• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መጪው ጊዜ ለናይጄሪያ “ብሩህ” ይሆናል!!

April 4, 2015 04:22 am by Editor 2 Comments

በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ የፖለቲካ አካሄድ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያመጣል የተባለው የሰሞኑ ምርጫ ውጤት ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት የመንፈስ ልዕልና አጎናጽፏቸዋል፡፡ በበርካታ ችግሮች ለተወጠረችው ናይጄሪያ “ብሩህ ጊዜ” ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን በምክትልነት ናይጄሪያን እያገለገሉ በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዑማሩ ሙሳ ሕይወታቸው በማለፉ ወዲያው የፕሬዚዳንትነት መንበሩን ተረከቡ፡፡ ዑማሩ ሙሳን ተክተው ጥቂት እንዳገለገሉ በወቅቱ በተካሄደ ምርጫ ሙሐማዱ ቡሃሪን አሸንፈው ናይጄሪያን ለአምስት ዓመታት መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የዛሬ አምስት ዓመት ባሸነፏቸው መልሰው ተሸንፈው ሥልጣናቸውን በሰላም አስረክበው በናይጄሪያ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ተግባር በመፈጸም ስማቸውን ከመቃብር በላይ ህያው አድርገዋል – ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን!!

ፕሬዚዳንት ዮናታን በሥልጣን በቆዩባቸው ዓመታት በርካታ ተግባራትን እንዳላከናወኑ እንዲያውም ላሁኑ ሽንፈታቸው እነዚሁ ጉዳዮች እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ የቦኮ ሃራም፣ የሙስና፣ የኢኮኖሚ አለማደግ፣ ወዘተ አንኳር ጉዳዮች ዮናታንን እንዳይመረጡ እንዳስደረጓቸው በስፋት ከሚነገሩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በምርጫው ዘመቻ ወቅት ውጤቱ ምንም ይሁን ግልጽና ፍትሐዊ ምርጫ በናይጄሪያ እንደሚደረግ ቃል የገቡት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ቃላቸውን ጠብቀዋል፤ የተናገሩትን ፈጽመዋል፤ የጀመሩትን ጨርሰዋል፡፡ የመራጩ ሕዝብ ድምጽ ሙሉ በሙሉ ተቆጥሮ ከመጠናቀቁ በፊት መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተቀናቃኛቸውን ጄ/ል ሙሐማዱ ቡሃሪን “እንኳን ደስ አልዎት” በማለት አመስግነዋቸዋል፡፡ ለናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በሕዝብ በመመረጣቸውም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ የሕዝብን ድምጽ እንደሚያከብሩ የሰጡትን ቃል በመፈጸም በአገራቸው ታሪክ የማይረሳና የማይሻር አሻራቸውን አትመዋል፡፡ ደም መፋሰስን ገትተዋል፤ ውድመትን፣ ጥላቻን፣ መራርነትን፣ ወዘተ አክሽፈዋል፤ የማያቋርጠውን የሥልጣንና የአምባገነንነትን አዙሪት ሰብረዋል፤ በዚህ ተምሳሌነታቸው እንደ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ እምነት ለሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ብቻ ሳይሆን ለኖቤልም ብቁ ተሸላሚ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡

ጉድላክ ዮናታን በአገሪቱ ሚዲያ ባስተላለፉት “ሽንፈትን የመቀበል” መግለጫ ላይ “ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ቃል ገብቼ ነበር፤ ቃሌን ጠብቄአለሁ፤ ከዚህ በተጨማሪም ናይጄሪያውያን በዴሞክራሲ ሒደት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምህዳሩን አስፍቼአለሁ፤ ይህ ለአገሬ ትቼ የማልፈው አንዱ ውርስ (ሌጋሲ) ነው፤ ወደፊት እንዲቀጥልም እመኛለሁ” ብለዋል፡፡ ምርጫው ሰላማዊና የተሳካ አንዲሆን የአገሪቱ የደኅንነት ኃይል ላከናወነው ሥራ አድናቆታቸውን ችረዋል፤ የፓርቲ ሰዎቻቸውን እና ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር የተጠቀመውን የናይጄሪያን ሕዝብ አመስግነዋል፤ በመጨረሻም ለጄኔራል ሙሃማዱ ቡሃሪ መልካሙን ሁሉ በመመኘት አገራቸውን ፈጣሪ እንዲባርካት በመማጸን ንግግራቸውን አጠናቀዋል፡፡

ሙሃማዱ ቡሃሪ ከጉድላክ ዮናታን የመልካም ምኞት መልክት ሲቀበሉ
ሙሃማዱ ቡሃሪ ከጉድላክ ዮናታን የመልካም ምኞት መልክት ሲቀበሉ

በአገራችን ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ አኳያ የናይጄሪያው አስቀድሞ መከሰቱ፤ ውጤቱ ያልተጠበቀ መሆኑ እንዲሁም የሥልጣን ሽግግሩ “በመተካካት” ሳይሆን በሕዝብ ምርጫ መከናወኑ የበርካታዎችን ቀልብ የሳበ ሆኗል፡፡ በተለይም በናይጄሪያ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለ ፕሬዚዳንት በምርጫ ተሸንፎ ከሥልጣን ሲለቅ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ገዢዎቿ ካልተፈነቀሉ ወይም ካልሞቱ ወይም ካልተሰደዱ መሪ ለመለወጥ ታድላ የማታውቀው አገራቸው ለዚህ ዕድል የምትበቃበት ዘመን መቼ እንደሚሆን የሚጠይቁና የሚወያዩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሚወዳደሩበት አካባቢ ለጎልጉል የተላከው መልዕክት እንዲህ ይላል፤ “በመጪው ምርጫ ብዙ አንጠብቅም፤ ሃይለማርያምም “ውርስ ተቀባይና አስፈጻሚ” እንደመሆናቸው ብዙ ይከውናሉ ብለን አንጠብቅም፤ ቢያንስ ግን እርሳቸው በሚወዳደሩበት ቦታ ፍትሓዊ የምርጫ ውድድር እንዲኖር በማድረግ ለፓርቲያቸው ሳይሆን ከፓርቲቸው በላይ ለሆነው ሃይማኖታቸውና ለሚያመልኩት አምላክ ታማኝ ቢሆኑ ይበቃናል”፡፡

ጉድላክ ዮናታን በወሰዱት እርምጃ “ከአፍሪካ መልካም ነገር አይወጣም” ለሚሉት ምዕራባውያን የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆነዋል፤ በርካታዎችን አስገርመዋል፤ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች “የጀመሩትን መጨረስ” ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አሳይተዋል፤ በተለይ “ምርጫ” ለማድረግ ደፋ ቀና ለሚሉ ምን ዓይነት መንገድ መከተል እንደሚገባቸው ሽንፈትን በመቀበል እንዴት አሸናፊ መሆን እንደሚቻል መስክረዋል፤ ለአገራቸው መጪው ዘመን “ብሩህ” እንዲሆን ታላቅ ተስፋ ፈንጥቀዋል፡፡ መልካም ዕድል (ጉድላክ) ዮናታን!


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    April 4, 2015 11:37 am at 11:37 am

    አዎን! ይችን አጋጣሚ ስንት ሰው ጓጉቶላት ነበር!?ብጥብጥ ቢነሳ እጀ-እረጃጅሞች የት እንደሚደርሱ..አጫጭሮች ማን ትከሻ ላይ ፊጥ ብለው እንደሚታዩ.. የማይታዩ፣ የማይዳሰ፣ሱ የማይጨበጡ፣ ሕዝብን ቀውጠው እንዴት ሳይነግዱ እንደሚያተርፉ…ያለው የሌለውን እንዴት እንደሚሸፍን..የሌለው ያለውን እንዴት አንደሚቦጭቅ…በዚች ግርግር ሀገርና የህዝብ ሀብት እንዴት እንደሚባነን…ማስረጃና መረጃ እንዴት እንደሚጠፋ ያለሙ፣ ያቀዱ፣ ያሰቡና ያሳሰቡ..ያሰፈሰፉ የውስጥም የውጭም ጃርቶች ውጥን እንዲህ በድምፅ ሲመክን መልካም ነው።

    **”ነዳጅ አምራች በሚባሉ ሀገራት ክብሪት በነፃ ይታደላል” ናይጄሪያ በሕዝብ ብዛትም ይሁን በሀገሪቱ ቆዳ ስፋት፣ ባላት ፎቅና መንገድ እርዝመት ሳይሆን ህዝቦቿ ፷ በመቶ ከድህነት ወለል በታች ያሉ ናቸው። አንድ መንግስት ሕዝቡን አስርቦ ለውጥ ሳያመጣ በሥልጣን ላይ የተቀመጠበትን ዘመን በመቁጠር የሕዝብ አበሳን አስቆጥሮ፣ ጥቂቶችን ገንዘብ አብዛኛውን ቂም አስቋጥሮ፣ መጪውን ትውልድ የብድር ዕዳ አቁፋዳ አሸክሞ፣ የሚገሰግስ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሙስና መር ኢኮኖሚ ዕድገትና ግስጋሴ ከአፍሪካ አንደኛ! ከዓላም ሁለተኛ! የሚሉ ቧልት፣ ፌዝ፣ ሽሙጥ፣ ሲሾመጥጥ ጥሩ አይሆንም!? ይህን ያገናዘበው የናይጄሪያ ምርጫ አሳታፊ፣ ፍትሃዊ፣ የሠላም የሥልጣን እርክክብ ትልቁን ክብርና ሞገስ ሊቸረው የሚገባው በሀብት በወታደሩ ብዛት ያልተመካውን በሕዝብ ደምፅ ያመነውን…ጉድላክ ዮናታን…እንኳን ደስ አለዎ አሸንፈዋል!።
    *** ለሀገራቸውና ሕዝባቸው መልካምን በማሰብ ተፎካካሪያቸውን ግባና ሞክረው ‘ጉድላክ’ ማለታቸው የአሸናፊ ታሪክ አስተላላፊነታቸው በቀሪው ዘመናቸው የጠቀለሉትን ሁሉ ሳይጠቀለሉ ፈተው በማስረከባቸው ‘ዮናታንን ጉድላክ ብለናቸዋል…”መለስ ዜናዊን ነፍስ ይማር! ኅይለመለስን ቀስ ብሎ ያብርር! ከኢህአዴግ መንፈሳዊ ቅናተኛ ይችን ተግባር ነጥብ ሳይቀር እንዳለ ቃልበቃል ይኮርጅና ያሳየን….ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን

    Reply
    • pheniel says

      April 21, 2015 04:22 pm at 4:22 pm

      ስለ ቦኮሀሬ በደንብ ቢፃፍ?

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule