በ1994ዓም የኢራቁ ፕሬዚዳንት ሳዳም ሁሴን “በምርጫ” 100% ደፍነው ነበር፡፡ ያለፈው ዓመት ደግሞ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ-ኧን ያለአንዳች ተቀናቃኝ ባደረጉት “ከፍተኛ ትንቅንቅ” በነበረበት የምርጫ ውድድር ብቻቸውን ተወዳድረው በመጨረሻው ላይ ትንፋሻቸውን ይዘው 100% ለመድፈን በቅተዋል፡፡ ሳዳም 100 ከደፈኑ በኋላ ብዙም አልቆዩም፡፡ በሌላ በኩል የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ ታላቁ ባለራዕይ መሪ ኪም ጆንግ ኢል ከልጃቸው ኪም ጆንግ-ኧን በ0.1% በመበለጥ በ2001ዓም 99.9% ያገኙ “ጎበዝ” ነበሩ፡፡ የኩባው ራዑል ካስትሮ በ2000ዓም 99.4% ሲያገኙ የሶሪያው ባሽር አል አሳድ 97.6% ያስቆጠሩ ሌላው “ደፋኝ” ናቸው፡፡ የቱርክሜኒስታኑ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በ1984 እንዲሁም የቼችኒያው የተባበሩት ሩሲያ ፓርቲ በ2003ዓም 99.5% ያስቆጠሩ ሌሎቹ “ጎበዞች” ናቸው፡፡ በ1996ዓም … [Read more...] about 100% ደፋኝ “ጎበዞች”
Archives for June 2015
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሄት
“ትግሌን አደራ” ነፃነቱን የተቀማ ሕዝብ ለድል የሚያበቃው ጠንካራ ድርጅት ይፈልጋል ምርጫና የሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ ምርጫ 2007 ሂደቱም ሆነ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብትና ደህንነት የሚጠብቅ መንግሥት የላትም በመሳሰሉና ሌሎችም ርዕሶች መጽሄቱ ታትሞ ወጥቶዋል - ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሄት
የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ
የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ! «ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔ ምንጮቻችን አረጋገጡ። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት፣ አጥኚዎቹ ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የትግሬ-ወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ያለፉትን የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት ጉዞ መዝነው፣ ለሥልጣኑ አስጊው ማን እንደሆነ በመተንተን፣ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ የትግሬ-ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት ዝርዝር ጥናት አቅርበዋል። በትግሬ-ወያኔ የስለላ ተቋሞች ከፍተኛ አካሎች አማካይነት የተደረገው ይህ ዝርዝር ጥናት፣ … [Read more...] about የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ
የመድረክ ምርጫ አስተባባሪ በደቡብ ኢትዮጵያ ተደብድበው ተገደሉ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በደቡብ ክልል አንድ የምርጫ አስተባባሪው አርብለት ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲም በምርጫ 2007 ዙሪያ የዛሬውን ጨምሮ 4 አባላቱና ደጋፊዎቹ መገደላቸውን አስታውቋል። በዚህ ሳምንት እንደተገደሉ ተቃዋሚዎች ከገለጿቸው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው አጠቃላይ ቁጥር ስድስት ደርሷል። በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የተገደሉት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ ሐሙስለት በሁለት ፖሊስ ባልደረቦች ከመኖሪያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ተደብድበው ህይወታቸው አልፎ ወንዝ ዳር መገኘታቸውን የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ምርጫ 2005 በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ወደ 46ሽህ የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንግስትና ምርጫ ቦርድ … [Read more...] about የመድረክ ምርጫ አስተባባሪ በደቡብ ኢትዮጵያ ተደብድበው ተገደሉ
ኦባማ “የዕረፍት ጊዜ ለማሳለፍ” ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ
ዳግም የመመረጥ ጭንቀት በማይኖርበት በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አፍሪካን ለዕረፍት ይጎበኛሉ፤ ይዝናናሉ፡፡ የዱር እንስሳትን ያያሉ፤ “የአገራቸውን ባህል ልብስ” ከለበሱ የአፍሪካ ሹመኞች ጋር ጥሩ ፎቶዎችን ይነሳሉ፤ የሥልጣን ዘመናቸው ካለቀ በኋላ ለሚመሠርቱት ቤተመጻህፍት ማስዋቢያ የሚሆን ለየት ያሉ ፎቶዎችን ይሰበስባሉ፡፡ መጪው ወር (July) መገባደጃ አካባቢ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአራተኛ ጊዜ አፍሪካን እንደሚጎበኙ ቤተመንግሥታቸው አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በሚካሄድባት አዲስ አበባ ላይ በመገኘት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአባታቸው አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ለመጎብኘት አስቀድመው ዕቅድ የያዙት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ጉዳይ አርብ ይፋ መደረጉ አስቀድሞ የታሰበ ሳይሆን … [Read more...] about ኦባማ “የዕረፍት ጊዜ ለማሳለፍ” ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ
በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ
አቶ ፈቃደ ሸዋቀና የስደትን ነገር መነሻ አድርገው ስለ ብሔራዊ እርቅ የሰነዘሩት ሀሳብ ካለፈው የባሰ ጨለማ የሆነው የሀገራችን መጻኢ እድል አሳስቦ አስጨንቆአቸው ያቀረቡት በጎ ሀሳብ እንደመሆኑ አንብበን የምንተወው ወይንም ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ብለን ልናናንቀው የሚገባ አይደለም፡፡ ርሳቸውም አንዳሉት ሁሉም የየበኩሉን ይበጃል የሚለውን ሀሳብ በመሰንዘር በመተላለቅ ሳይሆን በመታረቅ የምናተርፈበትንና ሀገራችንንም አድነን ለመጪው ትውልድ ልጆቿ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማቆየት ወደሚያስችለን እቅጣጫ ብናመራ ነው የሚበጀው፡፡ በዚህ መንፈስ እኔም እንዲህ ቢሆን እላለሁ፡፡ ወያኔ ስልጣኑን ለብቻው ካደረገ ግዜ ጀምሮ በተለያየ መንገድ የብሔራዊ እርቅ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የሀሳቡ አቀንቃኞች በሁለት ወገን መወገዛቸውን እናስታወሳለን፡፡ ወያኔ የደርግ ሥርዓት ወንጀለኞችን … [Read more...] about በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ
“መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው
* “ልማታዊ ግድያውን” ተጠናክሮ ቀጥሏል እየሠራሁ ነው ለሚለው ልማትና ግድብ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” እያለ የሚፈክረው ኢህአዴግ በየእስር ቤቱ የሚያሰቃያቸው ወገኖች ቁጥር እንዳለ ሆኖ “ልማታዊ ግድያውን” አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሰሞኑን በግፍ የተገደለው ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ማክሰኞ ዕለት የዓረና-መድረክ አባል የሆኑት አቶ ታደሰ አብርሃ ታንቀው መገደላቸው ተሰማ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሚያዚያ ወር በእንግሊዙ አምባሳደር የተጎበኙት አንዳርጋቸው ጽጌ ለመሞት ደስተኛ እንደሆኑና ምናልባትም የተሻለ መሆኑን ተናገሩ፡፡ የአቶ ታደሰ አብርሃን አገዳደል በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨው አምዶም ገብረሥላሴ በዚህ መልኩ አቅርቦታል፡- አቶ ታደሰ አብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አመራር አባል ትናንት ማታ 09/10/2007 ዓ/ም በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ። አቶ … [Read more...] about “መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
ከአዘጋጆቹ፤ ወዳጃችን ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ ... በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ ቆይተው ባለፈው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት እናንተ አንባቢያን ታሪካቸው መነሳት አለበት የምትሉትን ከፎቶ ጋር እንድታቀርቡ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡ የአገራችን ታሪክ በሚያስደነገጥ ፍጥነት እየወደመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን አንስተን ማወደስ ተገቢ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ አገራዊ ጥሪ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ትኩረታችን እና ኃይላችንን የሚወስደው ነገር አንድ ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም እየደረሰብን ያለው ጥቃት ከበርካታ አአቅጣጫ ነውና፡፡ ስለዚህ አሁንም ይህንን ዓምድ በከፈትንበት መልኩ ሥራቸውና ታሪካቸው እንዲነሳ የምትፈልጉት ሰው ካለ ፎቶውንና … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
የሻእቢያ “የተሀድሶ” ስትራቴጂ አካሄዱና እንደምታው
በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አስመራ ላይ የተሰየመው የሻእቢያ መንግሥት ለ 23 ዓመታት የተከተለውን አካሄድ እንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ገጽታን ለማሳየት እና ራሱን አለሳልሶና የሰላም አባወራ ሆኖ ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን ኢትዮጵያስ ምን እንደምታ አለው? የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋናአላማው ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የሻእቢያ “የተሀድሶ” ስትራቴጂ አካሄዱና እንደምታው
ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ
የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን … [Read more...] about ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ