• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው

June 18, 2015 08:59 am by Editor Leave a Comment

* “ልማታዊ ግድያውን” ተጠናክሮ ቀጥሏል

እየሠራሁ ነው ለሚለው ልማትና ግድብ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” እያለ የሚፈክረው ኢህአዴግ በየእስር ቤቱ የሚያሰቃያቸው ወገኖች ቁጥር እንዳለ ሆኖ “ልማታዊ ግድያውን” አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሰሞኑን በግፍ የተገደለው ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ማክሰኞ ዕለት የዓረና-መድረክ አባል የሆኑት አቶ ታደሰ አብርሃ ታንቀው መገደላቸው ተሰማ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሚያዚያ ወር በእንግሊዙ አምባሳደር የተጎበኙት አንዳርጋቸው ጽጌ ለመሞት ደስተኛ እንደሆኑና ምናልባትም የተሻለ መሆኑን ተናገሩ፡፡

የአቶ ታደሰ አብርሃን አገዳደል በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨው አምዶም ገብረሥላሴ በዚህ መልኩ አቅርቦታል፡-

አቶ ታደሰ አብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አመራር አባል ትናንት ማታ 09/10/2007 ዓ/ም በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።

tadesseአቶ ታደሰ አብርሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው አስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ አባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

አቶ ታደሰ ማታ 03:00 በሶስት ሰዎች አንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ህወታቸው እስከ 09:15 አላለፈችም ነበር። አደጋውን 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ እንዳልወሰዱት ተናገረው ነበር።

የአቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል እንዳይመረመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና አባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት አካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ አባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል። ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል አባሎቻችን የተከራዩት ሞተር ሳይክል በፖሊስ ትራፊክ ተከልክሏል።

የአቶ ታደሰ አብራሃ ቤት አከራይና ሌሎች ሰዎች ከአደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአቶ ታደሰ አብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ አባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።

ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ አስተባባሪና የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው አቶ ልጃለም ኻልአዩ በአዲስ አበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል። አቶ ታደሰ አብርሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።

“መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው

በሌላ በኩል ዘ ኢንዲፔንደንት የተሰኘው የእንግሊዝ ጋዜጣ እንደዘገበው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዜጋቸውን ለመጎብኘት በሄዱ ጊዜ የሰሙትንና ያዩትን ምስክርነት ለመ/ቤታቸውና ለአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት መላካቸውን አስታውቋል፡፡ ዘገባው ለባለቤታቸው በተሰጠበት ወቅት እጅግ ስሜትን የሚረብሽና መንፈስን የሚጎዳ ይዘት ስላለው ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው እንዲያነቡት የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ለባለቤታቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡

አምባሳደሩና አንዳርጋቸው የተገናኙት በእስር ቤት ሳይሆን የደኅንነት ባለሥልጣናት በተገኙበት ቦታ ነበር፡፡ “በአካላቸው ላይ የሚታይ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም” ያሉት አምባሳደሩ ለብቻቸው በመታሰራቸውና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚደርስባቸው ስቃይ መንፈሳቸውንና ስነልቡናቸውን እንደጎዳው በዘገባው ላይ ተናግረዋል፡፡andargachew

ሪፖርቱ ሲቀጥልም በውይይታቸው ወቅት አንዳርጋቸው ለአምባሳደሩ “እውነቱን ለመናገር ለመሞት ደስተኛ ነኝ – ምናልባትም የተሻለና ሰብዓዊነት ያለው ነው” ብለው እንደነገሯቸው በዘገባቸው ላ አስፍረዋል፡፡ “መንግሥት ይገድለዋል ብዬ ለማመን ይከብደኛል” ያሉት አምባሳደሩ አንዳርጋቸው በፈቃድ የመሞትን (ዩታኔዥያ) አከራካሪነት ያስተውላሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን ከታሰሩ አንድ ዓመት የሚሆናቸው የ60 ዓመቱ አንዳርጋቸው የእስር ቤት ጠባቂዎቻቸው ራሳቸውን ይገድላሉ ብለው እንደሚፈሩ እርሳቸው ግን እስካሁን እንዳልሞከሩት ተናግረዋል፡፡

የአምባሳደሩን ሪፖርት ያነበቡት ባለቤታቸው ሪፖርቱን በጽሁፍ ሲያነቡ እንዴት እንደሰበራቸውና እንደጎዳቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡ ለሌሎች የእንግሊዝ ዜጎች እንደተደረገው በእንግሊዝ መንግሥትም ሆነ በአምባሳደሩ ከዚህ የከረረ ጫና ባለመደረጉ ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚደረገው ጫና ሰሞኑን እየገፋ እንደመጣና ጉዳያቸው በተባበሩት መንግሥታት ልዩ ራፖርተር እየተመረመረ በመሆኑ ወደ እንግሊዝ እንዲመለሱ የሚደረገው ግፊት አንዱ አካል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የአንዳርጋቸው በእስር መቆየት ለኢትዮጵያና እንግሊዝ ግንኙነት መሻከር አስተዋጽዖ ያደርጋል በማለት የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ለኢትዮጵያው እስካሁን በ13 የተለያ ጊዜያት እንዳነሳ ጋዜጣው አስታውቋል፡፡ አንዳርጋቸው የኤምባሲው ሰዎችም ሆኑ ጠበቃ እንዳያገኙ ተደርጎ በእስር የመቆየታቸው ሁኔታ አግባብነት እንደሌላው አሁንም መወትወታችን እንቀጥላለን በማለት የአምባሳደሩ ዘገባ ገልጾዋል፡፡

“መሞቴ … የተሻለ ነው” በማለት አንዳርጋቸው መግለጻቸው በምን ዓይነት የመንፈስ ጭንቀትና ስቃይ ውስጥ እንዳሉና ምን ያህል እረፍት ለማግኘት እንደሚፈልጉ የሚያመለክት እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እየደረሰባቸው ያለውን እጅግ መራራ ስቃይም ሊስተዋሉ በሚችሉ ቃላት መግለጻቸው እየተሰቃዩ ከመኖር መሞትን እንዲመርጡ እንዳደረጋቸው ያሳያል፡፡

“በልማታዊ ግድያ” እና ማሰቃየት ላይ የተሰማራው ህወሃት/ኢህአዴግ ምርጫውን በግልጽ ከማጭበርበሩ አልፎ ቸሁ ደግሞ በተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት ወደ ግድያ ከፍ ማለቱ የዜጎችን ምሬት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋል የሚለው አስተያየት ከምንጊዜውም ይልቅ እየበረታ መጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሁኔታና አሠራር ለዕርቅ በመንቀሳቀስ ላይ ለሚገኙ ወገኖች እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥና ሃሳባቸውን እንዲተዉ የሚያስገድድ እንደሆነባቸው በጉዳዩ ላይ ከተሰማሩት ለመረዳት ተችሏል፡፡

ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ!

የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡samuel

ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡

የወጣት ሳሙኤል አወቀ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም የትግል አጋሮቹ፣ ጓደኞቹና ዘመዶቹ በተገኙበት በጎንቻ ሲሶነሴ ወረዳ ሰቀላ ቀበሌ ግንደወይን አርባይቱ እንሰሳ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 11፡30 ላይ ተፈፅሟል፡፡ (ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia)

ሳሙኤል ከመሞቱ በፊት የተናገረው

ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች!

ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች (ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን/ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው sammyደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እስር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!

በስልኬ እየተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡

ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው! (ከሳሙኤል አወቀ ዓለም – የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule