እጅግ የረቀቀው ፤ የሰው ልጅ ሠልጥኖ እጅግ መራቀቅን ፤ ሀ ያለው ጀግኖ ለመቸውም ቢሆን ፤ ሆኖ የታደለ ለሥልጣኔው ግንብ ፤ መሠረት የጣለ ረቂቅ ሥዕላትን ፤ ነው ያኔ እንደሣለ ያለእነዚያ ሥዕሉ ፤ በአገልግሎታቸው አይገቡበት ነገር ፤ ምንም ስለሌለው እንኳን እዚህ ሊደርስ ፤ እረቆ ሊማማር ምንም ምን ለማድረግ ፤ ከቶም አይችል ነበር በዓይን የማይታዩን ፤ በመሣሪያም ቢሆን የማይዳሰሱም ፤ ብቻ የሚሰሙን የሣለ ዕለት ነው ፤ ድንቅ አድርጎ እነሱን በጆሮዎቹ ብቻ ፤ የሚያዳምጣቸውን ለተለያዩ ድምፆች ፤ መልክ ቅርጻቸውን እነ አበገደን ፤ እነ አሌፍ ቤትን የሣለ ጊዜ ነው ፤ ጥንት በድሮ ዘመን የኛ አያቶች ደግሞ ፤ በዚህ ጥበባቸው እጅግ በረቀቀው ፤ የሥዕል ሞያቸው የሚያህላቸው የለም ፤ … [Read more...] about ዕጹብ ሠዓልያን