እ.ኤ.አ. በፌብሯሪ 22, 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) በኑረንበርግ ከተማ በጠራው የሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የድርጅቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው ወገኖች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።
የድርጅቱን የሩብ ዓመት እንቅስቃሴ ሪፖርት በማቅረብ የዕለቱን ፕሮግራም ያስጀመሩት የድርጅቱ የፕሮፖጋንዳና የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ አቶ በየነ መስፍን ሲሆኑ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይም የፓናል ውይይት ተደርጓል።በተለይም የወያኔ መንግስት በማናለብኝነት ከመጋረጃ ጀርባ በዳር ድንበራችን ላይ እያደረገ ያለውን ቁማር ከማውገዝ ባሻገር ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ክህደት በተጨባጭ በተግባር ለመቀልበስ ምን ይደረግ በሚለው ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ሃሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን በቅርቡ የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አለምነው መኮነን የአማራ ህዝብን የሚያንቋሽሽ ፀያፍ ንግግርን ኢሕአፓ የግለሰቡ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የወያኔ መንግስት አቋም ነው ብሎ የሚያምን ሲሆን አገዛዙም ለህዝብ ንቀት ባላቸው ነውረኛ ግለሰቦች የተሞላ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም በቅርቡ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን አውሮፕላን የጉዞ አቅጣጫ በማስቀየርና ጄኔቭ በማሳረፍ የፖለቲካ ጥገኝነት በጠየቀው ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ድርጊት የወያኔ መንግስት የግፍ አገዛዝ እርቃኑን የታየበት በመሆኑ በቅርቡ በጀርመን በሚገኙ የሲቪክ ማህበራት አማካኝነት በስዊዘርላንድ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚዘጋጁ ሰልፎች ላይ ሁሉም ዜጎች በመሳተፍ ለፍትህና ለነፃነት በፅናት መቆም እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
Leave a Reply