• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት

April 17, 2015 08:08 am by Editor Leave a Comment

ደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ዓመጽና ግድያ ቦኮ ሃራም የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ግጭቱንና ግድያውን እንዲያስቆም ገደብ ሰጠ፡፡ “አይማረኝ አልምራችሁም” አዘል መልዕክት ማስተላለፉ ተገልጾዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ያዕቆብ ዙማ ልጅ የውጭ አገር ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ መባረር አለባቸው በማለት ከተናገረ በኋላ የተነሳው ዓመጽና አሰቃቂ ግድያ በርካታዎችን ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል፡፡ ከኤድዋርድ ዙማ በተጨማሪ የዙሉው ንጉሥ ተመሳሳይ ንግግር በማድረጋቸው አፍሪካውያን በአፍሪካውያን ላይ ለማመን የሚከብድ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡

ይህ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለተለያዩ የውጭ አገር ዜጎች ዘግናኝ ሞት ምክንያት የሆነው ቀውስ በቶሎ እንዲቆም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ የተለያዩ የዜና መዋዕሎች ዘግበዋል፡፡

እስካሁን በእርግጠኝነት ባይታወቅም ከተገደሉት መካከል ናይጄሪያውያን መገኘታቸው ያስቆጣው ቦኮ ሃራም ደቡብ አፍሪካ ደም መፋሰሱን፣ ግድያውንና ዘረፋውን ካላስቆመች የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡ በተሰጠው ገደብ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በውጭ አገር ዜጎች ላይ እየተከሰተ ያለውን ለማስቆም እምቢ የሚል ከሆነ ቦኮ ሃራም ደቡብ አፍሪካን በቦምብ እንደሚያናውጣት አስጠንቅቋል፡፡ በዚህ በዩትዩብ ተሰራጨ በተባለ አጭር የቪዲዮ መልዕክት መሠረት ቦኮ ሃራም በአጸፋው በናይጄሪያ፣ በቻድ፣ በኒጀር እና በአካባቢው አገራት የሚገኙ ደቡብ አፍሪካውያንን በሞት እንደሚቀጣ ማስታወቁ ተገልጾዋል፡፡

የቦኮ ሃራም መልዕክት እርግጠኛ መሆኑ አልታወቀም ያለው አንድ የናይጄሪያ ጋዜጣ ቦኮ ሃራም ጥቃቱን ከላይ በተጠቀሱት አገራት በሚገኙ የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲዎችም ጭምር ላይ እንደሚያደርስ ማስታወቁን ዘግቧል፡፡

የስሙ ትርጓሜ “የምዕራባውያን ትምህርት ሃራም (እርኩስ) ነው” የሆነው ቦኮ ሃራም እኤአ ከ2009 ጀምሮ በናይጄሪያና አጎራባች አገራት እስከ 13ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን መግደሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት በርካታ ዜጎችን ያፈናቀለው ቦኮ ሃራም በዚህን ወቅት “ጥሩ ሰው” መስሎ ለመታየት መሞከሩ ያስቆጣቸው ናይጄሪያውያን በማኅበራዊ ገጾች አጸፋውን መልሰዋል፡፡ አንዱ አስተያየት ሰጪ “ቦኮ ሃራም አፉን ቢዘጋ ይሻለዋል፤ እነሱ ራሳቸው የሚያደርጉት (ዘግናኝ ተግባር) በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው የተሻለ ነው ብለው ያስባሉ፤ ማፈሪያዎች” ብሏል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ቦኮ ሃራምን አሸባሪ ድርጅት በማለት የፈረጀው ሲሆን የናይጄሪያ መንግሥት እስካሁን ከቦኮ ሃራም ጋር ጦርነት እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule