አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡ አዲስ አድማስ እንዲህ ይላል፡- “በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው - በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡ “ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው - ስልክ ተደውሎ። … [Read more...] about “ሕገወጦቹ!”
Archives for April 2015
“ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
እንደ ሚዲያ ወይም እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ይህን እንጽፋለን፡፡ እንደ ክርስቲያን ወይም እንደ ሙስሊም ሳይሆን እንደ አንድ ሰው ይህን እንናገራለን፡፡ ሰብዓዊነት ከሙያ በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከሃይማኖት በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከምን ዓይነት መጠሪያ በላይ ነው፡፡ በሊቢያ የሚገኘው የአይሲስ ተወካይ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን አረደ፤ በጥይት ረሸነ፡፡ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ዘገባውን አቀረቡ፤ ኢትዮጵያውያን መታረዳቸውን አወጁ፤ ዓለም ቪዲዮውን ተመለከተው፤ ዜናውን አነበበው፡፡ እኛም በሃዘንና በእንባ አንብበነዋል፤ ተመልክተነዋል፤ (ፎቶም ሆነ ቪዲዮውን እዚህ ላይ አንለጥፍም)፡፡ ኋይት ሃውስ እንኳን መግለጫ ሰጠ፤ ድርጊቱን ኮነነ፤ ከሰብዓዊነት በታች፤ ዘግናኝ፣ ፍጹም አረመኔያዊ፣ ጨካኝና ስሜት አልባ በማለት አወገዘው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ … [Read more...] about “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
“በሃይማኖት ማስገደድ የለም!”
የፌስቡክ ወዳጃችን Abubeker Siraj ከዚህ በታች ያለውን ጽሁፍ ከመልዕክት ጋር ልከውልናል፤ ሁሉንም እንዳለ አቅርበነዋል፡፡ ለፌስቡክ ወዳጃችን Abubeker Siraj ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሰላም እና በረከት ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን ጎልግሎች ሆይ! እኔ አንድ አንባቢያቹ ነኝ ከአዲስ አበባ። ፅሁፎቻቹን አነባለው አደንቃለው። ከምንም በላይ አገር ወዳድነታችሁ እና ሚዛናዊነታችሁን ሳላደንቅ አላልፍም። ዛሬ አንዲት ጉዳይ ላወራቹ ፈልጌ ነበር። እሱም አሁን ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ላይ የሚገኘው የወንድሜ ኢብኑ ሙነወር (Ibnu Munewor) ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ሰሞኑን አይ ኤስ አይ ኤስ በፈፀመው ዘግናኝ ኢ ሰብአዊ ተግባር ላይ ሲሆን በጥቅሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከዚህ አፀያፊ እና ዘግናኝ ተግባር ፍፁም የፀዳን መሆናችንን እና ከክርስቲያን ወገኖቻችን … [Read more...] about “በሃይማኖት ማስገደድ የለም!”
መፍትሔው የአማራ ተራድኦና የዕርቅ ድርጅት አይደለም
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ! … [Read more...] about መፍትሔው የአማራ ተራድኦና የዕርቅ ድርጅት አይደለም
ጨለማው ሳምንት
ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት! "ወንድሞቼ ያልፍልኛል ብለው ከቤት እንደወጡ እዚያው በበረሃ ቀሩ።" ትላለች እየሩሳሌም። እትብታቸው የተቀበረባትን ሃገር ለቀው ሲወጡ ጣሊያን ለመግባት ነበር ዕቅዳቸው። አውሮፓን አልመው ቀዬአቸውን ለቅቀው የወጡ እነዚህ ወጣቶች … [Read more...] about ጨለማው ሳምንት
በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር
"አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ. . . ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር. . . በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። . . . በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።" ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት። አስሩን ህጻናት በአንድ መኪና(ትራክ) ውስጥ አጭቆ ነበር ወደ ሞሉ የወሰዳቸው። የያዘው መኪና ከአራት ሰው በላይ መጫን አይችልም። እመንገድ ላይ ፖሊስ እንዳያያቸው "ሁላችሁም ጎንበስ በሉ።" ይላቸው እንደነበርም ህጻናቱ አጫውተውኛል። እነዚህ ሕጻናት ሀገሪቱ የምትመካባቸው የነገ ሳይንቲስቶችዋ ናቸው። ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ከፍተኛ፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት … [Read more...] about በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር
“አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች
* “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን” ቴድሮስ አድሃኖም በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ የተጀመረው ጥቃት ያስቆጣቸው የናይጄሪያ እንደራሴዎች በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ የሩዋንዳውን ፕሬዚዳንት በማስተናገድ የተጠመዱት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ አፍሪካ “የተፈጠረው ጊዜያዊ ችግር ነው ብለን እናምናለን” በማለት አስተያየት ሰጡ፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴድሮስ ከየቦታው ሃሳብ እየሰበሰብኩ ነው፤ “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉ ድጋፍ እናደርጋለን” አሉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግን የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የተነሳው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ ብዙዎችን እኤአ በ2008 የተከሰተውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል፡፡ በወቅቱ ከስድሳ በላይ … [Read more...] about “አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች
“አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት
ደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ዓመጽና ግድያ ቦኮ ሃራም የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ግጭቱንና ግድያውን እንዲያስቆም ገደብ ሰጠ፡፡ "አይማረኝ አልምራችሁም" አዘል መልዕክት ማስተላለፉ ተገልጾዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ያዕቆብ ዙማ ልጅ የውጭ አገር ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ መባረር አለባቸው በማለት ከተናገረ በኋላ የተነሳው ዓመጽና አሰቃቂ ግድያ በርካታዎችን ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል፡፡ ከኤድዋርድ ዙማ በተጨማሪ የዙሉው ንጉሥ ተመሳሳይ ንግግር በማድረጋቸው አፍሪካውያን በአፍሪካውያን ላይ ለማመን የሚከብድ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለተለያዩ የውጭ አገር ዜጎች ዘግናኝ ሞት ምክንያት የሆነው ቀውስ በቶሎ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ የተለያዩ የዜና መዋዕሎች ዘግበዋል፡፡ እስካሁን በእርግጠኝነት … [Read more...] about “አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት
What do we owe our patriotic mothers and fathers who saved Ethiopia from Colonial Domination?
* What is left from the Victory of Adowa? Introduction To write an article on such a major issue might seem too late. Many have written over the last three or more weeks in memory of the victory of Adowa. Many have tried not only to show the historical importance of the victory of Adowa, but also its political impacts over the liberation movements during the colonial time. The present political, economic social and cultural crisis of our country, however compels us to remember the victory of … [Read more...] about What do we owe our patriotic mothers and fathers who saved Ethiopia from Colonial Domination?
ወያኔ እና የቅድመ-ምርጫ ግምገማው
ወያኔ የአምስት ዓመቱ "የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ" እንዲሁም የዐባይ ግድብ ግንባታ እንዳልተሳካለት አመነ፣ በመጭው ምርጫም የሚያሰጋኝ የድርጅትም ሆነ የግለሰብም ተወዳዳዳሪ የለኝም አለ የትግሬ-ወያኔ መራሹ ዘረኛ አገር እና ትውልድ አጥፊ ቡድን፣ መጭው የይስሙላ ምርጫ ሊያስከትል የሚችለውን ሕዝባዊ ቁጣ እና እምቢተኝነት በከፍተኛ ደረጃ በመፍራት፣ ሊነሣ የሚችለውን ሕዝባዊ አመፅ በወያኔ ፍላጎት ሥር ለማዋል እንዲቻል፣ አባላቱን በመከፋፈል፣ ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የተያዘ ጥብቅ ሚሥጢራዊ ግምገማ እና ውይይት ማድረጉን የታመኑ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ውስጥ-ዐወቅ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። የሕወሓት/ኢሕአዴግ አባል በሆኑ እና ለወያኔ ታማኝ የሆኑ የየድርጅቶቹ አባሎች ተሣታፊ የሆኑበት ለበርካታ ቀኖች በተከታታይ ግምገማ እና ውይይት የተደረገባቸው … [Read more...] about ወያኔ እና የቅድመ-ምርጫ ግምገማው