• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!

April 6, 2015 02:42 am by Editor 1 Comment

የዘመቻው ቃል አቀባይ መግለጫ . . .

* የወሳኙ ማዕበል ሳውዲ መራሽ ዘመቻ በሁቲ አማጽያንን ላይ ከተጀመረ ወዲህ የአማጽያኑን የመከላከልና የማጥቃት አቅም ለማዳከም 1200 የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የዘመቻው ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በሶስተኛ ሳምንት በደፈነው ዘመቻ ገለጻቸው አስታውቀዋል

* አማጽያኑ በተከፈተባቸው የህብረቱ አየር ድብደባ  በከፍተኛ ሁኔታ የአየር ሀይልና የምድር ጦር መሽመድመዳቸውን ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ በየመን ግዛቶች በሸብዋን፣ አብያን፣ ላህጅና ያፍዕ በምድርም አማጽያኑን የሚቃወሙ ሀገር ወዳድ የጎሳ መሪ የመናውያን ጠመንጃ አንስተው እየተፋለሟቸው መሆኑን ጠቁመዋል። የህብረቱ ቃል አቀባይ በማከልም በምድር የተጀመረውን የየመናውያን እንቅስቃሴ ህብረቱ ድጋፍ እንደሚሰጠውም  ተናግረዋልYEMEN1

* የኢራንና የሂዝቦላህ ሁቲዎችን በመደገፍና በማሰልጠን በየመን ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸው አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በመግለጫቸው ተያዙ ስለተባሉት ሁለት ኢራናውያን ተጠይቀው መያዛቸውን አረጋግጠዋል

* በየትኛውም የባህር፣ የምድርም ሆነ በአየር መገናኛዎች የሁቲ አማጽያን ድጋፍ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ሁሉ መዘጋጋታቸውም የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ ተጠቁሟል

* ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ 35 ሽህ ቶን ሰብአዊ እርዳታ የያዘች የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አውሮፕላን ዘመቻው ለተጀመረ ለሁለተኛ ጊዜ የመን ሰንአ ገብታለች

* የፓኪስታን ፖርላማ የሀገሪቱ ጦር ለሳውዲ ህልውና ያለውን ጽኑ ድጋፍ ቢያረጋግጥም በሳውዲ የሚመራውን የአረብ ሀገራት በየመን ሁቲ ላይ የከፈቱትን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ጦሩ እንደማይቀላቀል ውሳኔ ማሳለፉ የገልፍ ሀገራትን አላስደሰተም

* የኢራን ፕሬዚደንት ሀሰን ሮሄኒ የየመን ጦርነት በውይይት መፈታት አለበት ሲሉ የመንግስት የበላይ የሆኑት የሀይማኖት አባት አያቶላህ አሊ ሆሜኒ በበኩላቸው ሳውዲ አረቢያ በየመን የዘይዲ ጎሳ የሁቲ ተዋጊዎች ላይ የወሰደችውን የአየር ድብደባ “የሰው ዘር ማጥፋት ነው!” ሲሉ ባሳለፍነው ሳምንት አጥብቀው ኮንነውታልfile-11-JUST-CAUSE

* በእስካሁኑ የየመን ግጭት 643 ነፍስ ሲቀጠፍ 2,200 ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአለም አቀፍ ጥበቃ ድርጅት World Health Organization መረጃ ጠቁሟል

የሳውዲ የመን ድንበር ውጥረት . . .

* በነጅራንና በጀዛን በሚዋሰኑት የሳውዲ የመን የጠረፍ ከተሞች ከዚህ ቀደም ከሞቱት 3 የሳውዲ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ 3 የሳውዲ ድንበር ወታደሮች በነጅራን ድንበር መሞታቸው ሲጠቆም 500 ያህል የሁቲ አማጽያን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ከተጀመረ መገደላቸውን የህብረቱ ቃል አቀባይ  ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

*  የሳውዲ የመን የጠረፍ የገጠር መንደሮች የሚገኙ ከ900 በላይ ሳውዲ አባዎራዎች ለደህንነታቸው ሲባል ከአካባቢው ተነስተው ወደ  ውስጥ ከተማ እንዲሰፍሩ ተደርጓል

* ከየመን በጦርነቱ እየተፈናቀሉ እየሸሹ ወደ ሳውዲ የሚገቡት የመናውያን ቁጠር ከፍ እያለ መምጣቱ ተዘግቧል

* በሳውዲ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙት ት/ቤቶች ለደህንነት ሲባል ተዘግተዋል

ኢትዮጵያውያን በየመን . . .

* ዛሬም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የየመን ከተሞች በጭንቅ ላይ ናቸው፣ በሰንአ ጦርነቱን ተከትሎ ህገ ወጥነት ሲንሰራፋ፣ ኑሮው ተወዶ እሳት ሆኗል፣ ከተባበሩት መንግስታት መጠለያና ከመጠለያ ውጭ ያሉ ዜጎች በአደጋ በጦርነት መካከል የድረሱልን ዋይታቸውን እያሰሙ ነውfile-11

* በሰማይ የህብረቱ ጦር የአየር ድብደባ፣ በምድር የሁቲና በተቃዋሚዎቻቸው ፍልሚያ ሰላሟን የነሳት ሁለተኛዋ የየመን ጥንታዊ የወደብ ከተማ በኤደን ያሉ ኢትዮጵያውያን ከከባቸው አደጋ አንጻር የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል፣ ደራሽ ባያገኙም “ድረሱልን!” እያሉ ነው!

* መሪ በሌላትና በጦርነት ሁከት እየፈራረሰች ባለችው ሀገረ የመን የተለያዩ ከተሞች “በህገ ወጥ መንገድ ወደ የመን ገባችሁ!” ተብለውና በሌላም ሌላ ጥቃቅን ጉዳዮች ለተለያዩ እስር የተዳረጉ ዜጎቻችን የረሃብ ጥማቱ ችጋር በርትቶባቸው በአደጋ ላይ መሆናቸውን እየሰማን ነው

* 700 ያህል ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ሲያስረዳ፣ ጠኔ ረሀቡ በርቶባቸው ከሰንአ አቅራቢያ ያለ አንድ እስር ቤትን ሰብረው ሊወጡ ሲሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የመገደላቸውን፣ 11 ያህል የመቁሰላቸውንና የተረፉት በጠባቂዎች ዱላ መነረታቸውን ከወደ ሰንአ ግሩም ተክለ ሀይማኖት የተገደሉት ኢትዮጵያን በፈሰሰበት መሬት ላይ ቆሞ እንደነበረ በገለጸልን ልብ ሰባሪ መረጃውን ጠቁሞናል

* ከአውሮፓ ሀገራት እስከ እስያና ሩቅ ምስራቅ ሀገራት በየመን ያሉ ዜጎቻቸውን ለማውጣት ተረባርበው ተሳክቶላቸዋል።

* የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ለማውጣት መዝገባ በጀመረ ማግስት 30 ዜጎቹ በኤደን በኩል በጅቡቲ አድርገው ወደ ሀገር ቤት መግታቸውን አስታውቋል። ማን ረድቶ አሸጋገራቸው የሚለው አሁንም አወዛጋቢ ቢሆንም  መግባታቸው ግን እውነት ነውfile-12-1

* መንግስት በቀጣይ ዜጎችን ከየመን ለመመለስ “ጥረት እየተደረገ ነው” ተብሎ እስካሁን 3000 ገደማ መታወቂያና ፓስፖርት ያላቸው ተመርጠው መመዝገባቸው ይጠቀሳል

* ከተመዘገቡት መካከል ወደ ሀገር ትመለሳላችሁ ተብለው ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ መሳፈሪያው ያመሩ ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል

* ምዝገባው መታወቂያና ፖስፖርት ያላቸውን ብቻ ስለሚያካትት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን እና በባህር የገቡ ፖስፖርትና መታወቂያ የሌላቸው ተንገዋለው መቅረታቸውን በምሬት እየተናገሩ ነው ። ያም ሁሉ ሆኖ መስፈርቱን አሟልተው እየተለዩ ከተመዘገቡት ውስጥ ወደ ሀገር የተመለሰ እስካሁን አልታየም ፣ አልተሰማም!

ቸር ያሰማን  !
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 5 ቀን 2007 ዓም


* በ9ኛ  ቀን በሳውዲ መራሹ  “ወሳኙ ማዕበል!” የአየር ማጥቃት ዘመቻ በየመን  ሰማይ በተጠኑ ወታደራዊ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ አየር ድብደባው መቀጠሉን የዘመቻው መምሪያ ቃል አቀባይ ብ/ጀኔራል አህመድ አሲሪ ናቸው፣ ጀኔራሉ በዚሁ መግለጫ በወደብ ከተማዋ በኤደንም የሁቲ አማጽያ አልበገርላቸው ካለው የአካባቢ ሚሊሽያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውን አስረድተዋል

ብ/ጀኔራል አህመድ አሲሪ
ብ/ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* ከሁቲ አማጽያንን ኤደንን እንዳይቆጣጠሩ በአካባቢው ሚሊሽያ በመሬት ቃታ እየሳበ እንቅስቃሴያቸውን ሲያሽመደምደው በሰማይ የህብረቱን ጦር በተጠኑ ኢላማዎች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በሚከወነው ድብደባ አማጽያኑን አቅመ ቢስ አድርጎ እንዳዳከማቸው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል

* ቃል አቀባዩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሰርጎ የሚገባባትን በሚዮን ደሴት Meon Island የሚገኙ የባህርና ሃይሉና የእግረኛው  ጦር መሳሪያዎች በሳውዲ መራሹ የአየር ድብደባ ኢላማ ገብተው ተደምስሰዋልም ብለዋል

* በአየር ድብደባው ተስፋ የቆረጡና የተዳከሙት የሁቲ አማጽያን በመገናኛ ብዙሃንን ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን በማሳሳት ላይ ናቸውም ብለዋል ብ/ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* በሌላ በኩል እየተካሔደ ስላለው ዘመቻ ማብራሪያ የሰጡት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አልጃብሪ  ዘመቻው በጥሩና በመጥፎ መካከል እንጅ በሱኒና በሸአ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ሚካሔድ ጦርነት አለመሆኑን ተናግርዋል።  አምባሳደሩ በማከልም የሳውዲ መራሹ አረብ ሃገራት ዋና አላማ በኢራን በሂዝቦላህ የሚመራውን የሁቲ አማጽያን ከስልጣን አስወግዶ፣ ህጋዊው የፕሬዚዳንት አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው መመለስ ነው ብለዋል። አምባሳደሩods የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላህ ሳላህን በሚመለከት ሲናገሩ አሊ አብደላ ሳላህ ከሁቲዎች ጎን መሰለፋቸው  የተሳሳተ አካሄድ ነው ሲሉ ነቅፈውታል

በሳውዲ የመን ድንበር ድንበር መገዳደል . . .

* በሳውዲ የመን ድንበር ባሳለፍነው ረቡዕ አንድ ድንበር ጠባቂ በሳውዲ የመን ድንበር ሁለት የድንበር ጠባቂ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ትናንት አርብ ተጨማሪ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ተጠቅሷል። መረጃውን የድንበር ጦሩ ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል  አዎል ቢን ኢድ አል በላዊ አረጋግጠውታል

* የሳውዲው ንጉስ  ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የሟች የድንበር ወታደር ቤተሰቦችን ልዩ የሀዘን መልዕክተኞች በመላክ  አጽናንተዋልdeath

ከዘመቻው ድጋፍ እስከ የመንን መልሶ መገንባት  . . . .

* በሳውዲ ታላላቅ ምሁራንና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች በሳውዲ መራሹን የየመን አየር ድብደባ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው

* የመን ከሁቴ አማጽያን ጠርታ የፕሬዚደንት አብድል ረቡ መንሱር ሃዲ መንግስት በሁቲ አማጽያን የተቀማውን ስልጣን ተቀብሎ የመን ስትረጋጋ የባህረ ሰላጤው ባለ ሃብቶች 150 በላይ ፕሮጀክቶችን በመክፈት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ እቅድ መያዛቸው ተጠቅሷል
(መቸ ይመጣ ይሆን? ብቻ ለዚያ ቀን ያድርሰን. . .)

በየመን የኢትዮጵያ ይዞታና  የ”እውነት፣ ውሸቱ” እሰጣ ገባ

* በየመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት እንደደረሰበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴድሮስ አድሃኖምና መስሪያ ቤታቸው ከቀናት በፊት፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ቢያስታውቁም የተላለፈው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል።  በተባራሪ ጥይት በኢምባሲው የሚገኝን አንድ መኪና ጎማ መታ ተብሎ ጥቀሰት ብሎ ማቅረቡ የተጋነነ መሆኑን ከየመን ሰንአ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የኮሚኒቲ  ሰራተኞች ለመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ተመላሽ ዜጋዎች በመመዝገብ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል። የኢምባሲውን መደብደብ ዜና የሰሙት በቦታው ያሉትን የኮሚኒቲ ተወካዮች ሳይቀር በሚኒስትሩ ኢምባሲው ተጠቃ በሚል በቀረበው መረጃ ግራ የተጋቡ እንደነበር የአይን እማኞች ጠቁመዋልbombing yemen

* የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም “በየመን ሰነአ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ደረሰበት!” ያሉትን ሰሞኛ ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበት አነጋጋሪ መረጃቸውን  ተከትሎ “ከአውስትራልያ የመጣች ታዳጊ 20 ሚሊዮን… ለገሰች!” እንደተባለችው ታዳጊ ወጣት ስጦታ ገንዘብ ምንጭ ዙሪያ የተደረገውን ያህል ሙግት እሰጣ ገባ የየመኑ ጥቀሰት ባይገንም “እውነት፣ ውሸቱ” ግን ቀጥሏል (አሜሪካ ቢሆን ይህ ይደምቅ ነበር ያሉኝ አሉ)

* ከቀናት በፊት በኤደን የመን አድርገው ጅቡቲ የገቡት 30  ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ተጠቁሟል፣ “ወደ ሃገር ቤት መግባቱ ለደህንነታችን ያሰጋናል!”  ያሉት ግን ወደ ሶስተኛ ሃገር የሚሻገሩበትን መንገድ በመላ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን እናሰማላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ ናቸው!

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም


ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል” በ8ኛው ቀን ክንውኖች. . .
እና በየመን ሁከትና የኢትዮጵያውያን ይዞታ!

* “ኤደን በሁቲዎች እጅ አልወደቀችም!” የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ
* “በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተደብድቧል፣ 2000 ተመዝግበው 30 ጅቡቲ ገብተዋል” ቴድሮስ አድሃኖም
* በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመግባት ፍላጎት አላሳዩም፣ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው፣ በፖለቲካ የሸሹት የምህረት ጥሪ ይደረግላቸውም እየተባለ ነው

8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ . . .

ሁቲ አማጺያን
ሁቲ አማጺያን

ኤደን በሁቲ አማጽያን ስር መሆኗን አልጀዚራና የተለያዩ የአረብ መገናኛ ብዙሀን የጠቆሙ ቢሆንም ትናንት ማምሻውን በሪያድ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር ሆነው ለጋዜጠኞች ስለ 8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ የሰጡት የዘመቻው ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ  ኤደንን ለመያዝ ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ኤደን ሙሉ በመሉ በሁቲዎች ቁጥጥር ስር አለመውደቋን አስታውቀዋል።

በ8ኛው ቀን የአየር ጥቃት ዘመቻ መግለጫ የሰጡት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በኤደን አካባቢ እግረኛ ጦር ጀምሯል ወይ? ተብለው ተጠይቀው፣ እግረኛ ጦር አለመጀመሩን አስረግጠው ተናግረዋል። በዚሁ መግለጫቸውም በኤደን ዙሪያ ስለተደረገውና እየተደረገ ስላለው የዘመቻው ክንውን ሲያስረዱ በዋናነት በምድርና በባህር የሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እንዳያገኙ መንገዶችን የመዘጋጋት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል።  ከዚህ ባከፈ የእግረኛ ጦር ዘመቻ አለመጀመሩን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል።

ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ
ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ

“ከወሳኙ ማዕበል” የአየር ጥቃቱን አፋፍሞ በቀጠለበት ሁኔታ በየመን የድንበር ከተማ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው አሲር ክልል በሚያዋስን ድንበር ግጭት መቀስቀሱ ተጠቁሟል።  ባልታወቁ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስም ሰልማን አልመልኪ የተባሉ አንድ የበታች ሹም የድንበር ጠባቂ  ወታደር መገደላቸውንና 10 ያህል መቁሰላቸውን የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ አስታውቀዋል። የአየር ጥቃት ከተጀመረ ወዲህ በድንበር ይህን አይነት ክስተት ሲታይ የመጀመሪያው ሲሆን በተባለው ግጭት የሞቱት የድንበር ጠባቂ የቀብር ስነስርአትም ትናንት ሀሙስ በአብሃ ከተማ ተከናውኗል!

* የኢትዮጵያ ኢንባሲ መደብደብና አሳሳቢው  የኢትዮጵያውያን ይዞታ. . .

በየመን ሰንአ የኢትዮጵየ ኢምባሲ ባሳለፍናቸው ቀናት በጦርነቱ የድብደባ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን የኢፊድሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ባሰራጩት መረጃ አስታውቀዋል። በተፈጸመው ድብደባ የተጎዳ ሰው የለም ከማለት ውጭ በጦር መሳሪያ ተደበደበ ስላሉት ኢምባሲ የጉዳት መጠን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ግን የለም።

9
አገር ለቅቀው የሚወጡ የውጭ ዜጎች

በየመንን ሁከት ተከትሎ በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ወደ ሀገር ለመመለስ የተመዘገቡት 2000 ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ከተመዘገቡት መካከል 30 ያህል በጦርነት ከምትናጠው ከኤደን ተነስተው ጅቡቲ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መረጃ ያስረዳል። በየመን እያደር የጦርነቱ መባባስ ስደተኞችን የመመለስ ስራውን እንዳወሳሰበው የጠቆሙት ቴድሮስ በሚቀጥሉት ቀናት የተመዘገቡትን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ በተቻለው መጠን እንደሚደረግ አስረድተዋል። በመጨረሻም ባስተላለፉት መረጃ የብዙ ሀገር ዲፕሎማቶች የመን ሰንአን ለቀው ሲወጡ “ከዜጎቻችን በፊት አንወጣም!” ብለው እስካሁን የመን አሉ ላሏቸው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዲፕሎማቶች ምስጋና አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ከ5000 ስደተኞች ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በየመን በኩል ወደ ሳወዲ ለመግባት አስበው በተለያዩ የየመን ክልሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አዳዳቢ እንደሆነ ቀጥሏል። ወደ ሶስተኛ ሀገር እንጅ በኑሮው ውድነትና በፖለቲካው አለመረጋጋት ተማረው በUNHCR የስደተኛ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ግን ወደ መጡባት ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው። እኒሁ በጭንቅ ላይ ሆነው ወደ ሀገር የመግባቱ ነገር እንደ ተሻለ አማራጭ የማያዩት ወገኖች አማራጩ ጥሏቸው ከየመን የወጣው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን UNHCR ወደ ሶስተኛ ሀገር ያሸጋግራቸው ዘንድ የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችን እንዲማጸኑላቸው በተለያዩ አለማት ላሉ ኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው!

በየመን ሁከቱ እያየለ ከሄደና የሳውዲ መራሹ የ10 አረብ ሀገራት የምድር ጦር እግረኛ ማዝመት ከጀመረ ያለውን አማራጭ መጠቀም ባልፈለጉ ኢትዮጵያውያን ላይ የከፋ አደጋ እንዳያጋጥማቸው ስጋት ተደቅኖባቸዋል። በተለያየ ምክንያት ፖለቲካውን ሸሽት ሀገር ለቀው አሁን አደጋ ላይ ሲወድቁ ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ የእስራት ፍርዱን የፈሩ ዜጎች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል። ይህን መሰሉን ችግር ማቅለል ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ መንግስት  ከችግሩ ቀጠና ወደ ሃገር ለሚመለሱ ማናቸውም ስደተኞች የምህረት ጥሪ ያቀርብ ዘንድ በዚሁ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ወገኖች ያስረዳሉ!

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓም


5 ኛው ቀን ዘመቻ . . .

የዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል” አበይት ክንውኖች ዳሰሳ!

* በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል

* የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር  መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና  ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

* ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል

* በጦርነቱ መካከል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል። በጥብቅ በታጠረው የሳውዲ ድንበር ወዲህና ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጦረነቱ እሳት መካከል  በአጣብቂኝ ውስጥ ስለ መሆናቸው በግል የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በሳውዲ የመን ድንበር በባህር ጠረፎች ከፍተኛ የእግረኛና የባህር ኃይል ሰራዊትና የሜካናይዝድ ጦር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷልFaisal_Putin

* በሳውዲ ድንበር፣ በጀዛን እና በኤደን የባህር ወሽመጥ በባብ አልመንደብ አካባቢ የባህር ኃይልና የምድር ጦር ዝግጅቱን አስመልክቶ የተጠየቁት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ “በጦርነት ውስጥ እያለህ ይህ መሰሉ ዝግጅት የተለመደ ነው!” ብለው መልሰዋል

* የምድር ጦር በሚመለከት በአንድ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዠን የተጠየቁት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ በሳውዲ በኩል የምድር ጦር ለማዝመት እስካሁን ውሳኔ አለመደረሱን ጠቁመዋል

* የየመን ፕሬዚዳንት አብድልረብ መንሱር በሳውዲ ስደት ላይ ሆነው በኢምሬት የየመን አንባሳደር አድርገዋቸው  የነበሩትን አህመድ አሊ አብደላ ሳላህን ከስልጣን አባረሩ። አህመድ አሊ በአባታቸው የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የጦር መኮነን ነበሩ። በኢምሬት አምባሳደር የተሰጣቸው በፕሬዚዳንት አብድልረቡ ሲሆን ከነበሩበት ቁልፍ የጦር መሪነት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦታ ለማሸሸት ታስቦ ነበር። አህመድ የፕሬዚዳንት አብድልረቡ ወዳጅና የአሁን ሁነኛ ባላንጣቸው የሆኑት የቀድሞው ፕሬዚዳንት የአሊ አብደላ ሳላህ የብኸር ልጅ ናቸው፣ ከቅርብ ወራት ጀምሮ አህመድ ከአባታቸው ጋር ሆነው ፕሬዚዳንት አብድልረቡን ለማውረድ የሁቲ አማጽያንን በመደገፍ መሪውን አሽቀንጥረው የመንን ለዛሬ መከራ እንደዳረጓት ይወነጀላሉ

* ባሳለፍነው ቅዳሜ  መጋቢት 19 ቀን 2007 በግብጽ ሻርማ ሸክ የተደረገው የአረብ ሊግ ስብሰባና ውጤቱ የአረብ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው እየተዘገበበት ይገኛል

እዚህም እዚያም የቃላት ጦርነቱ ተጋግሟል …

* የሁቲ አማጽያን የሳውዲ መራሹን የጦር አውሮፕላን ጣልን ይላሉ፣ የሳውዲ መራሹን ጦር ቃል አቀባይ በአንጻሩ የሁቲ አማጽያን ከዚያ የሚያደርሰውን አቅም በመጀመሪያ ቀን የአየር ድብደባ ብቻ አክሽፈነዋል በማለት በተዋጊ ጀቶቻቸው ላይ ጥቃት አለመድረሱን በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል5th day

* በየመን የሁቲ አማጽያንን በሳውዲ መራሽነት የተጀመረው የአየር ድብደባ እንዲያቆም ከሚፈልጉት ሀገራት መካከል ቀዳሚ የሆነችው የራሻው ፕሬዚዳንት ፑቲን ለአረብ ሊግ ስብሰባ በላኩት ደብዳቤ አረብ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ሰላምን ለማምጣት ከጦርነት ውጭ ያለውን የሰላማዊ መንገድ አማራጭ ይጠቀሙ ዘንድ መክረዋል

* የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዑድ አል ፈይሰል ግን የፑቲንን መልዕክቱን ተቃውመዋል።  በኢራን የሚደገፈውን በሶርያ የአሳድን መንግስት የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ በራሽያ ስንቅና ትጥቅ ይደገፋል ሲሉ የራሻን ተቃርኖ መንገድ ላይ የሰላ ሂስ ያቀረቡት ልዑሉ የራሻው ፕሬዚዳንት ፑቲን ከአረብ ሀገራት ጋር የቆየ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ንግግራቸውን አርመው አቋማቸውን ይፈትሹ ዘንድ አሳስበዋል።

* ከኢራን እርዳታ በማግኘት የሚታሙት የሽምቅ ተዋጊው የሀማስ መሪዎች ሳውዲን ጭምሮ የ10 አረብ ሀገራትን ዘመቻ ሲደግፉ የኢራንና የሶርያ መንግስት ደጋፊ የሊባኖሱ የሂዝቦላህ መሪ ሸህ ሀሰን ነስርአላህ የሳውዲ መራሹን ዘመቻ በማውገዝ በተለይ በሳውዲ መንግስትን መወረፋቸው የሳውዲን መንግስት አስቆጥቷል

* በሊባኖስ የሳውዲ አምባሳደር አሊ አዎድ አሲሪ ጭብጥ የሌለው ሀሰት ነው ያሉት የሂዝቦላሁ ሀሰን ነስርአላህ ንግግር ሂዝቦላህ የሚወክለውን የኢራን አቋም የተንጸባረቀበት አሳሳች መልዕክት እንደሆነ ለአረብ ኒውስ አስረድተዋል

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም


በ4ኛው ቀን ዘመቻ

* ትናንት ቅዳሜ መጋቢት 19 ግብጽ ሻርማ ሸክ ተሰብስበው የነበሩት 22 የአረብ ሊግ ሀገራት መራሄ መንግስታት በ26 ኛው መደበኛ ስብሰባ የየመንን ጉዳይ በሰፊው ተነጋግረውበታል

* መራሔ መንግስታቱ የሁቲ አማጽያን በኃይል ከያዘው ስልጣን ለማስወገድና ህጋዊውን የአብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው ለመመለስ ተስማምተዋል!yemen1

* የሳውዲው ንጉስ ሰልማን “ዘመቻው ግቡን እስኪመታ አያቆምም!” ሲሉ የግብጽ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ በበኩላቸው የጽንፈኝነትን መንሰራፋት በማውሳት በአረብ ሀገራትን አደጋና ከኢራን ትንኮሳ ለመታደግ ጥምር የጦር የአረብ ሀገራት ሰራዊት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ በአጽንኦት ተናግረዋል

* ጉባኤው በአረብ ጥምር የህብረት ጦሩን ጉዳይ ከመከረ በኋላ በስብሰባው መዝጊያ የአብ ሊግ ዋና ጸሃፊ ነቢል አል አረቢ ባሰሙት የአቋም መግለጫ ከዚህ ቀደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያቀረቡት ረቂቅ ህግ ተጠንቶ በአጠቃላይ ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ ተገናኝተው በመምከር ታሪካዊ ያሉትን የህብረት ጦሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመመስረት እቅድ መያዙን አስታውቀዋል

* የኩዌትን አሚር ጨምሮ የተለያዩ አረብ ሀገራት ኢራን የአካባቢውን ሀገር ሰላም ለመንሳት በተዘዋዋሪ የምታሳየውን ተደጋጋሚ ፍላጎት ተቃውመውታል

* ፖለቲካ ነውና ያልተጠበቀው ይሆናል፣ የፍልስጥኤም መሪ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አባስ በአረብ ሊግ ስብሰባ የተገኙ ሲሆን ከኢራን ድጋፍ ያገኛል የሚባለው የፍልስጥኤሙ ሽምቅ ተዋጊ ሃማስ የአረብ ሀገራቱን አቋም የሚደግፍ አስገራሚ የድጋፍ መግለጫ አውጥቷል

* የየመንን ህጋዊ መሪ አብድልረቡ መንሱር አልሃዲን መንግስት ወደ ስልጣን ለመመለስ በሳውዲ የሚመራውን ዘመቻ እንደሚደግፈው ፍልስጥኤምን ነጻ ለማውጣት ጠመንጃ ያነሳው ሽምቅ ተዋጊው ሃማስ ዘመቻውን ደግፎ መግለጫ ማውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟልyemen al sisi

* ስድስቱ ኦማንን ሳይጨምር የባህረ ሰላጤ ሀገራትን ሳውዲ፣ ኢምሬት፣ ቃጣር፣ ኩዌትና ባህሬንን ጨምሮ ዮርድያኖስ፣ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ሞሮኮ በዘመቻው ተሳታፊ ሲሆኑ ቱርክ፣ ሞሮኮ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ቤልጅየም ድጋፍ መስጠታቸው ይጠቀሳል በአንጻሩ ሶርያ፣ ኢራን፣ ራሽያና ቻይና ዘመቻውን አጥብቀው ተቃውመውታል

* ኢራን የሁቲ ሸማቂዎችን በማስታጠቅና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች የየመን ፕሬዚዳንት አብድልረቡ መንሱርና የአረብ ሀገር መራሔ መንግስታት ቢጠቁሙም ኢራን የሚቀርብባት ውንጀላ ሁሉ “መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው!” ስትል አስተባብላለች

የትዕንግርተኛው የመን “ድብደባውን አቁሙ!” ተማጽኖ . . .

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ ከ30 ዓመት በላይ የመንን ሲያስተዳድሩ አቀማጥለው የደገፏቸው፣ የአረብ አብዮት መጥቶ ሀገር የመን ስትታመስና ፕሬዚዳንት አብደላ ሳላህ በአጥፍቶ ጠፊ ሲጎዱ አፈፍ አድርገው ህይወታቸውን የታደጉትንና ወደ ኋላም የመን በተቃውሞ ስትናጥና ስልጣናቸው አልረጋ ሲል መውጫ መንገድ ያበጁላቸው በቅርብ ሳውዲዎች፣ በርቀት የባህረ ሰላጤ ሀብታም አረብ ሀገራትና ምዕራባውያን ናቸው

* ዛሬ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከቁርጥ ቀን ደጋፊያቸው ከሳውዲ፣ ከአረብ ሀገራትና ከምዕራባውያን በተቃራኒ ጎራ መሰለፋቸው ይጠቀሳል፣ የቀድሞ ታዛዥ አጋራቸውና ስልጣናቸውን ሳይወዱ በግድ ያስረከቧቸውን የፕሬዚዳንት አብድልረቡ መንበረ ስልጣን እንዳይረጋ እንደ ኢራን በድብቅም ባይሆን በግላጭ ሁቲዎችን በመደገፍ የቀድሞው መሪና ልጃቸው አህመድ የመንን ለዚህ ውጥንቅጥ እንዳደረሷት ይጠቀሳልyemen2

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በ26 ኛው የአረብ ሊግ የመሪዎች ስብሰባ ለተቀመጡት መራሔ መንግስታት ሳውዲ መራሹ ዘመቻ ያቆም ዘንድ “ችግሩ የተፈጠረው በፕሬ አብድልረቡ የአስተዳደር አቅም ማነስ ነው፣ ድብደባውን አቁሙ፣ መፍትሔው በድርድር እንጅ በጦርነት አይደለም!” የሚል አንድምታ ያለው ትንግርተኛ ተማጽኖ በአንድ ታዋቂ የአረብኛ ቴሌቪዥን በኩል መልዕክት አስተላልፈዋል

* የቀድሞው ፕሬዚዳንት የቆየውን የሳውዲና የሀገራቸውን መልካምና ጠንካራ ግንኙነት፣ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የመናውያን በሳውዲ በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተው የመገኘታቸውን መልካም ጉርብትና በማውሳት ሳውዲ መራሹ ጦር በየመን ላይ የከፈተውን ዘመቻ ልጆቻችንና ሀገራችን እያወደመ ነው ሲሉ ድብደባው በአስቸኳይ ያቆም ዘንድ ልዩ መልዕክትን ለሳውዲ መንግስት አስተላልፈዋል

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በዚሁ ንግግራቸው የመንን በድርድር የማረጋጋቱ ስራ ቅድሚያ ይሰጠው ሲሉ የየመን ወቅታዊ ችግር በድርድር ከተፈታ በቀጣይ ምርጫ ቢደረግ እርሳቸውም ሆኑ የቤተሰብ አባሎቻቸው ወደ ስልጣን መንበር የመውጣት ፍላጎት እንደሌላቸው በንግግራቸው አስታውቀዋል

* የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ ልጆች መካከል የጦር መኮንኑ አህመድ በሶስተኛው ቀን የአየር ላይ ድብደባ እንደቆሰሉ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ጠቁመዋል። የተረጋገጠ መረጃ ነው ማለት ግን አይቻልም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀድሞው የየመን አስተዳደር በከፍተኛ የጦር ኃላፊነት ያገለግሉ ከነበሩት ውስጥ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ አህመድ በሳውዲ የተመራው ጦር የዘመቻ ጥቃት ከመደረጉ አስቀድሞ የሁቲ አማጽያንን ከስልጣን ለማስዎገድ እድሉ እንዲመቻችለት ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት አለማግኘቱን አል አረቢያ ዘግቦታል

የሁቲዎቻ ዛቻና የዘመቻው መምሪያ መግለጫ

* የሁቲ ከፍተኛ ባለስልጣን አብል ሙንኢም አል ቁረሽ የሳውዲን ጣልቃ ገብነት በዚህ ከቀጠለ ሳውዲ ልትቆጣ ጠር የማትችለው ጥቃት እንሰነዝራለን ሲሉ ለኢራን አል ፋሪስ ዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ ዝተዋል

* በሁቲዎች ዛቻና በዘመቻው ዙሪያ ትናንት መግለጫ የሰጡት በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር ቃል አቀባይ  ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ስለ አራተኛው ቀን የአየር  ድብደባ መግለጫ ሰጥተዋል

* ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በተለያዩ ከተሞች በዘመቻው መምሪያ በተጠኑ የሁቲ አማጽያን ወታደራዊ ኢላማዎች አልፎ ወደ ሳውዲ የመን ድንበር የጀዛንና ነጅራን ዘልቀው ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ የሁቲ ቡድን አባላት እግር በእግር  እያታሰሰ የመደምሰሱ ስኬታማ ስራ መስራቱን የዘመቻው ቃል አቀባይ አስረድተዋልyemen3

* ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በዚሁ መግለጫቸው በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር በሁቲ አማጽያን እጅ የነበረውን የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ballistic missile stockpile በአብዛኛው ማውደሙን አስታውቀዋል

* ከየመን ሰንአ የህብረቱ የአየር ኃይል ጦር የደቡብ ከተማዋ በዳሊያ ባደረገው ወታደራዊ ይዞታዎች ኢላማ ያደረገ ድብደባ የሁቲ አማጽያን ጸረ አውሮፕላን በመተኮስ መልስ መስጠታቸውም ተጠቁሟል

* ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉ የሳውዲ ፣ የምዕራባውያን ሀገር ዲፕሎማቶች እና የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞችን በተለያየ ዘመቻ ሰንአ የመንን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 20 ቀን 2007 ዓም

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. amaz says

    September 15, 2015 10:57 am at 10:57 am

    ሁቲ ነፃ አውጭ ግንባር ናቸው ሊደበደቡ አይገባም እነሱ በሳወዲ መራሹ ጦር መደብደብ ለሳውዲ ታማኝ የሆነውን አብደረቡር መንሱር ሀዲን በስልጣን አቆይቶ አሻንጉሊት ለማድረግ ነው እንጂ ማ አሳድን ለመጣል በሶርያ የሚዋጉትን ለምን አለደበደቡም በተቃራኒው ያስታጥቃሉ freedom fighter እያሉ ያሞካሻሉ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule