የሕዝቡን፣ የብአዴንና የኦህዴድን ተቃውሞ የሚጨፈልቅበት ዘዴ ነው። ህወሃት ምንም የዓላማና የአቋም ብዥታ የለበትም። ህወሃት ዓላማውን ጠንቅቆ የሚያውቅና ለዓላማውም በፅናት በቡድንና በግለሰብ የሚሰራ ድርጅት ነው። በቅርቡ አባይ ፀሃይ እንደተናገረው በእኩል ተጠቃሚነት ላይ ስምምነት ከማድረግ ኢህአዴግ ቢፈርስ እንደሚሻል የህወሃትን አቋም ሳይደብቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ አድርጓል። ህወሃት የበላይነቱን ለማስጠበቅ የማይፈነቅለው ዘዴ የለም። ማታለል፣ መለመን፣ ማጭበርበር፣ መደለል፣ ማስፈራራት፣ ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል የታወቁ ዘዴዎቹ ናቸው። ይህ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ የፖለቲካ ምእዳሩን ለማስፋት ይጠቅማል ብሎ የሚያስብ የፓርላማ አባል ካለ፣ ከእንስሳቶች የተሻለ ደመ ነፍስ የሌለው ሰው ብቻ ሊሆን ይችላል። የፖለቲካ ምእዳር የሚሰፋው ሕዝብን በማስፈራራትና አገርን በሙሉ እስር ቤት በማድረግ አይሆንም። ይህ ሂትለር የናዚን የፋሺዝም አገዛዝ ለመመስረት የሄደበት አይነት መንገድ ነው። ሰው ላይ መሣሪያ ደግኖ ነፃ ውይይት ማድረግ አይቻልም። በእስር ያለ ሕዝብ የፖለቲካ ምእዳር ለማስፋት የሚያስችል ነፃ ውይይት ለማድረግ አይችልም።

በቅርቡ በግፍ ታስረው ለተፈቱ ለነበሩ ታጋዮቹና ጀግኖቹ ሕዝቡ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድጋፉን ያሳየበትና አቀባበሉን ያደረገበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሚዲያዎቻና በዲፕሎማቶች ዘንድ እጅግ የተደነቀና የተዘገበ ጉዳይ ሲሆን፤ ህወሃትን ደግሞ በአለም አቀፍ መድረክ እርቃኑን ያሰቀርው ጉዳይ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አንዱ ዓላማም ይህንን ህወሃትን በአለም አቀፍ ደረጃ እርቃኑን ያስቀረውን ዓይነት የሕዝብ ተቃውሞ በግልፅ እንዳይታይ ነው። ነገር ግን ከአሁን በኃላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍርሃት ለህወሃት የማይገዛበት ደረጃ ላይ የደረሰ ስለሆነና ሰላማዊ ተቃውሞውንም የሚቀጥል በመሆኑ ፓርላማው ህወሃት ሕዝቡን እንዲጨፈጭፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ማፅደቅ ታላቅ ወንጀልና ፀረ – ሕዝብ ድርጊት ይሆናል።

የአማራና የኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት ዓላማ በኦሮሞና በአማራ መሀከል ጎጂ ንትርክ ሳይሆን ጤናማ ውይይትና ትብብር የሚጎለብትበትን መንገድ የሚያበረታቱ ሀሳቦችን በማፈላለግና በማሰራጨት፤ በኦሮሞና በአማራ የፖለቲካ ልዒቃንና አክቲቪስቶች መሀከል የሚደረገው ያለፈ ታሪክ ንትርክን በተመለከት የታሪክ ባለሙያዎች በሰለጠነ መንገድና በመከባበር እንዲወያዩበት የሚገባ መሆኑን እያበረታታ። በአሁኑ ወቅት የአማራና የኦሮም የፓለቲካ ልዒቃንና አክቲቪስቶች በአንገብጋቢው የወቅቱ የፓለቲካ ጉዳይ ላይ በማተኮር የህወሃትን አገርንና ሕዝብን የሚያጠፋ ድርጊት ለመቋቋም የሚችሉበትን ጠንካራ ትብብር የሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ነው። በመተሰሳሰብና በመከባበር ላይ የተመሰረት ትብብርና አንድነት ቀጣይ፣ እውነተኛና ጠንካራ ኃይል ይሆናል። ተያይዞ ከመውደቅ ተያይዞ መነሳት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይበጃል።

የአማራና ኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት

AOCPP (Amhara and Oromo Cooperation Promotion Project)

Contact: aocpp2016@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column, state of emergency, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    February 27, 2018 07:53 pm at 7:53 pm

    ትግሉን መቀጠል እንጂ ሌላ አማራጭ የለም።
    ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን አሁን ሦስቱ እጩዎች ታውቀዋል፡፡
    #ሽፈራው_ሽጉጤ (ከ ደኢህዴን)
    #ደመቀ_መኮንን (ከ ብአዴን)
    #አብይ_አህመድ (ዶ/ር) (ከ ኦህዴድ)
    እጩ የማያቀርበው ህወሓት የሚሰጠው ድምጽ ጠቅላይ ሚንስትር ማን እንደሚሆን የሚወስን ይሆናል፡፡ አይገርምም?
    ህወሓት ሽፈራው፣ እንደ ኃይለማርያም የህወሓት ሎሌ ነው። ደመቀ አቅም የለውም። በረከት ኢትዮሚድያ ዛሬ በለቀቀው ደብዳቤው ላይ አቢይ አህመድን አጣላልቶ ጽፏል።

    አንድ ነገር ግልጽ ነው፤ ግልጽ ይደረግ። ህወሓት በኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥና በፓርላማ ከኦህዴድ፣ ከአማራና ከደቡብ እኩል አባላት አሉት። በማ/ኮ = 9። በፓርላማ = 45። ይህ ህገወጥ ተግባር ብቻውን ሦስቱን ጥለው መውጣታቸውን ግድ ይላል። አሁን የትግሉ ድርሻና ኃላፊነት ከህወሓት/ኢሕአዴግ እጅ ወጥቷል። ሕዝቡ እጅ ገብቷል። ስለ ብሔር በማውራት ጊዜ አናጥፋ። እከሌ እንዲህና እንዲህ እያልን ጉልበት አንፍጅ። ነገሮችን ቀላልና ግልጽ አድርገን እንያዛቸው።
    1/ የአገሪቷ በጀት ምዳቤ ልኩ በሕዝብ ብዛት መሆኑ ነው፤ ኦሮምያና ትግራይ እኩል በጀት ሊኖራቸው በምንም ሚዛን አይችሉም፣ አይገባም።
    2/ የትግራይ ተወላጆች በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በአፋር፣ በኦሮምያ፣ በአዲስ አበባ ንግድ ማንቀሳቀስ ሲችሉ፣ ለዚያውም ትርፋቸውን ካካበቱበት ሥፍራ ላይ ኢንቬስት እንደማድረግ ለትግራይ ልማት ሲያውሉና ውጭ አገር ሲያሸሹ፣ ሌላው ተመልካች መሆን አይገባም። የየክልሉ መስተዳደር ይህን ማስቆም አለበት።
    3/ የትግራይ ተወላጆች እንደ ማንኛውም ዜጋ ሠርተው መኖር ይችላሉ። በህወሓት አሠራር ግን ብልጫ ሊሰጣቸው አይገባም፤ መቆም አለበት። የጎሣ ጥላቻ መወገድ አለበት። እኩልነት፣ እኩልነት፣ እኩልነት። የአማራና የኦሮሞ ቄሮዎች የትውልዱ ተረካቢዎች እንደ መሆናቸው ተግተው ዐይን ያወጣ መድልዎ ማስቆም አለባቸው።

    Reply
  2. Geta Yimesgen says

    February 27, 2018 11:55 pm at 11:55 pm

    ዶ/ር አቢይ አህመድን ጥላሸት የሚቀባው
    የበረከት ስምኦን ደብዳቤ
    ኢንሳን የመሰረተ አብይ አይደለም የተቋሙ ዳይሬክተርም ሆኖ አያውቅም፣ የትምህርት ማስረጃውም ፌክ
    ነው፣ ብአዴን ሃገሪቱን ካልመራ እንጫረሳለን እያለን ነው ራሱን የአማራ እንደራሴ አድርጎ የሾመው
    ትግሬው በረከት ስመኦን። አንብቡት
    ————–
    ሰላም የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች።
    ልባዊ ሰላምታዬን ባላችሁበት አቀርባለሁ።
    የውስጥ ድክመቶቻችን ያስከተሉት የህዝብ ቅሬታና ክፍተት እንዲሁም አጋጣሚውን የተጠቀሙበት ሀይሎች
    አፍራሽ ሚና ተዳምሮ አሳሳቢ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ድርጅታችን ጥልቅ ተከታታይና ዙሪያ መለስ
    የተሀድሶ ስራዎችን እያካሄደ እንደሆነ ይታወቃል። የዚህ አካል የሆነው የብአዴን ጥልቅ ግምገማ
    መጠናቀቁንና የአቋም መግለጫውን ከሚዲያ ሰምታችኋል።
    የተሀድሶ ሂደታችንን በሰፊው ህዝብ ዘንድ ለማስረጽ በተለይም ለስልጣን ያለ የተዛባ አተያይን እና
    የህዝበኝነት ዝንባሌዎችን የሚተነትኑ ጽሑፎች በአዲስ ራዕይ መጽሔት በኩል በማውጣት ህዝቡ
    እንዲወያይበት አድርገናል።
    በነዚህ ሁለት ቁልፍ ችግሮች ዙሪያ በቀጣይም በሚመለከታቸው የኢህአዴግ መዋቅሮች አማካኝነት ሰፋፊና
    ጥልቅ ውይይቶችን የሚደረጉ ይሆናል።
    ይሁን እንጂ የድርጅታችን ሊቀመንበር የስራ መልቀቂያ ማስገባት እና የአመራሮች በተለያዩ ስራዎች
    መጠመድን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለስልጣን ባለ የተዛባ አተያይ የተመሰረተ አደገኛና ትርምስ
    የሚጋብዝ ህዝበኛ አካሄድ እየታየ በመሆኑ የተወሰኑ ነጥቦችን ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ታይቶኛል።
    በድርጅታችን ባህል ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እና የማህበረሰብ ለውጥ ማምጫ የልማት መሳሪያ እንጂ
    የግለሰብ ዝና (personality cult የሚባለው) የሚገነባበት አይደለም። ከሊቀመንበር ጀምሮ በየትኛውም ቦታ
    ላይ የሚደረግ ምደባ የግለሰቡን ጽናት ልምድ የግምገማ ውጤት የመሳሰሉትን ነገሮች መሰረት ያደረገ
    ብቻና ብቻ ነው። እነዚህን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሟላው እጩ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ደመቀ መኮንን
    ቢሆንም ሌሎች የተሻሉ ካሉ በአመራር ስብሰባ ላይ ቀርቦ የምንነጋገርበት እንጂ እንደኒዎ ሊበራል
    ድርጅቶች በየሶሻል ሚዲያው ቅስቀሳ የሚደረግበት አሰራር የለም።
    በክልል ቴሌቪዥን የአንድን እህት ድርጅት የአመራር አባል ማስታወቂያ የሚሰራበት እና ህዝቡ የተሳሳተ
    ግንዛቤ እንዲይዝ የሚደረግበት አካሄድም ከድርጅታችን ባህል ያፈነገጠ ነው። በተለይ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ
    አንዱ ምክንያት የሆነው ዛሬ በኦሮሚያ ቴሌቪዥን በአማርኛ የቀረበው ዶኩመንታሪ ከአብዮታዊ ባህል
    ያፈነገጠ የድርጅትን ስልጣን በህዝበኝነት ለመቆጣጠር የተደረገ እና ህዝቡን ለተሳሳተ ግንዛቤ ብሎም
    ግርግር ሊሚመራ የሚችል ነው።
    ዶኩመንታሪውን አስደንጋጭ የሚያደርገው ከድርጅታችን ባህል ማፈንገጡ ብቻ ሳይሆን ከእውነት የራቁ
    መረጃዎችን የያዘ መሆኑን ነው።
    የደርግ ስርአትን በሚገረሰስበት ወቅት በየቦታው የኦህዴድን መዋቅር ስናደራጅ ጓድ አብይ አህመድ
    ድርጅቱን እንዲቀላቀል እንዳደረግን እና በክፍለ ህዝብ ክንፍ ተመድቦ የሰላምና መረጋጋት እንዲሁም
    የቅስቀሳና ማደራጀት ስራዎችን እንዲያግዝ ማድረጋችን ትዝ ይለኛል። በ1987 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት
    ጸድቆ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲደራጅ የሰራዊቱን ተዋጽኦ ለማመጣጠን ወደ ሰራዊቱ እንዲገቡ ከተደረጉ
    የድርጅት አባላት አንዱ ነበር። ሻዕቢያ በወረረን ወቅት በሀምሳ አለቃ ማዕረግ በራዲዮ ኦፕሬተርነት ይሰራ
    እንደነበር የሰራዊቱን ዝግጅት ለመጎብኘት በሄድኩበት ወቅት ተረድቻለሁ።
    በ1997ቱ ምርጫ ማግስት ከሰራዊቱ ጋር በነበሩ ስራዎች አጋጣሚ አግኝቸው መቶ አለቃ ደርሶ እንደነበር
    አስታውሳለሁ። ከዛ በኋላ ሰራዊቱ ውስጥ በቆየባቸው ጥቂት አመታት ከመቶ አለቃ ወደ ሌተናል ኮሎኔል
    ማዕረግ መድረሱ ያጠራጥረኛል። የሌተናል ኮሎኔል ማእረግ ከተሰጠውም ሊሆን የሚችለው የብሄር ተዋጽኦ
    ማመጣጠን በሚባለው አካሄድ ነው። የብሄር ተዋጽኦ የማመጣጠን አሰራራችን ህገመንግስታዊና ትክክለኛ
    ቢሆንም በዚህ አካሄድ ፈጣን እድገት ያገኙ አባላት አላማውን በመገንዘብ ሰራዊቱ ውስጥ እስካሉ ድረስ
    ይገለገሉበታል እንጂ ከሰራዊቱ ከወጡ በኋላ ለማስታወቂያ ፍጆታ አያውሉትም።
    ለስልጣን ያለንን የተዛባ አተያይ የሚያመለክቱ በርካታ ግነቶች በዶክመንታሪው ላይ መታየታቸው
    የድርጅታችንን ጤንነት ቆም ብለን መመርመር ማየት እንዳለብን የሚጠቁም ነው። የኢንሳ መስራች ነው
    ተብሎ የቀረበው ግራ የሚያጋባ ነው። ይህን ዘመናዊ ሀሳብ ያፈለቀው ጓድ መለስ ዜናዊ ነው። ሲከተል
    ደግሞ ኢንሳ መስራች አለው ከተባለ መስራቹ መንግስት ነው። በመሰረቱ ኢንሳ ቀድሞ ሲግናል ሬጅመንት
    ሲባል ከነበረው አሀድ ያደገ ተቋም ነው። እዚያ የነበሩ ዋነኛ ሞተሮች ደግሞ የብአዴን ፍሬዎች የሆኑት እነ
    አህመድ ሀምዛ እነ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው። ለጓድ አብይ የኢንሳ ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመበት አጋጣሚ
    የነበረ አይመስለኝም። የመስሪያ ቤቱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደመሆኑ ጓድ መለስ የዳይሬክተር
    ለውጥ ሹመት ሰጥተው ቢሆን ያሳውቁን ነበር።
    ከግል ህይወት ታሪክ ወይም ሲቪ ጋር በተያያዘ ጓድ ሃይለማሪያም በሰጡት መመሪያ መሰረት
    የአመራሮችን የትምህርት ማስረጃዎች ማሰባሰብና ማደራጀት ሲካሄድ ጓድ አብይ በውጭ ሀገር የማስተር
    ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝቻለሁ በሚለው መረጃው ምክንያት ከጓድ ሙክታር ጋር ውዝግብ ውስጥ
    ገብተው እንደነበር አስታውሳለሁ። የሰነድ አደራጅ ኮሚቴ የተጠቀሰውን ዩኒቨርሲቲ ሆነ የትምህርት ማስረጃ
    ማረጋገጥ አለመቻሉን ለማዕከል ሪፖርት ሲያደርግ ጓድ ሙክታር ስልጣኑን ተጠቅሞ ባለማስቆሙ ከጓድ
    አብይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደቀረበ ይታወሳል። ይህም ለስልጣን ያለ የተዛባ አተያይን የሚያመለክት መሆኑ
    ተግልጾለት ሂሱን የዋጠ ሲሆን አጠቃላይ ጉዳዩ በእናት ድርጅት ተገምግሞ እንዲቀርብ አቅጣጫ ተሰጥቶ
    ነበር። ዛሬ ዶኩመንታሪው ላይ ተደግሞ ሳየው የስንት አመታት ግምገማና ውይይት ምን ወንዝ ወሰደው
    የሚያስብል ነበር።
    የግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው የድርጅት መድረክ ይታያል። እነዚህን መረጃዎች እዚህ ለማቅረብ ያስገደደው
    ምክንያት ህዝብ የተሳሳተ ግንዛቤ ተፈጥሮበት ወደውዥንብርና ግርግር እንዳይገባ ከወዲሁ እርማት መስጠት
    ግዜ የማይሰጥ ድርጅትንና ሀገርን የማዳን ተግባር በመሆኑ ነው። አመራሮች በተለያዩ ስራዎች በመያዛቸው
    የተለመደውን መዋቅር ሳልጠብቅ የድርጅታችንን አባላትና ደጋፊዎች በቀጥታ እና በፍጥነት ማስገንዘብ
    አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
    መላው የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች በየአቅጣጫው በሚታዩ ነገሮች ሳይደናገሩ የኢህአዴግና የብአዴን
    አመራሮች ስልጣንን የለውጥ መሳሪያ እንጂ የግል ጥቅም ማራመጃ አድርገው እንደማያዩት እምነት
    ሊያሳድሩ ይገባል። አንዳንድ በየቦታው የሚታዩ ጤናማ ያልሆኑ ዝንባሌዎችም በዙሪያ መለስ ግምገማ
    የሚስተካከሉ ናቸው። በአመራር ረገድ የሚፈጠር ክፍተት አይኖርም። ጓድ ኃይለማርያም በስራ ላይ
    ናቸው። እሳቸው ፈጥነው መልቀቅ ቢያስፈልጋቸው እንኳን የኢህአዴግ ምክር ቤት ምርጫ እስከሚያደርግ
    ድረስ በህገ-መንግስቱ መሰረት ምክትላቸው ስራውን እየሸፈኑ ይቆያሉ።
    ከህዝባችን ጋር ሆነን የማንፈታው ችግር የለም!
    የህዳሴ ጉዟችን ይሳካል!”
    በረከት ስምኦን
    ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
    February 27, 2018

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule