• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሕገወጦቹ!”

April 21, 2015 06:47 am by Editor 1 Comment

አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡

አዲስ አድማስ እንዲህ ይላል፡- “በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው – በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡

“ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው – ስልክ ተደውሎ። የደወለለት ሰው፣ “የናንተ ሰፈር ልጆች ሊታረዱ ሲሉ የሚያሳይ ፎቶ በፌስቡክ ተለጥፏል” ብሎ ሲነግረው፤ በደንጋጤ “እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ። “የወንድሜን ስም ጨምሮ ነገረኝ፤ የወንድሜን ስም አያውቅም ነበር” ይላል የኢያሱ ወንድም።

“የኔ ፌስቡክ ስለማይሰራ ጓደኛዬ ጋር ሄጄ አየሁ። በደንብ ስላልታየኝ እንደገና ከምሽቱ አራት ሰዓት ስንከፍት ወንድሜን ተንበርክኮ አየሁት። ባልቻን ደግሞ ቀይ ቱታ ካደረጉት መሀል ለየሁት፡፡ ለእናቴ ከመንገሬ በፊት ለሩቅ ዘመዶች ለመናገር እያሰብኩ እያለ እነሱ ቀድመው ሰምተው ለቅሶ ላይ አገኘኋቸው” ብሏል የኢያሱ ወንድም።balcha-and-eyasu

“ኢያሱ ኳታር ሰርቶ የተወሰነ ገንዘብ ይዞ ስለመጣ የባልቻንም ወጪ ሸፍኖለት ነው አብረው የሄዱት። ከኢትዮጵያ ወጥተው በሱዳን ጉዞ የጀመሩት ከሁለት ወር በፊት ነው። “ሱዳን እያሉ በስልክ እንገናኝ ነበር። ገንዘብ ሲያስፈልጋቸው እልክላቸው ነበር” የሚለው የኢያሱ ወንድም፤ “ወደ ሊቢያ ከተሻገሩ በኋላ ግን ስልክ ቁጥር እሰጥሃለሁ ቢለኝም አንገናኝም ነበር” ብሏል።

ስም ለማውጣት፤ ቃላት ለመሰንጠቅና ለመቀመር አቻ የማይገኝለት ኢህአዴግ ለሙታንም ሃዘኔታ የለውም፡፡ “አደገኛ ቦዘኔ፣ አሸባሪ፣ ሕገመንግሥት የሚንዱ፣ የልማት ጸሮች፣ …” እያለ ስም የሚለጥፈው ሳያንሰው ሟቾችንም ህገወጥ እያለ ለመጥራት ምንም አይገደውም፡፡ ኢህአዴግ “እያለባማት” ያለችውን ኢትዮጵያ ጥለው ስለሄዱ “ህገወጥ” ናቸው፡፡ አውሮጳና አሜሪካ ደርሰው ግን “የውጭ ምንዛሪ” መላክ ሲጀምሩ “ዲያስፖራ”፣ “ባለሃብት”፣ “ኢንቨስተር”፣ “የልማት አጋር”፣ የሚለውን ስያሜ ይጎናጸፋሉ፡፡

the twoሰኞ ምሽት የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ የቀረበው ኤርምያስ ዓለማየሁ አይሲስ ስለገደለው አጎቱ ባልቻ በለጠ ሲናገር እንዲህ ብሏል፡፡

“በአንድ አገር ስደት የሚመጣበትን መሠረታዊ ነገር መረዳት (ይገባል)፤ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ነው እነዚህ ወገኖች የሄዱት፤ … መንግሥት ምንም ያመጣልናል ብለን አናስብም፤ … መንግሥት የመጀመሪያ ዜና ላይ አስተባብሏል፤ ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አላረጋገጥንም ብሏል፤ መንግሥት ዕውቅና ሳይሰጥ የውጭ ጣቢያዎች ዕውቅና ሰጥተዋል፤ … ዛሬ በቪዲዮ ስለታየና ግልጽ የሆነ መረጃ ስለተገኘ እንጂ ብዙ ወንድሞቻችን ሄደው አልቀዋል፤ መንግሥት “ስደተኛ” አይላቸውም፤ “ተቸግረው” አይላቸውም “ህገወጥ” ነው የሚላቸው፤ ይህ ሊሰመርበት ይገባል፤ “ህገወጥ ስደተኞች ሞቱ” ብሎ ነው መንግሥት በተደጋጋሚ የሚዘግበው፤ “ሕገወጥ” የሚለው ቃል ለዚያ ነገር ያለውን አመለካከት በግልጽ የሚያሳይ ነው፤ ወንድሞቻችንን ከዚህ የሄዱት ደልቷቸው አይደለም። ተቸግረው ነው። መንግስት ወንድሞቻችንን ስደተኛ ለማለት እንኳን አይፈልግም። ከመንግሥት ምንም (የምንጠብቀውና) የምንፈልገው ነገር የለም”፡፡ (የኢያሱና ባልቻ ፎቶ ከአዲስ አድማስ የተወሰደ)

በጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የተቀናበረ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    April 22, 2015 03:41 am at 3:41 am

    ^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
    እያሱ ኳታር ሠርቶ ወገኑ ባልቻን ዕረዳውና
    ሊያልፍላቸው አስበው ኑሮአቸው ሊቀና
    ሰው በሀገሩ ሁለተኛ ዜጋ በቋንቋ በነገድ ውገና
    በቁም እሥር ከበይ ተመልካች ተቀምጠው ጎዳና
    ሀገር አቋረጡ ለተሻለ ኑሮ ድሃ ሀገር እናት ናትና
    ያው…ጭራቅ ሰው መሳይ አውሬ ገጠማቸውና
    ከጭንቀት ስቃይ እንዳቀረቀሩ ተቀሉ እንደገና!
    ****
    ይህን ነበር ያሉን ‘ሜንጫ’ ማለት ቡጢ ነው ?
    በቅርብ የፈራን የጮኽነው በእሩቁ አየነው
    ባለሥልጣናቱ ተሳናቸው አሉ ሙታንን መለየት
    ፓርቲ ብሄር ቋንቋ ሆኖ መለያው ልዩ ዜግነት
    እረ እንዴት? ባልቻ እና እያሱ ከመለስ አነሱ
    ልማታዊ አድር-ባይ! ሆድ-አደር! ሲተረማመሱ
    ድንኳን ጥለው በጥቅማጥቅም ወር ሲያስለቅሱ
    ጅግና ለወገኑ በቀዬው ሀዘኑን ላይገልፅ በዱላ መባረሩ
    ለወያናይት!ብቻ ሆነ ሀብት ምህዳር ሀገሩ ?
    ሳውዲያ ዓረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ የመን፣
    ሊቢያ፣ ግብፅ፣ እስራኤል፣ በሱዳን አለቅን
    ኢህአዴግ ደስታውን ገለፀ ይበላችሁ አለን!
    እረ ለመሆኑ ቆሉብን ፈጩበን አላገጡብን
    ሠላም! ከዛሬ ነገ ስንል ዳሩ መሀል ሲሆን ታገስን
    አሁንስ አበዙት! አሁንስ ናቁት ትውልዱን
    ሰብከው ያጃጃሉን ልዩነታችን ነጣጥሎ አስበላን
    እንግዲህ ይነጋል ስንል ጨለመ በወገናችን
    ግዜው አሁን ነው የእንቢተኝነት አንድነታችን!!።
    ለሃይማኖታቸው ፅናት ለተቀሉ ነፍስ ይማርልን!
    በለው!*********

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule