- ወያኔ የአምስት ዓመቱ “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” እንዲሁም የዐባይ ግድብ ግንባታ እንዳልተሳካለት አመነ፣
- በመጭው ምርጫም የሚያሰጋኝ የድርጅትም ሆነ የግለሰብም ተወዳዳዳሪ የለኝም አለ
የትግሬ-ወያኔ መራሹ ዘረኛ አገር እና ትውልድ አጥፊ ቡድን፣ መጭው የይስሙላ ምርጫ ሊያስከትል የሚችለውን ሕዝባዊ ቁጣ እና እምቢተኝነት በከፍተኛ ደረጃ በመፍራት፣ ሊነሣ የሚችለውን ሕዝባዊ አመፅ በወያኔ ፍላጎት ሥር ለማዋል እንዲቻል፣ አባላቱን በመከፋፈል፣ ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የተያዘ ጥብቅ ሚሥጢራዊ ግምገማ እና ውይይት ማድረጉን የታመኑ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ውስጥ-ዐወቅ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። የሕወሓት/ኢሕአዴግ አባል በሆኑ እና ለወያኔ ታማኝ የሆኑ የየድርጅቶቹ አባሎች ተሣታፊ የሆኑበት ለበርካታ ቀኖች በተከታታይ ግምገማ እና ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች፦
አንደኛ ፦አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ በኃላፊነቱ ይቀጥል ወይስ ይነሣ?
ሁለተኛ፦የትግሬ የበላይነት አለ? ወይስ የለም?
ሦሥተኛ፦የአምስት ዓመቱ “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ”፣ እንዲሁም የዐባይ ግድብ ግንባታ በታቀደው መልኩ ያለመከናወናቸው መሠረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው?
አራተኛ፦ በ2007 ዓ.ም. ምርጫ ጠንካራ ተቃዋሚዎች አሉ ወይ? ካሉስ እነማን ናቸው?
የሚሉት እንደሆኑ ታማኝ እና ሁነኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የውስጥ-አዋቂ ምንጮች አረጋግጠዋል።
በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ በተደረገው ግምገማ እና ውይይት ከሚከተሉት ውሣኔዎችና ድምዳሜዎች ላይ መደረሱን ምንጮች አስረድተዋል። አቶ ኃይለማርያም በያዘው የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ኃላፊነት ይቀጥል? ወይስ አይቀጥል፣ በሚለው ጉዳይ ላይ የወያኔ ቡድን አንድ ቁርጥ ያለ አቋም ላይ ለመድረስ እንዳልቻለ ታውቋል። ከሕወሓት ውጭ ያሉት እና “የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች” የሚባሉት አባሎች፣ “ኃይለማርያም ወያኔ ከሚሰጠው መመሪያ ውጭ የማይንቀሳቀስ በመሆኑ በያዘው ቦታ ቢቀጥል የሚያመጣው ችግር የሌለ ስለሆነ ይቀጥል” ሲሉ፣ የወያኔ አባላት ከሆኑት የተወሰኑ ትግሬዎችም “እስካሁን እኛ ያልነውን ብቻ ሣይሆን፣ ያሰብነውን እና ልንሠራ የምንፈልገውን ቀድሞ የሚናገርልን ስለሆነ በያዘው ቦታ መቀጠሉ ለወያኔ ዓላማ መሳካት ያግዛል እንጂ አይጎዳም” ሲሉ መደመጣቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል “አክራሪ” እና “ለምን ከወሣኝ የሥልጣን ቦታ ላይ ትግሬ ይጠፋል? እኛ ሞተን እና ቆስለን ባስገኘነው ሥልጣን የሌላ ነገድ አባል የሆነ እና በትግሉም ወቅት ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ ያላደረገ ሰው፣ በመለስ ዜናዊ ብቸኛ ውሣኔ ለዚህ ቦታ የበቃ ሰው፣ ለተከታዮቹ አምስት ዓመታት በሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም” በማለት ኃለማርያም በሌላ ትግሬ እንዲተካ የከረረ አቋም መያዛቸው መስተዋሉን የሞረሽ ምንጮች አስረድተዋል። “ኃይለማርያም መነሣት አለበት” የሚሉት የወያኔ አባሎች የሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ፣ “ኃይለማርያም ከወያኔ ፍላጎት ያፈነገጠ ጠባይ ባይታይበትም፣ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ለእርሱ የሚደርስ በመሆኑ፣ መረጃዎች ለወያኔ የሚደርሱት በሁለተኛ ደረጃ ስለሆነ፣ ፈጣን ውሣኔዎችን ለመስጠት ተቸግረናል። ለዓላማችን መሣካትና በፈለግነው አቅጣጫ ለመጓዝ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱ ቦታ በትግሬ መያዝ አለበት” የሚል መሆኑ ታውቋል። ኃይለማርያም ደሣለኝ መነሳት አለበት የሚለው ቡድን በተጨማሪ መከራከሪያነት የሚያነሳው ጭብጥ አለ። ይኸውም፦ “ለአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እና ለዐባይ ግድብ ግንባታ መክሸፍ ዋነኛ ምክንያቱ የአመራር ድክመት፣ የውጭ ፖሊሲያችን ውድቀት” መሆኑ መወሳቱ እና “መለስ ቢሆን ወይም ሌላ ትግሬ አመራሩን ቢይዝ ኖሮ ይህ ውድቀት አይከተልም ነበር። ኃይለማርያም ፈጥኖ የመወሰን ብቻ ሣይሆን፣ በራስ የመተማመን ችግር ስላለበት በእርሱ አመራር ወደ ግባችን መድረስ አንችልም” ከሚል ድምዳሜ መድረሳቸውን ያስረዳሉ። ይህ የተከፋፈለ አመለካከት “ኃይለማርያም ይቀጥል? ወይስ በሌላ ይተካ?” ለሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ መልስ ላይ አለመደረሱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
በዚህም ይመስላል፣ ወያኔ የመጭውን ምርጫ ውጤት ተከትሎ ሊቀሰቀስ ለሚችል ሕዝባዊ አመፅ፣ ቀጥቅጦ እና ጨፍልቆ የወያኔን የበላይነት ለማረጋገጥ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ”ሕገመንግሥቱ የተሰጡትን ሥልጣኖች” በመሻር፣ ጊዜያዊ አዋጅ ከማወጅ አንስቶ፣ የአገሪቱን የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ኃይል በበላይነት የሚመራ እና የሚቆጣጠር ኮሚቴ ፈጥሯል። የኮሚቴው ሰብሳቢም ጨካኙ እና ፈሪው ዐባይ ፀሐዬ እንዲሆን ተደርጓል። ይህን ውሣኔ ከላይ “ኃይለማርያም ይነሳ? ወይስ ይቀጥል?” ለሚለው ጥያቄ መነሳት አለበት የሚሉት ወገኖች አቋም ከወዲሁ አንድ እርምጃ ወደፊት የተራመደ እና ኃይለማርያም በዐባይ ፀሐዬ የተተካ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም ኃይለማርያም ለይስሙላም ቢሆን በወረቀት ላይ የተሰጡትን ወሣኝ የሆኑትን ሥልጣኖቹን አጥቷልና!
“የትግራይ የበላይነት አለ? ወይስ የለም?” ለሚለው የመገማገሚያ ነጥብ፣ እጅግ በርካታ ሰዎች “የትግራይ የበላይነት አለ። በሁሉም የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ በትግሬዎች የተያዙ ናቸው” ሲሉ፣ የተወሰኑት ደግሞ፦ “የትግሬ የበላይነት የለም” እንዳሉ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። በየትኛውም ደረጃ የየውይይቱ መሪዎች ትግሬ ካልጠፋ በስተቀር ሁሉም ትግሬዎች ናቸው። እነዚህ አገማጋሚዎች “የትግሬ የበላይነት አለ” ሲሉ ኃሣባቸውን የገለጹትን፥ “የትግሬ የበላይነት አለ ስትሉ የበላይነቱ በምን፣ በምን እንደሚገለፅ አስረዱ” በማለት ተገምጋሚዎችን አፋጥጠው መያዛቸው ታውቋል። ተገምጋሚዎቹም ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ፦ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ መስኮች ወሣኝ ቦታዎች ብቻ ሳይሆኑ ጥቃቅን ቦታዎች ሳይቀሩ በትግሬዎች መያዙ፤ ትግራይ ከሌሎች ክልሎች ተነጥላ እንድትበለጽግ መደረጉ፤ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት፤ የጤና፣ የመገናኛ፣ እና የኢንዱስትሪ ግንባታዎች በትግራይ መሠራታቸው፤ የቀረው ቀርቶ ትግርኛ መናገር የማያስፈትሽ እና የማያስጠይቅ እንደሆነ ተጨማጭ ማስረጃዎችን በማቅረብ መልስ እንደሰጡ ታውቋል። ለተሰጡት መልሶች አወያዮቹ “ይህማ የግንቦት 7 እና የኢሣት ፕሮፓጋንዳ ነው። ትግሬን የሚጠሉ ሰዎች አቋም ነው። ጥቅማቸው የተነካባቸው የቀድሞው ሥርዓት ናፋቂዎች የሚያራግቡት ፖለቲካ ነው” በማለት እንዳጣጣሉት ለማወቅ ተችሏል። በሚያስገርም ሁኔታ “የትግሬ የበላይነት የለም” ያሉትን ደግሞ “እናንተ አድርባዮች ናችሁ! ወላዋዮች እና አስመሳዮች ናችሁ። ግምገማው ተገቢውን ውጤት እንዳያስገኝ ያሰባችሁ ናችሁ” በማለት የዘለፉዋቸው እንደሆነ ሲታወቅ፣ በዚህ የመገማገሚያ ርዕስ አንድ ዓይነት አቋም ላይ ሳይደረስ፣ አወያዮቹ እንደተለመደው የተሰጡትን ኃሣቦች በማጣጣል ውይይቱ መደምደሙ ታውቋል።
በሦሥተኛ ደረጃ የመገማገሚያ ርዕስ በነበረው በተደረገው ግምገማ እና ምዘና፥ “የአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሁም የዐባይ ግድብ በታሰበው መልኩ አለመከናወኑ ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃላይ ውድቀት እንደሆነ” በሙሉ ድምፅ መስማማታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ለዕቅዶቹ አለመፈጸም መሠረታዊ ምክንያቶች ሆነው የተጠቀሱት፦ “ከአበዳሪ እና ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች ይገኙ የነበሩት ዕርዳታዎች እና ብድሮች መቋረጥ፣ ለዕቅዶቹ ተፈጻሚነት የሚያስፈልጉት ግብዓቶች አብዛኛዎቹ ከውጭ መሆን እና ይህን ማግኘት አለመቻሉ” እንደነበረ ሲጠቀሱ፣ “ይህ ደግሞ የውጭ ፖሊሲያችን ውድቀት መሆኑ፣ የፖሊሲው ውድቀት ደግሞ ብቃት ያለው እንደመለስ ያለ መሪ አለመኖሩ” እንደሆነ በስፋት መገለጹን የውስጥ-ዐወቅ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። በመሠረቱ መለስ ዜናዊ ይህንን የቅዠት ዕቅድ ሲያወጣ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የሚያስፈልጉት አግባብ ያላቸውን ፖሊሲዎች እንዳልቀረፀ ይታወቃል። ከዚያም በላይ የአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገት በውጭ ዕርዳታ እና ብድር በሚገኝ መዋዕለ-ንዋይ ብቻ ይከናወናል ብለው የሚያስቡ ገዢዎች፣ ከመነሻውም ያለባቸውን የአመራር ድክመት የሚያሣይ ነው። ስለዚህ ብዙ የተደሰኮረለት “የአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ውጤቱ ዜሮ ቢሆን ቀድሞውንም የሚጠበቅ ነው።
የ2007 ዓ.ም. ምርጫን በተመለከተ በተደረጉ ግምገማዎች እና ምዘናዎች፣ ሕወሓት/ኢሕአዴግን የሚያሰጉ፣ በሕዝቡ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች እንደሌሉ በገምጋሚዎቹ እይታ ሙሉ እምነትና ስምምነት መደረሱ ታውቋል። በሌላ በኩል “ብቻቸውን ለምርጫ ቀርበው ለምን ምርጫ ይላሉ?” ለሚሉ ወገኖች አፍ ማዘጊያ፣ እንዲሁም እንዳለፈው ምርጫ “በ99ነጥብ6 አሸነፍን” ላለማለት፣ “በዓላማ ከእኛ ጋር የሚስማሙትን፣ በአፈጻጸም የሚለዩትን በመድረክ ሥር ከተሰባሰቡት ሰዎች በድርጅት ስም ሳይሆን፣ በግለሰብ ደረጃ ተመርጠው የፓርላማ ወንበር የሚያገኙበት ሥልት እንዲመቻች” በማለት መስማማታቸው ተረጋግጧል። ይህም ለታማኝ ተቃዋሚዎቻቸው ለእነ ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ፣ ለዶክተር መረራ ጉዲና፣ ለአቶ ገብሩ አሥራት ዓይነቶች በር የተከፈተላቸው እንደሆነ ይጠቁማል። “ይህን ሁላ አድርገንም ምርጫውን እኛ አሸነፍን ብንል ሕዝቡ ሊቀበለን ስለማይችል፣ ይህን ተከትሎ ለሚፈጠር አመፅ አስፈላጊውን የኃይል ርምጃ የሚወስድ በቂ ዝግጅት እንዲደረግ” የሚል ውሣኔ አሣልፈዋል። ይህም ቀደም ሲል ጀምሮ የታሰበበት እንደሆነ ታውቋል። ስለሆነም ከይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ሥልጣን የተረከበው በዐባይ ፀሐዬ የሚመራው ኮሚቴ ዐቢይ ተግባር፣ ሕዝባዊ አመጽን መስበር እንደሆነ የኮሚቴው ዓላማና የግምገማው ውጤት ያሳያል። ለዚሁ ተግባር ሲባልም በከተሞች የተጠናከረ የስለላ እና የመቺ ኃይል ቡድኖች ተደራጅተው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆኑ ታውቋል። በገጠር የገበሬ ማኅበራት በእያንዳንዱ ምርጫው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈላቸው ከአንድ መቶ እስከ መቶ ስልሳ የሚሆኑ አፋኝ ቡድኖች አባሎች መመደባቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በየአምሥት ዓመቱ የይስሙላ የምርጫ ድራማ እንደሚያዘጋጅ እና ውጤቱም ሁልጊዜ በትራጄዲ እንደሚደመደም ይታወቃል።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ሐሙስ ሚያዝያ ፰ ቀን ፪ሺህ፯ ዓም (Thursday April 16, 2015)
Leave a Reply