በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤
በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሃከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሃት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልጹ ጥቂቶች በብዙሃኑ ደም ዎኝተው የበላይነታቸውን በአቋራጭ ለማረጋገጥ የነበራቸው ህልም መና መቅረቱ የኮሚኒቲው ማህበር ከህግ እና ስረአት ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የማይበገር መሆኑንን ያረጋጋጠበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። በተለይ ይላሉ እኚህ አስተያየት ሰጪ ጉዳይ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ በሚመለከታቸው አካላቶች ትኩረት ሳይሰጠው ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አያሌ ወገኖች ዘግናኝ የሆነ ነገር ውስጥ ሊገቡ ይችሉ እንደነበር አውስተው ሶሻል ሚዲያዎች አደጋ ከመድረሱ በፌት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው የህዝቡን እሮሮ በማስተጋባት የኮሚኒቲውን አባላት ከአሰቃቂ ግጨት በመታደጋቸው ሊመስገኑ ይገባልም ብለውል።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በዲያስፖራው ዘንድ ተደማጭነት እና ክብር ያላቸው 3 ዲፕሎማቶች ኤንባሲውን ወክለው በታዛቢነት መገኘታቸውን የሚናገሩ ምንጮች ስብሰባው ያለምንም ስጋት እና ሁከት በሰላም እንዲካሄድ ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጋቸውን አክለው ገልጸዋል። በስብሰው ወቅት የኮሚኒቲው ስራ አመራር የ20 ወራቱን የስራ ሪፖርት በማስደመጥ በአባልቱ መሃከል ከፍተኛ ውይይት መድረጉን የሚናገሩ እማኞች በስራ አመራሩ የቀረበው ሪፖርት በአብዛኛው አባላት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ሳይሽሽጉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኮሚኒቲው ሊቀምንበር አቶ ቃሲም ያሲን በቀረብው ሪፖርት ዙሪያ ከአድማጮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በመስጠት በጉባኤው ተሳታፊዎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ከመደረጉም በላይ የኮሚኒቲው ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል በኮንተራት ለግለስቦች ቢተላለፍ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ከአንድ አድማጭ የተሰነዘረውን ሃሳብ የኤንባሲው ተወካይ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር የኮሚኒቲው ንበረት ለዲያስፖራው ያለውን አጋርነት እና ጠቀሜታ በዝርዝር በማስቀመጥ የኮሚኒቲው ንብረቶች በኤንባሲው ስር እንደመሆናቸው መጠን አካሄዱ ህጋዊ መስረት ሊኖረው ስለማይችል የቀርበውን ሃሳብ ውድቅ በማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጠዋል፡፤
የማህበሩ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል የሆነው ካፍቴሪያ ዘንድሮም 61 ሺህ ሪያል ኪሳራ ማሳየቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል። በዚህ ስብሰባ ላይ የሃይማኖት አባቶች የህገር ሽማግሌዎች ጨምሮ ከኤንባሲ 1/ ክቡር አቶ አህመድ ጠላህ 2/ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር 3/ ክቡር አቶ መስፍን ድባቡ መገኘታቸውን የሚገልጹ የኮሚኒቲው አባላት ከስጋት እና ጭንቀት ይልቅ የጉባኤውን ምሸት በነጻነት ማሳለፋቸውን አስረድተዋል። ለጉባኤው የቀረበ የተባለው ሪፖርት ግልባጭ በእጃችን እንደገባ ሰሞኑን በዚህ ገጽ በስፋት ለመዳሰስ ይሞከራል።
(Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት)
Leave a Reply