"የኢትዮጵያ ሃየር መንግድ ለአፍሪካ ኩራት ነው" ሲባል ከቃላት መፈክርነት ባለፈ የአውነትም ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ የሚያድርባቸው ዜጎች እንደሚኖሮ እገምታለው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በረዥም ታሪኩ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በአንፃራዊነት በተቋሙ ውስጥ ስማቸው እጅግ የገነነ ብቁ አብራሪዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች (ግራውንድ ቴክኒሻን) እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በአብዛኛው በኢትዮጵያዊያን የተሞላ ነው፡፡ ለዚህም ነው የአፍሪካ ኩራት ለመባል የበቃው፡፡ ይህ ኩራት እና አድናቆት ከታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጀምሮ ጥቂት በማይባሉ አፍሪካዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ነው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሎሜ፣ማላዊ እና ቶጎ በመሳሰሉ የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ አክሲዮን ሼር በመግዛት እያስተዳደረ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ … [Read more...] about የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና …
Archives for February 2014
ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ
ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ በረዳትነት የሚያበረውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ካሳረፈ ወዲህ የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛውን ትኩረት ይዞ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ድርጊት በኋላም በሁለቱም ጎራ ያሉ አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በተመለከተ የተለያየ መላምት ትችትና ነቀፋ ሲሰነዝሩበትና ሲሰናዘሩበት ሰንብተዋል፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን ጀግና ነው አርበኛ ነው ሲለው “መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ከሀዲ ነው ብለውታል፡፡ እነኝህ ሁለቱም አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በየበኩላቸው ያሉትን ለመሆኑ የየራሳቸውን ማስረጃ የሚሏቸውን ነገሮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ክፍል ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና ነው የሚሉበትን ምክንያት ሲጠቅሱ በአገዛዙ ተማሮ … [Read more...] about ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ
“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”
የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ … [Read more...] about “ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”
ለስምህ ስም ሁነው
ከሚለጥፍብህ ከአፉ እንደመጣ ሚሻለውን መርጠህ ለራስህ ስም አውጣ ሺ ጨዋ ብትሆን ሚልዮን ጥንቁቅ ሰው ሰው በሰውነትህ የሚልህ ስላለው በችሎታህ መጠን ኪሎህን መዝነህ ጭማሪ መጠሪያ ስም ስጠው ለራስህ ሚጠራህ ከጠፋ አንተ ባወጣኸው በተግባር ታይና ለስምህ ስም ሁነው። … [Read more...] about ለስምህ ስም ሁነው
ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በጀርመን ተካሄደ
እ.ኤ.አ. በፌብሯሪ 22, 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) በኑረንበርግ ከተማ በጠራው የሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የድርጅቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው ወገኖች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። የድርጅቱን የሩብ ዓመት እንቅስቃሴ ሪፖርት በማቅረብ የዕለቱን ፕሮግራም ያስጀመሩት የድርጅቱ የፕሮፖጋንዳና የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ አቶ በየነ መስፍን ሲሆኑ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይም የፓናል ውይይት ተደርጓል።በተለይም የወያኔ መንግስት በማናለብኝነት ከመጋረጃ ጀርባ በዳር ድንበራችን ላይ እያደረገ ያለውን ቁማር ከማውገዝ ባሻገር ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ክህደት በተጨባጭ በተግባር ለመቀልበስ ምን ይደረግ በሚለው ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ሃሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን በቅርቡ የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አለምነው መኮነን የአማራ ህዝብን የሚያንቋሽሽ ፀያፍ … [Read more...] about ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በጀርመን ተካሄደ
‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ነጐዱ። ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች አምባገነን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል። በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በዓለም ዙሪያ በተለያየ ዘመን ወደ ሥልጣን ከመጡት መሰል ፀረ-ሕዝብ መንግሥታት ቢብስ እንጂ በምንም መልኩ … [Read more...] about ‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!
ትዝታ በ60/በስድሳ
ወደ ኋላ ሄዶ አበባ ሲፈካ፣ ጊዜ ሲተካካ፣ ልጅ ስልጣኔ መጥቶ በራችን ሲያንኳዋካ፤ ከባህል ጥል ገጥሞ ለመኖር ለብቻው፣ ማየት ማስተዋል ነው፣ ኧረ የሰላም ያለህ ተው አይሆንም ሲለው ባህል ሲማጠነው ደባል እንዲሆነው፤ (ቀሪውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ትዝታ በ60/በስድሳ
የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤ በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሃከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሃት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልጹ ጥቂቶች በብዙሃኑ ደም ዎኝተው … [Read more...] about የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ "ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?" ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር። ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው … [Read more...] about ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)
በድሉ ዋቅጅራ ‹የሌላቸው ባለቤቶች› የሚል ቅራኔ ውስጥ የገባው ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ተነሥቶ ነው፤ አንዳንዴ ሁኔታዎች እያስገደዱን ቅራኔዎችን እንቀበላለን፤ አንድ ጌታ አሽከራቸውን ይጠሩና ባላገር ወደሚኖሩ እናታቸው ዘንድ ይልኩታል፤ ነገር ግን ‹ሞተው ከሆነ እንዳትነግረኝ› ብለው አስጠንቅቀውት ይሄዳል፤ ሴትዮዋ ሞተው ይደርሳል፤ ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው፤ ሲያንሰላስል ብዙ ቀናት ከቆየ በኋላ ጎፈሬውን ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ይላጭና ግማሹን ብን አድርጎ ያበጥርና ጌታው ዘንድ ይቀርባል፤ አንዴ ጎፈሬውን እየነካካ፣ አንዴ የተላጨውን እየዳበሰ ጥያቄዎቻቸውን ሲመልስ፣ ጌታው ተቆጡና ‹ምንድን ነው የምታድበሰብሰው አርፈው እንደሁ በወጉ አትነግረኝም!› ብለው ሲጮሁበት ‹አዬ ጌታዬ አርስዎ መቼ በወጉ ላኩኝና!› ብሎ መለሰላቸው። የበድሉ ‹የሌላቸው› በግማሽ እንደተላጨው ጸጉር ነው፤ … [Read more...] about የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)