• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦባማ “የዕረፍት ጊዜ ለማሳለፍ” ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ

June 20, 2015 06:52 am by Editor 2 Comments

ዳግም የመመረጥ ጭንቀት በማይኖርበት በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አፍሪካን ለዕረፍት ይጎበኛሉ፤ ይዝናናሉ፡፡ የዱር እንስሳትን ያያሉ፤ “የአገራቸውን ባህል ልብስ” ከለበሱ የአፍሪካ ሹመኞች ጋር ጥሩ ፎቶዎችን ይነሳሉ፤ የሥልጣን ዘመናቸው ካለቀ በኋላ ለሚመሠርቱት ቤተመጻህፍት ማስዋቢያ የሚሆን ለየት ያሉ ፎቶዎችን ይሰበስባሉ፡፡

መጪው ወር (July) መገባደጃ አካባቢ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአራተኛ ጊዜ አፍሪካን እንደሚጎበኙ ቤተመንግሥታቸው አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በሚካሄድባት አዲስ አበባ ላይ በመገኘት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአባታቸው አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ለመጎብኘት አስቀድመው ዕቅድ የያዙት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ጉዳይ አርብ ይፋ መደረጉ አስቀድሞ የታሰበ ሳይሆን እግረመንገድ የተወሰነ ጉዳይ እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ በአዲስ አበባው ቆይታቸው ከኢህአዴግ ሹመኞችና ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር ይገናኛሉ፤ በንግድ ዙሪያም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አስቀድሞ ወደ ኬኒያ ሊያደርጉ የወሰኑትን ጉብኝት የተቃወሙት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ በመጨመሯ ተቃውሟቸውን የበለጠ እንዲሰማ እያደረጉ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት በኬኒያ ምርጫን ተከትሎ በተነሳው የዘር ዕልቂት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዑሁሩ ኬኒያታ ጉዳይ መጨረሻው ሳይታወቅ ኦባማ ኬኒያን አይጎበኙም ሲባል መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት በቂ ማስረጃ በማጣቱና ኬኒያም ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆኗ ክሱን ለጊዜው እንዲቆም አድርጎታል፡፡ ውሳኔውን የሚቃወሙት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አሁን ደግሞ ከምርጫ ጋር በተያያዘ በርካታ ወንጀሎች በተፈጸመባት ኢትዮጵያ ኦባማ ጉብኝት ሊያደርጉ መወሰናቸውን ፕሬዚዳንቱ የሚያወሩትና የሚያደርጉት ፍጹም የማይገናኝ መሆኑን እንደምታዊ አስተያየታቸውን በመስጠት ተቃውመውታል፡፡ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን የሚይዝ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በሥልጣን ላይ እያለ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ በምርጫ ዝረራ (መቶ በመቶ) አሸንፌአለሁ ከሚል አገዛዝ ጋር እንዴት እጅ ይጨባበጣሉ፤ እንዴትስ ለስብሰባ አብረው ይቀመጣሉ ከሚለው አስተያየት አኳያ የኦባማ ጉብኝት ካሁኑ በርካታ ተቃውሞዎች ገጥመውታል፡፡

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ከሮበርት ኬኔዲ የፍትሕና የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ያነጋገራቸው ጄፍሪ ስሚዝ ሲናገሩ “በዚህ ሳምንት ብቻ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በተገደሉባት ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝት እንዲያደርጉ መወሰኑ በጣም የሚረብሽ ነው” ብለዋል፡፡ ሲቀጥሉም “እንዲያውም ይህ ጉብኝት አሜሪካ የአፍሪካ አምባገነኖች ረዳት ነች ተብሎ የተሰጣትን ምሳሌነት ያጠናክረዋል” በማለት ለኤኤፍፒ ተናገረዋል፡፡

አገራቸውን ለ18 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ የዳረጉ ናቸው ተብለው በበርካታ አሜሪካውያን ዘንድ በምሬት የሚነሱት ኦባማ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የገቡትን ቃል ሳይፈጽሙ መቅረታቸው መራጮቻቸው ያዘኑበት ጉዳይ ነው፡፡ አሜሪካውያን አሁንም ሥራ አጥነት ጎድቷቸዋል፤ አሁንም ኑሯቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየወረደ መጥቷል፤ አገሪቱ የተሸከመችው ዕዳ ሊያስከትል የሚችለው ማኅበራዊና ሌሎች ቀውሶች ከግምት በላይ ሆኗል፡፡ በዚህ ዓይነት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የገቡትን ቃል ያልፈጸሙ መሪ የአፍሪካ መሪዎችን በንግድ ጉዳይ ላይ ምን ብለው ነው የሚያማክሩት በማለት የኦባማን የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚቃወሙ ይጠይቃሉ፡፡ ወይስ አሜሪካንን እንዴት በዕዳ እንደነከሯት በማስተማር አፍሪካውያንም እንዴት የአሜሪካንን ፈለግ እንደሚከተሉ ነው የሚመክሯቸው በማለት ከፌዝ ጋር የተቀላቀለ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ (በአሁኑ ወቅት በአንዳንዶች ግምት የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው)

ቡሽ በቦትስዋና ከቤተሰባቸው ጋር ባደረጉት ጉብኝት የዝሆን ኩምቢ ሲነኩ (Photo: TIM SLOAN/AFP/Getty Images)
ቡሽ በቦትስዋና ከቤተሰባቸው ጋር ባደረጉት ጉብኝት የዝሆን ኩምቢ ሲነኩ (Photo: TIM SLOAN/AFP/Getty Images)

በርካታ “የመጀመሪያው …” ማዕረግ የተጎናጸፉት ኦባማ (የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት፣ የመጀመሪያው በሥልጣን ላይ እያለ የኖቤል ሰላም ተሸላሚ፣…) ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ “በሥልጣን ላይ እያለ ኢትዮጵያንና የአፍሪካ ኅብረት የጎበኘ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት” የሚል ሌላ “የመጀመሪያ” ማዕረግ ሰጥቷቸዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት የአፍሪካን የዱር አራዊት በመጎብኘትና በመዝናናት በርካታ ፎቶዎችን ለቤተመጻህፍታቸው እንደተነሱት ጆርጅ ቡሽ፤ ኦባማም በኢትዮጵያ በሚያደርጉት “የመዝናኛ ጉብኝት”፤ “የአገር ባህል” ልብሳቸውን ከለበሱ የአፍሪካ “አምባገነኖች” ጋር የሚነሱት ፎቶ ወደፊት ለሚያቋቁሙት ቤተመጻህፍት ጥሩ የግድግዳ ማድመቂያ ይሆናል በማለት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የዓለምአቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡ (የፕሬዚዳንት ኦባማ Photo: Jacquelyn Martin/AP)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. mulugeta says

    June 20, 2015 02:42 pm at 2:42 pm

    Useless report, you should not post this at all dedeb

    Reply
  2. በለው ! says

    June 22, 2015 02:30 pm at 2:30 pm

    “በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ ላይ በተመሠረተው የሰብዓዊ መብት መረጋጋጥ እኔም ያቺን ሀገር ሄጄ እረግጣለሁ ሲሉ ኦቦ ሁሴን አስታወቁ!”
    ምን ፍቅር አደረባቸው!?…
    ቅናት! እኮ ምን? ህወአት/ኢህአዴግ በሼክ አላሙዲን በኩል የተሸከሸከ ቼክ ለቢል ክሊንተን ፋውንዴሽን ማስገባታቸውን ሲሰሙ እኔስ በጡረታ ዘመኔ ለፋውንዴሽኑ የኢህአዴግን ራዕይ ማስቀጠል አዋጪ የወዲሁ የቅድመ ሥልጣን ላይ የቦንድ ግዢ (ኢንቨስትመንት) ያህል ነው ሲሉ አብራርተዋል።
    ለመሆኑ ከየትኞቹ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ሊሰበሰቡ ይሆን?
    ከአልበሽር?ከኢሳያስ አፈወርቂ? ሮበርት ሙጋቤ? ባላፈው ነጩ ቤት ከመግባት ከተከለከሉት ጥቁር የአፍሪካ መሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይመጡ ይከለከላሉን? ለትላልቆች የአፍሪካ ወንጀለኞች በዓለም ፍርድ ቤት አለመዳኘት ከለላ ያገኙት በትውልድ አፍሪካዊው ትንሹ ኦቦ ሁሴም ባራክ ጥበቃ ይሆን?ሞኝ የቀድሞ ያሜሪካ መሪዎች የዕርዳታ ስንዴ ሲልኩ ጡረታ ሳይወጡ ድርሽ አይሉም ለምን? ቻይና መንገድና የአፍሪካ ህብረት ህንፃን በነፃ ሠርታ እስክታስረክብና የአፍሪካን ግማሽ ገበያ በማልማትም በማዋለድም አስክትቆጣጠር በጉጉት ሲጠብቁ ይሆን አሁን ሕዝብና መሬቱን ሳይሆን ቀጠናውን በገዛ ገንዘብና የጦር መሳሪያዋ መግዛቷን ሲያቁ ባነው ተባነው ነው!?በፓርላ ውስጥ” አንደኛ ቻይና! ሁለተኛ ቻይና !ሶስተኛ ቻይና ያለው የኢኮኖሚስት ተጠቅላይ መሪ ማን ነበር?
    …..ኦቦ ሁሴን ባራክ በኬንያ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ጉባዔ ከተከታተሉ በኋላወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ታውቋል፡፡*ኢትዮጵያ ነገር ፈጠራ!” ለሦስተኛው ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ጉባዔ” ባለፉት ሁለት ጉባኤዎች ምን ተሠራ? ኢትዮጵያና ኢህአዴግ እንደሁ ከወለድ ነፃ!..በረጅም ግዜ የሚከፈል ብድር! ..በአነስተኛ ወለድ ብድር! ግማሽ ብድር ግማሽ ስጦታ!ከአፍሪካ አንደኛዋ ተመፅዋች ሀገር ይሉና…ከአፍሪካ አንደኛ…ከዓለም ሁለተኛ ያደገች የተመነደገች…ወጣቱ ዕድገቱን እየናቀ የሚሰደድባት…ደላላ እንደልብ ሰው የሚሸጥበት ልማታዊ ሙስና መር ኢኮኖሚ የተፈጠረበት ህዝቡ እንደ ጠ/ሚሩ ልዩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ አገላላፅ ” ለኤርትራ አሰብ ወደብና የባድሜን መሬት..ለጅቡቲ ውሃና መብራት..ለኬንያ መብራትና ጥራጥሬ እህል ..ለሱዳን ለም መሬትና የቀንድ ከብት…ለግብፅ የአባይ ግድብ ቦንድ ተሰጠ ብሎ የሚጮህ…ምቀኛ ህዝብ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት ኢህአዴግ ዓላው ነው ምቀኞች!! ሲሉ ነገረውናል ኦቦ ሁሴን ባራክ በአንድ ወቅት ንግራቸው የኢትዮጵያ ገበሬ ትርፋማ ሆኗል! ልጆቹን ከፍሎ ያስተምራል! ድህነትን ተረት አድርጎ ለዓላም ምሳሌ ሆኗል ብለው ነበር አሁን እዚያ ገበሬ ቤት ሲበሉ ሲጠጡ እሳት ዳር ቁጥ ብለው ኩበት ጭስ እየጠገቡ አረቄ እየመጠጡ ሲያወጉ ማየት አለብን… ሂልተንና ሸራተን ባጅብ ተጎልቶ የብሔር ብሄረሰብ ዳሌ ሲናጥ መመልከትና መገልፈጥ ልማታዊ አፍሪካዊ የአሜሪካ መሪ አያሰኝም እንዲያውም ጥቁር የጥቁርን ሕዝብን መናቅና በጭቆናው መደሰት ትርፉ ትዝብትና ነው በለው!።ጥቁር አራት ነጥብ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule