የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡
ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡
ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡
ናይጄሪያም ከአንድ ወር በፊት ተመሳሳይ ሕግ ያወጣች ሲሆን የዑጋንዳው ሕግ በረቂቅነት ከወጣ የዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ምዕራባውያን ከፍተኛ ተጽዕኖ በማድረግ ሕጉ ተግባራዊ እንዳይሆን፤ ከሆነም በአብዛኛው የህጉ ክፍል እንዲሸራረፍ በርካታ ሙከራዎችን፣ ማስፈራሪያዎችንና ውስወሳዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡
በአሜሪካ የፕሬዚዳንት ኦባማ አፈቀላጤ የህጉን መጽደቅ “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ዑጋንዳ ባስቸኳይ ሕጉን እንድትሰርዝ የጠየቁ ሲሆን አሜሪካ ከዑጋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምታጤነውም ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንም በበኩላቸው የሕጉን መጽደቅ የኮነኑ ሲሆን የተወሰኑ የአውሮጳ አገራት ለዑጋንዳ የሚሰጡትን ዕርዳታ እንደሚያቋርጡ ዝተዋል፡፡ ሌሎች አገራት ግን እንዲህ ዓይነቱ የዕርዳታ ማቋረጥ ውሳኔ ዑጋንዳውያንን የሚጎዳ በመሆኑ እርምጃው መወሰድ የለበትም ይላሉ፡፡
የዑጋንዳ ሕግ አውጪዎች ያረቀቁትን ሕግ በፈረሙበት ጊዜ ሙሴቪኒ እንዳሉት ምዕራባውያን በዑጋንዳ ጉዳይ በግልጽ ጣልቃ እየገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “አፍሪካውያን በሌሎች ላይ የራሳችንን አመለካከት አንጭንም” ያሉት ሙሴቪኒ ምዕራባውያን እስካሁን ያደረጉት ጣልቃገብነት ትክክለኛ እንዳልነበረ እና ይህም ደግሞ “ማኅበራዊ ኢምፔሪያዝም” ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡ ግትርና ግዴለሽ ምዕራባዊ ድርጅቶች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፋፋት እየጣሩ መሆናቸውንና ለዚህም ሰዶማዊነት ተግባር የኡጋንዳን ህጻናት እየደለሉ ወደ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሚያስገቧቸው ከሰዋል፡፡ በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሰዶማውያን ደሃ ዑጋንዳውያንን ዒላማቸው በማድረግ በገንዘብ በመደለል ለግብረሰዶማዊነት እንደሚጋብዟቸውና ቀጥሎም ለግብረሰዶማዊ አዳሪነት እንደሚዳርጓቸው ሙሴቪኒ ተናግረዋል፡፡
የዑጋንዳን ውሳኔ አስመልክቶ የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሙያ የሆኑ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት “ኢህአዴግም ከየምዕራቡ ለሚለቃቅመው ዕርዳታ ብሎ የአገርን ባህልና ማኅበራዊ እሴት ከሚያጠፋ ይልቅ ተመሳሳይ ተግባር ሊወስድ ይገባዋል፤ የተቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት በጸረ አሸባሪ ህግ ስቃዩን ከሚያሳይ የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በማውጣት ይህንን በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ወረርሽኝ መላ ሊለው ይገባል” ብለዋል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
sara says
I am so happy when i read god blessed you Uganda, the lord hands be With Uganda
Ppl and With this greatest leader,
andnet berhane says
በግብረ ሶዶማውያን ወይም የዚህ ወረርሽኝ አስፋፊዎች የተወሰደው የህግ ረቂቅ አስፈላጊነቱ እንደ ሃገር ገደብና ተግባሩ ትክክል አለመሆኑን ለሕብረተሰቡ ሕጋዊ ጥንቃቄ መስጠት በፈጣሪም ትእዛዝ (በመጽሐፍ ቅድሱ ውስጥም ) በመተላለፍ ቅጣት ተደርጓል ስለዚህም የኡጋንዳ መንግስት ያስተላለፈው ያጸደቀው ውሳኔ ሰባዊ መብትን የሚጻረር ባለመሆኑ እንደ ግለሰብ እደግፋለሁ፡ ነገርግን ለሚደረገው ምንኝውም ቅጣት እርምጃ ከተግባሩ እሚታቀብበት የሕክምና የስነአይምሮ የሃይማኖት እርዳታ በመድረግ ተፈላጊው እንክብካቤና ምክር በመስጠት እንዲረዱ እንጂ እስርቤት በበለጠ የከፋና የተዛመተ አደርገዋል የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብትም ለድነዚህ ያለ አሳፋሪ ተፈጥራዊና ባህላዊ ከማጥፋት በዚህ ተግባር የተሰማሩ ወይም የተለከፉ ወገኞች በተማሩትና ባላቸው ሞያ ሀገርና ሕብረተሰቡን በመርዳት የሚችሉበት ከበሽታው እሚፈወስበት መንገድ ይፈጠር እላለሁ፡ ማሰር መፍትሄ የለውም ። በጣም ከሚገርመው ጉዳይ በዚህ ሕግ ላይ የአሜሪካው ጆን ኬሪ የሰጡት መግለጫ ይህ ሕግ ለኡጋንዳውያን አሳሻኝ ነው ሰባዊ መብትም መጣስ ነው ሲሉ ድጎማውም እንዲቋረጥ ሲሉም ተሰምተዋል፡ ያሳዝናል በኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገር እየተፈጸመያለውን የመብት ጥሰት የፍትህ መጓደል ያለውን እምባ ገነን ሰርዓት ለመኮነን በየትኛውም መድረክ ድምጻቸው አልተሰማም ይህ ጉዳይ አሜሪካንን በውጭ አለም ያላትን አቋም ፍንትው አርጎ የሚያሳይ በዓለም ሕብረተሰብ ውስጥ በሃገራቸው የተሰራፋውን ባሕልና የእምነት መዛባት በሌላው ለማሰራጨት ግብረ ሰደማውያንን መደገፍና ከሰባዊ ረገጣ ማገናኘት ያስተዛዝባል፡ ይህ ጉዳይ ተፈጥራዊ ሳይሆን በራስ አለመተማመን የሚመጣ እንጂ ፈጣሪያችን ሁሉንም አስተካክሎ ለሁሉም ፍጥረቶች አድሏል፡ በፍላጎቱ መሆን የሚፈልግ የግል ውሳኔው ስለሆነ ተቃውሞ የለኝም ነገር ግን ሕግን መጣስ አልደግፍም፡ የወጣው ሕግ መተግበር ይገባል የረጅም ጊዜ እስራት የሚለው ተገቢነት የለውም መሻሻል ያስፈልጋል፡ ወያኔ የሀገሪቱን ባህልና ልምድ ለማኮላሸት ግብረሰዶማውያን ተቀብሎ በኢትዮጵያ ስብሰባ አድርጓል ተቃዋሚዎችን አስሯል ደብድቧል ይህንንም በግልጽ እንደተቀበልው የተረዱት ሞሶቬኒ በግልጽ ተናግረውታል፡
bella says
tnx god this should also happen everywhere and our country
Tewodros says
ይህ በሃገራችን ከአጸያፊም አልፎ ከህብረተሰቡም ገለልተኛ የሚያደርግ ነዉ ወሬዉን ስትሰማ እንኴን ይሰቀጥጣል ሴት ወይም ወንድ ባልጠፋበት ይህን ተግባር መፈጸም ለጆሮም ይሰቀጥጣል በፈጣሪም ትእዛዝ(በመጽሐፍ ቅድሱ ውስጥም ) በመተላለፍ ቅጣት ተደርጓል እስኪ ከታች የተጻፈዉን እነሱ የሚሉትን እንኴን በማንበብ ብቻ ምን ያሀል እንደሚያስጠላ
በአሜሪካ የፕሬዚዳንት ኦባማ አፈቀላጤ የህጉን መጽደቅ “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸውታል ዑጋንዳ ባስቸኳይ ሕጉን እንድትሰርዝ የጠየቁ ሲሆን አሜሪካ ከዑጋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምታጤነውም ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንም በበኩላቸው የሕጉን መጽደቅ የኮነኑ ሲሆን የተወሰኑ የአውሮጳ አገራት ለዑጋንዳ የሚሰጡትን ዕርዳታ እንደሚያቋርጡ ዝተዋል
በበኩሌ አሳፋሪ ሆኖ አግኝቸዋለሁ በመጨረሻም አገራችንም የዑጋንዳን ፈለግ መከተል እንዳለባት አምናለሁ
ሰላም says
ጎልጉሎች፣ ይህን ጉዳይ ማቅረባችሁ ያስመሰግናችኋል። ከታች ያለውን አግኝቼ ላክሁላችሁ። በደህና ቆዩ።
http://ethiopianchurch.org/en/editorial2/102-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%8A%90-%E1%88%9D%E1%8C%8D%E1%89%A3%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%88%B4%E1%89%B6%E1%89%BD.html#disqus_thread
Solomon says
የሞራል ዝቅጠትን እንታገል፡፡ እነኝህ ሰዎች የአለምን ህዝብ ማዝቀጥና እንደእንሰሳ መግዛት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
MASRESHA says
የእኛስ መሪዎች የሃይማኖት አባቶችና የፖለቲካ መሪዎች መንግሥት ምን ይላሉ? ትውልድ እያበላሸ ያለውን ይህንን ተግባር በአደባባይ ሊዋጉት ይገባል፡፡ ድህነት ሰዶማዊነትን በመቀበል ወይም በማስተናገድ አይጠፋም ይከፋል እንጂ፡፡
Zemen says
“አላየሁም : አልሰማሁም : አልናገርም” የሚል ወግ አጥባቂ ባህል ውስጥ አየኖርን የህን ጉዳይ አንደ አንድ ተዓኣምር አድርገን ማውራት መጀመራችን ያስቀኛል፥፥ ወደድንም ጠላነም ለተመሳሳያ ጾታ ፈላጎት ያላቸው ሰወች በአግራችን ከድሮም ነበሩ ፥ አሁንም አሉ ፥ ወደፊትም ይኖራሉ፥፥ ለዚህ በቂ ማስረጃው “ሚስቱ ናቀችው” “ሚስቱ ከጎረቤት ወለደች” “ሴታሴት ወንድ” “ወንዳወንድ ሴት” “ፍናፍንት” አና መሰል አባባሎች ሞኝ አይዎራም በሚል ዘይቤ ታፍነው ሰሜቱም ያላቸው በባህል በሃይማኖት ሰበብ የውስጣቸውን አፍነው ለአመታት ይኖራሉ ። ትልቁ ጥያቄ “ለምን አንደዚህ ሆኑ?” የሄም ጥፍት ከሆነ መስተካከል የሚችልም ነገር ከሆነ በምን መልኩ ልንረዳቸው አንችላለን ብሎ በመጠየቅ የመጽሃፍ ቀዱሰንና ሌሎች የሃይመኖት መጽሃፎች በማጣቀስ ያገደሉ ያታሰሩ ማለት ምን ያህል አርቆ ማሰብ ማስተዋል የተሳነን ጫካ ውስጥ አንደሚኖር ያልሰለጠነ ማህበረሰብ ሰበዓዊነት የጎደለን ሑዋላ ቀር መሆናችንን ያሳያል::
ሲጀመር ሲጀመር የሄን ጉዳይ ሆን በሎ መንግስት ያቀናበረው ካሉት ማህበረሰባዊ ፥ ኢኮኖሚያዊ ጥያቀዎች መመለሰ ባለመቻሉና ለቀጣዩ መርጫ ተፈቃሪ መስሎ ለመቅረብ የጠነሰሰው ሴራ ነው አንጂ አሁን ማን የሙት የሄ ጉዳይ በሃገራችን አንዲህ ጉድ ሆኖ ከኑሮዋችን የሚያሰናክለን ተልቅ ጥያቄ ነው?? አይደለም። ችግር ያለባቸውን በቁጥር አዚህ ገቡ የማይባሉ አቅም የሌላቸውን ሚስኪን ወጣቶችን መርጦ አንዲህ ያለ የጥላቻ ዘመቻ ማካሄድ ሀሊና ካለው ሰው የሚጠበቅ ነው?? በበኩሌ አንደዚህ ያሉን ሰዎች የሰነ-ልቦና መክር መስጠት : ፍቅር ማሳየት አና ወደባሰ የብችኝነትና ራስን የመጉዳት አዝቅት ሳይገቡ መርዳት አንጂ አንደ ወደቀ ዛፍ ምሳር አብዝቶ የራሴን ወንድም አና አህቶች መግደል አልፈልገም ::
gizachew says
this is realy immoral every body must fight against this