ከ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ጀምሮ፤ ለመብት፣ ለነፃነትና በሰላም ሠርቶ ለመኖር ያለው ትግል፤ ሳያርፍ በተከታታይ አሁንም እየተካሄደ ነው። በነዚህ ባለፉት ፵ ዓመታት፤ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤ በትግሉ ከሕዝብ ጎን ተሰልፈው ሕይወታቸውን ሠጥተዋል። ቆራጥ የሕዝብ ጠበቃዎች ወጥተዋል፤ ሕይወታቸውን ላመኑበት ዓላማ በቆራጥነት በመሥጠት በጀግንነት ተቆጥረዋል። ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቷል። በግለሰብ ደረጃ፤ አጥንት የሚሰብሩ፣ ደም የሚነውጡ፣ ልብ የሚነኩ፣ አንጀት የሚያንሰፈስፉ፣ ጀግንነት የተሞላባቸው ተግባራት ተከናውነዋል። ድርጅቶች ተነስተዋል፣ ወድቀዋል። በድርጅቶች ደረጃ፤ ሕዝባዊ ጉዳዮችን መልክ ባለው መንገድ አመቻችተው ባደባባይ አውጥተዋቸዋል። አባሎቻቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለውበታል። መሪዎቻቸው ከፍተኛ መሯሯጥን የኑሯቸው ማዕከል አድርገው … [Read more...] about መማር እንችላለን ወይ?
Archives for April 2015
በጋሞ ጎፋ ፖሊስ በህዝብ ላይ የጭካኔ እርምጃ ወሰደ
በጋሞ ጎፋ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ አልጌ ቀበሌ ፖሊስ በንፁሃን ላይ የጭካኔ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአባያ ሀይቅ ዙሪያ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት ነዋሪዎች መሬት ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት እንደተሰጠባቸው መነገሩን ተከትሎ የአካባቢው ሽማግሌዎች ከሶስት ጊዜ በላይ ለክልሉ አስተዳደር ማመልከቻ ቢያስገቡም መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ አስተዳደር ምንም አይነት መልስ ባይሰጥም የዞኑ አስተዳደር "መሬቱ ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት ተሰጥቷል" የሚል ውሳኔ በማስተላለፉ ነዋሪዎቹ ይህን የዞኑን አስተዳደር ውሳኔ እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህዝቡን ተቃውሞ ተከትሎም ፖሊስ በአባያ ነዋሪዎች ሰፈር እየመጣ እያስፈራራ እንደሚመለስ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የካቲት 30/2007 እንደተለመደው ፖሊስ ነዋሪዎቹን ለማስፈራራት ወደ ሰፈር … [Read more...] about በጋሞ ጎፋ ፖሊስ በህዝብ ላይ የጭካኔ እርምጃ ወሰደ
በስዊድን የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር ራሱን አስተዋወቀ
የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር በስዊድን ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመግለጽ፤ የድጋፍ ማኅበሩ ቅዳሜ አፕሪል 4 ቀን 2015 ዓ.ም. (መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.) ራሱን አስተዋውቋል። በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ዓላማና ተግባርን ጥሪ ለተደረገላቸው ተሰብሳቢዎች ያስረዱት አቶ ሰለሞን ጌታነህ የድጋፍ ማኅበሩ ሰብሳቢ ናቸው። አቶ ሰለሞን በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተደረገው የማስተዋወቁ ሥነሥርዓት ላይ ስለሰማያዊ ፓርቲ ሲያስረዱ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በወጣት አባላት የተመሰረተና የሚመራ መሆኑን ገልጸው፤ ወጣቱ ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ብልጫ ያለው እንደሆነና የወጣቱም ድጋፍ ሰማያዊ ፓርቲን እንዳልተለየው አሳውቀዋል። አያይዘውም ሰማያዊ ፓርቲ የዓላማ ጽናቱ የበረታ በመሆኑና በሀገር ውስጥ የሚያደርገውም እንቅስቃሴ እጅግ የጎላ ስለሆነ ፓርቲውን ሁላችንም መደገፍ ይገባናል … [Read more...] about በስዊድን የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር ራሱን አስተዋወቀ
“የወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!
የዘመቻው ቃል አቀባይ መግለጫ . . . * የወሳኙ ማዕበል ሳውዲ መራሽ ዘመቻ በሁቲ አማጽያንን ላይ ከተጀመረ ወዲህ የአማጽያኑን የመከላከልና የማጥቃት አቅም ለማዳከም 1200 የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የዘመቻው ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በሶስተኛ ሳምንት በደፈነው ዘመቻ ገለጻቸው አስታውቀዋል * አማጽያኑ በተከፈተባቸው የህብረቱ አየር ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ የአየር ሀይልና የምድር ጦር መሽመድመዳቸውን ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ በየመን ግዛቶች በሸብዋን፣ አብያን፣ ላህጅና ያፍዕ በምድርም አማጽያኑን የሚቃወሙ ሀገር ወዳድ የጎሳ መሪ የመናውያን ጠመንጃ አንስተው እየተፋለሟቸው መሆኑን ጠቁመዋል። የህብረቱ ቃል አቀባይ በማከልም በምድር የተጀመረውን የየመናውያን እንቅስቃሴ ህብረቱ ድጋፍ እንደሚሰጠውም ተናግረዋል * የኢራንና የሂዝቦላህ ሁቲዎችን በመደገፍና በማሰልጠን … [Read more...] about “የወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!
Perspectives on the Declaration of Principles regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam
I. Introduction On March 23, 2015, Egypt, Ethiopia and the Sudan signed a declaration of principles on the Grand Ethiopian Renaissance Dam[2] (GERD). Since then, an intense debate has been going on regarding the modalities and core principles which were spelled out in the Declaration. Unfortunately, the principles contained in the Declaration have invited unhealthy rhetoric, particularly within Egypt, Ethiopia and among the Ethiopian diaspora. There are two fundamental reasons for the negative … [Read more...] about Perspectives on the Declaration of Principles regarding the Grand Ethiopian Renaissance Dam
“በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል” ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
በአሜሪካ ከሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ለፍሕትና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ አባላት ጋር በተለያዩ ስቴቶች ለመወያየት ወደዚያ ለማቅናት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያመሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ባላወቁት ምክንያት ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ጉዟአቸው እንደስተጓጎለ ገለጹ፡፡ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወደ አሜሪካ ለመብረር ሁሉን ነገር አሟልተው ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የአውሮፕላን መሳፈሪያ ሰዓት እስከሚደርስ ሊሸኟቸው አብረዋቸው ከነበሩ ጓደኞቻችው ጋር ሲጨዋወቱ አምሽተው ወደ ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ የመጨረሻውን ፍተሻ አልፈው ወደ አውሮፕላን መግቢያ በር ለማምራት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ፍተሻ ጋ ሲደርሱ ፓስፖርታቸውን … [Read more...] about “በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል” ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
ታሪክ ይፋረደናል!
እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ እኛ “የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን አብጦ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል! አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ … [Read more...] about ታሪክ ይፋረደናል!
ስልጣን ላይ አድሮ ለመገኘት ሃገርን መሽጥ፤ ህዝብን መሸፈጥ ለምን? እስከመቼ?
የህወሃቱ መሪ መለስ ዜናዊ ሰሜን አፍሪቃ የተነሳሳው ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያኖች ዘንድ መወያያ ርዕስ እንዳይሆንና አመጹም እንዳይዛመት "ዛሬን ስልጣን ላይ አድሮ መገኘት፤ ቀኑን እንዳመጣጡ ለማለፍ ስልት መቀየስ" በሚል እምነቱና ስልጣንን ከህዝብም ከሃገርም በላይ አምላኪነቱ የተነሳ: ለነገ ምን ችግር ያመጣል? ጉዳቱስ መጠኑና ስፋቱ ምን ያህል ይሆናል? ሃገር ሉዓላዊነትና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ላይ የሚኖረው አዎነታም ሆነ አሉታ ተጽዕኖ ሳያሳስበው ብልጭ ባለለት ማምለጫ መንገድ ብቻ የሚንቀሳቀሰው መለስ "አባይን እገድባለሁ" የሚል ቅዥት ይዞ ብቅ እንዳለ ሁላችንም እናስታውሳለን። ይህን ያልታሰበበት፤ ያልተጠና፤ ህዝብ ያላወቀውና መክሮ ያልተስማማበትን ቅዥት በየሙያው ዘርፉ አንቱ የተባሉና የሃገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ተናገረውበታል፤ ጽፈውበታል አስጠንቅቀዋል፡ ህወሃት ግን የዕለት ስልጣንና … [Read more...] about ስልጣን ላይ አድሮ ለመገኘት ሃገርን መሽጥ፤ ህዝብን መሸፈጥ ለምን? እስከመቼ?
መጪው ጊዜ ለናይጄሪያ “ብሩህ” ይሆናል!!
በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ የፖለቲካ አካሄድ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያመጣል የተባለው የሰሞኑ ምርጫ ውጤት ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት የመንፈስ ልዕልና አጎናጽፏቸዋል፡፡ በበርካታ ችግሮች ለተወጠረችው ናይጄሪያ “ብሩህ ጊዜ” ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን በምክትልነት ናይጄሪያን እያገለገሉ በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዑማሩ ሙሳ ሕይወታቸው በማለፉ ወዲያው የፕሬዚዳንትነት መንበሩን ተረከቡ፡፡ ዑማሩ ሙሳን ተክተው ጥቂት እንዳገለገሉ በወቅቱ በተካሄደ ምርጫ ሙሐማዱ ቡሃሪን አሸንፈው ናይጄሪያን ለአምስት ዓመታት መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የዛሬ አምስት ዓመት ባሸነፏቸው መልሰው ተሸንፈው ሥልጣናቸውን በሰላም አስረክበው በናይጄሪያ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ተግባር በመፈጸም ስማቸውን ከመቃብር በላይ ህያው አድርገዋል - ፕሬዚዳንት ጉድላክ … [Read more...] about መጪው ጊዜ ለናይጄሪያ “ብሩህ” ይሆናል!!
የት ሂዱ ነው?
ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን "የሙጢኝ!" ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን "የሙጢኝ!" እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ … [Read more...] about የት ሂዱ ነው?