• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!

February 24, 2014 06:20 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ነጐዱ። ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች አምባገነን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል።

በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በዓለም ዙሪያ በተለያየ ዘመን ወደ ሥልጣን ከመጡት መሰል ፀረ-ሕዝብ መንግሥታት ቢብስ እንጂ በምንም መልኩ የተሻለ አይደለም።  ፋሽዝምን እንቃወማለን፣ እናወግዛለን እያለ በጫካ ያናፋ የነበረው ወያኔ ዛሬ በዲሞክራሲ ድባብ ሥር እየተገበረው ያለ አገርና ሕዝብን ማዋረድና መዝረፍ፣ መቀጣጫ እያለ በግፍ ማሰርና መግደል ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? በአዲስ አበባ ፣ በጋምቤላ ፣ በአዋሳ ፣ በወለጋ ፣ በሰሜን እና በአራቱም ማእዘን የኢትዮጵያ ክልሎች በየእለቱ በወያኔ ታጣቂዎች እየተካሄደ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ምን ብለው ይጠሩታል?

ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል፤ አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደ አቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የወያኔ መንግስት መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የዚህ ጽሁፌ ዋና አላማ የወያኔ መንግስት የፋሽስት አገዛዝ ስለመሆኑ ምሳሌዎችን አንድ ሁለት በማለት ነቅሸ በማሳየት ማስረገጥ ሲሆን ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ ያካሂድ የነበረውን የንፁሃን ወገኖቻችንን ጭፍጨፋ ለማስረጃነት በማንሳት ለማሳየት እሞክራሉ።

  • ወያኔ በ1969 መጀመሪያ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያ በመፈፀም ፋሽስታዊ ጉዞውን ሀ ብሎ ጀመረ። ግድያው ሳያንሰው የንፁሃን ዜጐችን ሃብትና ንብረትም ወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖረበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል።
  • ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በ1984/5 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አደረሰ። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል፤ የተገደሉትንም ቤት ይቁጠራቸው። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ በመሆን የፋሽስቱ ወያኔ የግፍ ፅዋ ገፈት ቀማሽ ከመሆን አላለፈም።
  • ወያኔ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀልን ማንም ይረሳልዋል ብየ አላስብም? ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይም ይገኛሉ።
  • የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በወያኔ ወታደሮች ተቃጥሎበታል፤ ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል።
  • የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ይገኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል።

እንደው በደፈናው በአገራችን ታሪክ ውስጥ በሕዝባችን ከቶም እንደ አሁኑ ሳንጃ በአንገቱ ላይ ተወድሮ ጦር ተሰብቆበት የሚገኝበት የፋሽስታዊ አገዛዝ ጊዜ የለም። ፋሽዝም ዛሬ በወያኔ/ህወሃት ጊዜ ነግሷል ሥርም ሰዷል። በሥልጣን ላይ ለመቆት፣ ሃብቷን በዝብዞና ሽጦ ለማፈራረስ በታቀደው የአገዛዝ ሽብር ተግባር፣ ፋሽዝም በዴሞክራሲ ታዛ ሥር ወያኔ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ እየፈጸመው ያለ ለመሆኑ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ይረዳውል ብየ አምናለሁ። ፋሽስት ሕዝብ ይጨፈጭፋል፣ ያስፈራራል፤ ፋሽስት የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳን ያስፋፋል፣ ውሽት ይዋሻል፤ ፋሽስት ትምክህተኛና ጦርነት ፈላጊ ነው። ፋሽስት ራስ ወዳዶችን፣ ሆዳሞችን፣ ግብዞችን፣ ዱርየዎችን መሳሪያ ያደርጋል፤ ፋሽስት ድርጅቶችን ያስፋፋል፣ ተለጣፊ ያበዛል ወዘተ። እንግዲህ የፋሽስት አገዛዝ ባህርያትን ማንሳቴ ወያኔን በነዚህ ባህሪያትም መዝነን ፍረጃችንን ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ በማሰብ ነውና መዝኖ ፍርድ መስጠቱን ለእናንተው ትቻለሁ።

ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እጁን በንፁኃን ዜጎች ደም የታጠበው የወያኔ አገዛዝ ሕጋዊ የአምልኮት ነፃነታቸው ያለምንም የአገዛዙ ጣልቃገብነት እንዲከበር የጠየቁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን በጅምላ በሃይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ወንጅሎ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል። በክርስቲያን እምነት ተከታይ ወገኖቻችንም ተመሳሳይ ግፍ ሲፈፀምባቸው ተመልክተናል። ገዳማትን ማፍረስና መነኮሳትን ማሳደድና መግደል የወያኔ መለዮው ሆኗል። ወያኔ ንፁኃን ዜጎችን ከማሰቃየት፣ ከማሰርና ከመግደል የታቀበበት ወቅት ከቶውንም የለም፤ አልታየምም።  ድብደባው፣ ማሰሩና ግድያው እየተፈጸመ ያለው በሁሉም የሃገሪቷ ክፍሎች በሚኖሩ ንፁሃን ዜጐች ሲሆን በግፍና በገፍ ወደ እሥር ቤት የማጎር እርምጃዎች ያልርኅራሄ ተፈጽመዋል፤ እየተፈጸሙም ነው።

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በኢትዮጵያዊ ትዕግሥትና አርቆ አስተዋይነት በፋሽስቱ ወያኔ ወገን ሲደበደብ፣ ሲባረር፣ ሲገደል፣ ሃብት ንብረቱ ሲዘረፍ፣ ዳር ድንበሩ ሲወሰድ፣ በቋንቋ ልዩነት ሲመደብ፣ የተማረ ወገን ሲገደልና ሲሰደድ፣ አገር ለውጭ ባለሃብት ስትሽጥ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን እስከ አሁን በደልን ተሸክመህ በዝምታ ታግሰሃል። ዛሬ በፋሽስቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ተደፍራለች፣ ሕዝቧ ተዋርዷል፣ የታሪክ ክብሯ ተንቋል። ለብዙ ሺህ አመታት የኛ ቀደምት ትውልዶች አጥንትና ደማቸውን በማፍስስ ታፍራና ተፈርታ የኖረች አገር ዛሬ በዚህ ወቅት የትውልድ መካን ሆና ጥቃቱና ጥፋቱ እጅግ ተነባብሯል። ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሆይ! ፍርሃት ከአደጋ የመከላከያ ባህሪ እንጂ እየሸሹ ለመጥፋትና ለመሞት አይደለም። ይህ ጭቆናና ጥቃት ሊያበሳጭ፣ ሊያናድድህና ሊያስቆጣህ ይገባል። ሰው ነህና ለመብትና ለነፃነት መታግልና ለመጭውም ትውልድ ለልጆችህ አገር ማቆየት ይኖርብሃል። የኛ ቀደምት አባቶችና እናቶች እኛ ሞተን አገር ትኑር ብለው ለኢትዮጵያ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ታሪክ ምስክርነትዋን መዝግባለች። ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ወኔና ጀብዱ፣ አትንኩኝ ባይነት ይደገም። ወያኔ ኢትዮጵያዊነት የሌለው አረመኔ ፋሽስት ነውና፤ መወገድ አለበት። ስለዚህ ለትዕግሥት ገደብ እንስጥ፣ አንዋረድ ፣ ትውልድ እንጠብቅ፣ አገርና ሕዝብ እናድን።

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

ለአስተያየትዎ፡ kiduszethiopia@gmail.com አድራሻየ ነው።

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule