• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጨለማው ሳምንት

April 20, 2015 01:02 am by Editor Leave a Comment

ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት!

“ወንድሞቼ ያልፍልኛል ብለው ከቤት እንደወጡ እዚያው በበረሃ ቀሩ።” ትላለች እየሩሳሌም። እትብታቸው የተቀበረባትን ሃገር ለቀው ሲወጡ ጣሊያን ለመግባት ነበር ዕቅዳቸው። አውሮፓን አልመው ቀዬአቸውን ለቅቀው የወጡ እነዚህ ወጣቶች ህልማቸው እውን ሊሆን አልቻለም። ከሌሎች 28 ወገኖቻችንን ጋር ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ህይወታቸው አለፈች። ‎ISIS የተባሉ ጨካኞች ሲያርዷቸው በቪደዮ አሳዩን።

የሳምንቱ ሃዘን እጥፍ ድርብ ነው። ኢትዮጵያዊ ላይ ያነጣጠረ እስከሚመስል ድረስ ነው እየተካሄደ ያለው። ብሔራዊ መንግስት ስለሌለን ብሄራዊ ውርደታችን አላቆመም።  ከ 700 በላይ ስደተኞችን ይዛ ወደ አውሮፓ ትጓዝ የነበረች ጀልባም በዚህ ሳምንት ነበር በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሰመጠችው። ቁጥሩን ለማረጋገጥ ባይቻልም፣ ከሞቱት ገሚሱ ኢትዮጵያውን እንደሆኑ ከወደ ጣልያን የሚመጣው መረጃ ይጠቁማል።

በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በቁም ሲቃጠሉ እና ሲገደሉ እያየን ነው። በተለይ ደርባን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እስካሁንዋ ደቂቃ በፍርሃት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል።

የመን ያሉ ወገኖቻችንም ምጥ ላይ ናቸው። የመን ያሉ ኢትዮጵታውያን ቁጥር ከምናስበው በላይ መሆኑ እጅግ ይረብሻል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ.ኦ..ኤም እንደሚለው ከሆነ በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር አንድ ሚልዮን ይጠጋል። ሁሉም በጭንቅ ላይ ናቸው። ያለመታደል ሆኖ የሚቆረቆርላቸው መንግስት ግን አላገኙም። ልብ በሉ ከአንድ ሚሊዮን ዜጋ፤ በስልጣን ላይ ያለው መንግስታችን 30 ዜጎቼን በጅቡቲ አድርጌ ወደ ሀገር ቤት አስገባሁ ሲል አብስሮልናል። በእርግጥ ይህ ጉዳይ በሊቢያው ክስተት ከሰጡት ምላሽ አይብስም። የ ISIS አሸባሪዎች ኢዮጵያውያንን አረድን ባሉ ግዜ “ጉዳዩን እናጣራለን” ሲሉ ነበር የቀልዱብንል። ከዚህ ድርጊት የባሰ ምን ሊመጣ ይችል ይሆን? በበረሃ የወደቀን ወገን፣ የትና በምን አግኝተው ነው የሚመረምሩት። አለሁ ባይ አካል ስለሌለን የተረሳን እና የተዋረድን ህዝቦች ነን።

እንደሌሎች ሀገሮች በአለማቀፍ መድረክ የሚከራከርልን አካል ስለሌለን የጥቃት ሰለባ እንድንሆን ተደርጓል። ሃገራችንም ጥርስ የገባች ሃገር ሆናለች።

ይህንን ስረዓት እየሸሹ እየሄዱ አውሬ የሚበላቸውና በረሃ ወድቀው የሚቀሩትን ወገኖች ቤቱ ይቁጠረው። በሳውዲ ጀምሮ የመን ተከትሎ ከዚያም በደቡብ አፍሪካ እና በሊቢያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በተለያዩ አረብ ሃገሮች በቃላት መግለጽ የማይቻል ድርጊት እየተፈጸመብን ነውና ሁላችንንም እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው።

ሰው ወድዶ አይሰደድም። ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ይሰደዳል፣ የተገፋ ህዝብ ይሰደዳል፣ ፍትህ ያጣ ህዝብ ይሰደዳል፣ የተራበ ህዝብ ይሰደዳል። ስደት እስካለ መከራውም ይኖራል።

የሃዘን ቀን ቢታወጅልንም፣ ባይታወጅልንም ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም። በዚህ ጨለማ ሳምንትም ሆነ ከዚያ በፊት በሆነው ነገር ሁሉ ልባችን ተነክቷል። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጠለቀ የሃዘን ስሜት ውስጥ ነን።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አሜሪካዊትዋ ባለስልጣን፣ ዌንዲ ሼርማን መንግስታችን ስኬትን እያስመዘገበ እንደሆነ በዚሁ ሳምንት ነበር ያበሰረችን። ዜጋው ሁሉ ተስፋ ቆርጦ እየተሰደደ በየበረሃው መውደቁን ይሆን ዌንዲ እንደ ስኬት የቆጠረችው?

የማያልፍ የለምና ይህም ጊዜ ያልፋል። እስከዚያው ግን ወዳጅ ዘመዳቸውን ያጡ ሁሉ ፈጣሪ ብርታቱን ይስጣቸው። መፍትሄው ታድያ ፍትሃዊ ስርዓትን እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። ይህ ሲሆን የስደት ምንጩ ይደርቃል።

Filed Under: Uncategorized Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule